2011-07-13 09:56:24

እግዚአብሔር በእርሱ እንድናምን አያስገድደንም፣ ሆኖም ግን በፍቅሩ ወደ እርሱ ይስበናል።


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ትናንትና ረፋድ ላይ ለበጋ ዕረፍት ከሚገኙበት ካስተል ጋንደልፎ ሐዋርያዊ አደራሽ በብዙ ሺ ከሚቆጠሩ ምእመናንና ነጋድያን የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት። “የእግዚአብሔር ፍቅር የሰው ልጅ ነጻነትን ስለሚያከብር። እግዚአብሔር በእውነትና በርኅራኄው ወደ እርሱ ይስበናል እንጂ በእርሱ እንድናምን አያስገድደንም” ሲሉ አስተምረዋል፣ የትናንትናው እሁድ ዓለም አቀፍ የባሕር እሁድ ሆነ በመታወሱም በተለያዩ የባሕር ወንበዴዎች ታጒረው የሚገኙ ሁሉ ነጻ እንዲለቀቁ ጥሪ አቅርበዋል፣
ባለፈው እሁድ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ እንዳሳሰቡት። ቅዱስነታቸው በሰሜኑ ንፍቀ ክበብ የበጋ ወራት በመሆኑ። ለበጋ ዕረፍት ከሚገኙት የካስተል ጋንደልፎ ሐዋርያዊ አደራሽ። የበጋ ወራት የመጀመርያ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ጉባኤ ኣስተምህሮ ባቀረቡበት ብዙ የአከባቢው ምእመናንና ከተለያዩ ቦታዎች የተሰበሰቡ ነጋድያን በጭበጨባና በሆሆታ ደስታቸውን ገልጠዋል፣
ቅድስነታቸው የዕለቱን ቃለ ወንጌል ተመርኲዘው የዘር ምሳሌን እንደ መነሻ በመውሰድ። “መልካም ዘር የሆነውን የእግዚአብሔ ቃል የሚዘራና መልካም ዜናውን እንደሰዎቹ አቀበባል ዓይነት የትለያየ ውጤት መገኘቱን የሚያስተውል ዘሪው ኢየሱስ ነው።” ብለዋል፣ አያይዘውም “አንዳንዱ ቃሉን እንደነግሩ የሚሰማ ግን ምንም የማያፈራ፤ ሌላው ደግሞ ለግዜው በስሜት የሚቀበለው ሆኖም ግን ወላዋይ በመሆኑ ወዲያውኑ ሁሉን የሚያጠፋ፤ አንዳንዱ በዚሁ ዓለም ፈተናና ምቾት እንዲሁም በሌላ ሐሳብና ሥጋት ስለሚጨነቅ ምንም ሳላፈራ ታንቆ የሚቀር፤ ሌላው ደግሞ እንደ መልካም መሬት ቃሉን ጠንቅቆ በመስማትና አመርቂ ፍሬ በማፍራት ቃሉን የሚሰማ አለ” ብለዋል፣
ሐዋርያት ኢየሱስን ለምን በምሳሌ እንደሚናገር በጠየቁት ግዜ። በሐዋርያቱና በሌሎች አሕዛብ መካከል ልዩነት እንዳለ ይግልጥላቸዋል፣ ለሐዋርያቱ ማለትም እርሱን ለመከተል ለወሰኑ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት በግልጥ ሊናገር ይችላል፣ ለሌሎች ግን ልባቸውን በመለወጥ ወደ ውሳኔ እንዲደርሱ እንዲገፋፋቸው በምሳሌ ይናገራቸውል። ምክንያቱም በምሳሌ መናገር አንጎላችንን እንደሚያስብና የምሳሌውን ትርጉም እንደሚርዳ ያደጋሉ፣ እንዲሁም ነጻነታችንን መልእክቱን ለመርዳትና ለመወሰን ይረዱታል። በማለት የምሳሌውን ትርጉም አብራርተዋል፣
