2011-07-22 16:47:01

ድርቅና ረሃብ በአፍሪቃ ምሥራቃዊ ክፍል


በሶማልያ ተከስቶ ባለው ድርቅና ረሃብ የዓለም ማኅበረሰብ እንዲንቀሳቀስና ሁነኛ የነፍስ አድን እርምጃ እንዲወስድ የዓለም የተባበሩት መንግታት ዋና ጸሐፊ ባን ኪሙን ጥሪ አቅርበዋል፣ የሰው ሕይወት እያጨደ ያለው በአፍሪቃ ቀንድ በተለይም ሕፃናትን እያጠቃ ያለው ድርቅና ረኃብ በተባበሩት መንግሥታት የረሃብ አደጋ ተብሎ መታወጁ የሚታወስ ሲሆን ሰዎች እርዳታ ለመፈለግ እንደ ጐርፍ እየተጓዙ መሆኑ ተገለጠ፣ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ ባን ኪሙን ሁኔታውን አስመልክተው። ለአባል አገሮች ባቀረቡት ጥሪ ለፈጣኝ እርዳታ የሚውል ቢያንስ 3.5 ሚልዮን የሚገመቱ የሰው ሕይወቶች ለመዳን 1.6 ቢልዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ገልጠዋል፣ የዓለም ማኅበረሰብ የሶማልያን ሕዝብ አሁኑኑ ካልረዳ በጎረቤት አገሮች እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ እንደሚከሰትም አስጠንቅቀዋል።።
ይህ በእንዲህ ሳለ የአፍሪቃ ካሪታስ (ግብረ ሠናይ ማኅበር) ይህ በየአፍሪቃ ምሥራቃዊ ክፍል በተለይም በአፍሪቃ ቀንድ በሚታወቀው ክፍል በድርቅና ረኃብ ተከስቶ ያለው አስከፊ ጥፋት ለመጋፈጥ በየዞኑ ያሉ የካሪታስ ማኅበሮች የተቻላቸውን ያህል እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል።። እንደ ካሪታስ አፍሪቃ ግምት በምሥራቅ አፍሪቃ በሶማልያ ኢትዮጵያ ኤርትራና ኬንያ 10 ሚልዮን የሚገመት ሕዝብ ፈጣኝ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።። ሶሊዳሪቲ ፋንድ የተባለው የምግባረ ሠናይ ድርጅት በእነዚህ አገሮች ለሚገኙት የካሪታስ ማኅበሮች ለህዝቡ እንዲያዳርሱ በካሪታስ አፍሪቃ በኩል 25 ሚልዮን ኤውሮ እርዳታ እንደሰጠም ጽሕፈት ቤቱ አመልክተዋል፣
ፊደስ ለሚባለው የዜና አገልግሎት በላከው ዘገባ መሠረት ካሪታስ አፍሪቃ አሁን በተከሰተው ችግር ፈጥሮ ለመድረስና ለመርዳት ብቻ ሳይሆን ጽሕፈት ቤቱ የአፍሪቃ ጳጳሳት ሲኖዶስ በሮም ባካሄደው ጉባኤ አደራ እንዳለው በዞኑ ጳጳሳት ጉባኤዎች በሚገኙ የተለያዩ ሃገረስብከቶች መካከል የአጋርነትና መረዳዳት መስመር እየፈጠረ ነው፣ አሁን ሊደረግ የታቀደው በሃገረ ስብከቶች መካከል በካሪታስ አውታሮች አመካኝነት የጋራ የድጋፍ ገንዘብ መዋጮ አሰባሳቢ ማኅበር ማቋቋም መሆኑን አመልክተዋል፣
በተጨማሪም ካሪታስ አፍሪቃ በመላው ዓለም የሚገኙ የእርሱ አባላት ለዚህ አንገብጋቢ ሁኔታ የሚውል እርዳታ ለመሰብሰብ በሁሉም አውታሮችና ተቁዋሞች የተቻላቸውን ያህል እንዲያደርጉና እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል፣
በሌላ በኩል ደግሞ ዓለም ዓቀፍ የምግብ እርዳታ ድርጅት ወይም ፋኦ በረሐብ ለሚሠቃየዉ የአፍሪቃ ቀንድ ሕዝብ የሚሆን የ120 ሚልዮን ዶላር እርዳታ የሚያሰባስብበት ሁኔታ ለመፍጠር እፊታችን ሰኞ እአአ ሐምሌ 15 ቀን 2011 ዓም ዓለም አቀፍ ኣስቸኳይ ጉባኤ በሮም እንዲካኤድ ጥሪ አቅርበዋል፣ የድርጅቱ ጠቅላይ ዳይረክተር ከዛሬ ሐምሌ 22 እስከ 24 ቀን ቦታውን እንደሚጐበኙም ተያይዞ የመጣ ዜና አብራርተዋል፣ የድርጅቱ ቃለ አቀባይ ትናንትን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በሶማልያ ውስጥ ያለው የእርዳታ ፈላጊ ህዝብ ቁጥር ክ2.4 ሚልዮ ወደ 3.7 ሚልዮን ከፍ ማለቱን አመለከተ፣ ባኩል ባሳ ሻበለ በሚባሉ የሶማልያ ክልሎች ረኅቡ እጅግ ከፍ ብለዋል በየዕለቱ ክ10,000 ሰዎች 6 እንደሚሞቱም አመልክተዋል፣ የድርጅቱ ዘገባ እንደሚያመለክተው ።ሶማሊያ፥ ኢትዮጵያ፥ ኬንያ፥ ጁቡቲና ዩጋንዳ ዉስጥ አስራ-ሁለት ሚሊዮን ያሕል ሕዝብ በረኃብ አለጋ እየተገረፈ ነው።።








All the contents on this site are copyrighted ©.