2011-07-29 13:34:44

ቤተ ክርስትያን እና ፖለቲካ


የስዊዘርላንድ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት እ.ኤ.አ. ነሐሴ 1 ቀን 2011 ዓ.ም. በአገሪቱ ለሚከበረው የፈደራላዊ ዓመታዊ በዓል ምክንያት ባስተላለፉት ሐዋርያዊ የግብረ ኖውሎ መልእክት፣ ቤተ ክርስትያን የአንዱ ፖለቲካ የምትደገፍ ሰልፈኛ ፖለቲካ የምታንጸባርቅ ሳትሆን፣ በፖለቲካው ሂደት ድምጽ ለሌው ድምጽ በመሆን ሀሳብዋን በማቅርብ በማኅበራዊው ሕይወት ንቁ ተሳታፊ ነች የሚል ሐሳብ እንዳሰመሩበት ተገለጠ። የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ያስተላለፈው መልእክት እፊታችን ሰኞ በጠቅላላ በአገሪቱ በሚገኙት ቁምስናዎች በይፋ እንደሚነበብም የአገሪቱ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ድረ ገጽ ካሰራጨው ዜና ለመረዳት ተችለዋል።

ቤተ ክርስትያን ከፖለቲካው ጉዳይ የተገለለች አይደለምች፣ በኅብረተሰብ ዘንድ የምትኖር ከኅብረትሰብ ጋር አብራ የምትጓዝ ስትሆን ለአገር እና ለመላው ዜጋ ጥምቅ እንዲተኮር የምታነቃቃ፣ ፖሊቲካ የላቀው ክብሩን ጠብቆ ለሕዝብ አና ለአገር አገልግሎት መሆኑ ለማረጋገጥ እና ቤተ ክርስትያን ካላት የዓለማዊነት ትሥሥር ገጠመኝ በተለይ ደግሞ ባላት ኵላዊነት ባህርይ መሠረት ካካበተቸው ልምድ የፖለቲካው ዓለም ተገቢ እና ለሰው ልጅ ክብር ልክነት ያለው መፍትሔ እንዲያረጋገጥ ትብብርዋን እና ድጋፍዋንም ጭምር እንደምታቀርብ እና በዚሁ ጉዳይ ላይም ሐሳብዋን እንደምታጎላ የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት መልእክት እንዳሰመረበት ከምክር ቤቱ ድረ ገጽ ለመረዳት ተችለዋል።

ለድምጽ ውሳኔ ሳይሆን ወንጌልን በመከተል ገዛ እራሷን በወንጌል በመመዘን ምንኛ ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታማኝ መሆንዋ በመገምገም የምትኖር በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የምትመራ እንጂ የፖለቲካ ሰልፍ አይደለችም፣ የአንዱ የፖለቲካ ሰልፍ ደጋፊም አትሆንም፣ ስለዚህ ለሁሉም የሚበጅ የአገር እና የሕዝብ ጥቅም እንዲረጋገጥ ሰውን ማእከል ያደረገ አመለካከት የምታመለክት መሆንዋ የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት መልእክት አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.