ቅዱስነታቸው ትምህርታቸውን በመቀጠል የኢየሱስ በምሳሌ መናገር ትርጓሜ። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን እንደ ምሳሌ በማቅረብ የእርሱን ትምህርት እንዲህ ሲሉ ገልጠዋል፣ “ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ “ኢየሱስ እነዚህን ቃላት የተናገረበት ምክንያት የሚሰሙትን ወደ እርሱ ለመሳብ ወደ እርሱ የመጡ እንደሆነም እንደሚያድናቸው ለማስረዳት ነው።” ሲል ያብራረዋል” ብለዋል።። የዚህ ምሳሌ ዋና መልእክት ኢየሱስ ራሱ ጥልቅ የእግዚአብሔር ምሳሌ ስለሆነ። በእርሱ ሰብአውነት የእግዚአብሔር መለኮታዊነትን የሚገልጥና የሚሸፍን የእግእዚአብሔር አካል ራሱ ኢየሱስ ነው። በዚህ መንገድ እግዚአብሔር በእርሱ እንድናምን አያስገድደንም፣ የእግዚአብሔር ፍቅር የሰው ልጅ ነጻነትን ስለሚያከብር። እግዚአብሔር በእውነትና በርኅራኄው ወደ እርሱ ይስበናል፣
ቅዱስነታቸው በላቲኑ ሥርዓተ አምልኮ ግጻዌ ነገ የኤውሮጳ ጠባቂ የሆነው የቅዱስ አቡነ ብሩክ ዝክረ በዓል መሆኑን በማስታወስ አብነቱን እንድንከተል እንዲህ ሲሉ አሳስበዋል፣ በሰማነው ቃለ ወንጌል ብርሃን በሚመለከት ቅዱስ አቡነ ብሩክን ቃለ እግዚአብሔር የመስማት አስተማሪያችን ያደረግን እንደሆነ ቃለ እግዚአብሔርን በጥልቀትና በጽናት ለማዳመጥ ከእርሱ እንማራለን፣ ከዚሁ የምዕራባውያን ምንኲስና ትላልቅ አበው አንዱ ከሆነው እንዴት አድርገን ለእግዚአብሔር በሕይወታችን የሚገባውን ቦታ ማለት የመጀመርያውን ቦታ ለመስጠት እንደምንችል እንማር። ማለትም በጥዋትና ማታ ጸሎት ዕለታዊ ተግባራችንን ወድ እርሱ በማማጠን ለእግዚአብሔር በልባችን የመጀመርያውን ቦታ ለማስያዝ እንችላለን°። እመቤታችን ድንግል ማርያም በእርሷ አምሳይ መልካም መሬት ሆነን የቃሉን ዘር ብዙ ፍሬ ለማፍራት ትርዳን” ካሉ ብኋ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት አሳርገዋል፣
ከጸሎቱ በኋላ በዕለቱ የሚታወሰው የባሕረኞችና ዓሣ አጥማጆች ሐዋርያዊ ግብረ ተልእኮን ለማስታወስ የባሕር ሰንበት ምክንያት በማድረግ ለሁሉም ባሕረኞችና ቤተሰቦቻቸው በጸሎት እንደሚያስብዋቸው ገልጠዋል። በተለይ 800 የሚገመቱ በተለያዩ የባሕር ሽፍቶች ታጉረው ስላሉት እንደሚጸልዩ አውስተው ይህንን ጥሪ አቅርበዋል፣
እንኚህ እስረኞች በሰብአዊ ርኅራኄና ክብር እንዲያዙ እማጠናለሁ። በእምነት እንዲጸኑና ከሚወድዋቸው ተሎ እንደሚገናኙ ተስፋ እንዲያደርጉ ስለቤተ ሰቦቻቸውም እጸልያለሁ። በማለት መልእክታቸው አስተላልፈዋል፣
በመጨረሻም በተለያዩ ቋንቋዎች በማመስገንና የሰሜኑ ንፍቀ ክበብ የበጋ ዕረፍትን በማስመልከት ቤተ ሰቦች ልጆቻቸውን ተፈጥሮን እንዲያደንቁና እንዲያፈቅሩ እንዲያስተምሩዋቸው። የዕረፍት ግዜም በቅዱስ ቊርባንና በጸሎት እንዲሁም በመልካም ሥራ ወደ እግዚአብሔር የምንቀርብበት ግዜ መሆኑን አሳስበዋል፣ ለሁላቸውም መልካም እሁድ በመመኘት ሐዋርያዊ ቡራኬ ችረዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.