2011-07-11 13:47:43

አዲሲቷ ሉአላዊት ሃገር፦ የዜጎችዋ ደስታ እና ተስፋ


ባለፈው ቅዳሜ የደቡብ ሱዳን ሉአላዊነቷ በይፋ በታወጀበት ዕለት በተለያዩ አገሮች የሚኖሩት የዚህች አዲሲቷ አገር ዜጎች በታላቅ ደስታ ቀኑን አክብረው መዋላቸው ተገለጠ። ይህ ክልል በቆዳው ሥፋት አንጻር ሲታይ ስፐይን እና ፕርቱጋል RealAudioMP3 ቢጠቃለሉም በልጦ የሚገኝ ቢሆንም ቅሉ የዜጎቹ ብዛት ግን ከ10 ሚሊዮን በታች እንደሆነ ነው የሚነገረው።

ደቡብ ሱዳን በነዳጅ የማዕድን ሃብት የታደለ ሆኖ ነገር ግን ያለው የልማት ዕድገት በዓለም አቀፍ ደረጃ በጣም ዝቅተኛ በሕፃናት የሞት መጠን በእጅግ የተጠቃ በመሃይምነት የተጠቁ የክልሉ ሴቶች ብዛት 84 በመቶ የሚለካ ሲሆን፣ ይኸንን ሁሉ እግምት ውስጥ በማስገባት የደቡብ ሱዳን የልማቱ ዕቅድ የተጋረጡበት እክሎች ቀላል እንዳልሆነ ሚስና የዜና አገልግሎት ካጠናቀረው ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።

የደቡብ ሱዳን ሉአላዊነት በይፋ በታወጀበት ዕለት የተከናወነው ሥነ ሥርዓት የቀድም የደቡብ ሱዳን የነጻነት ግንባር አባላት ባቀረቡት የወታደራዊ ሠልፍ ትርኢት በተለያዩ ዘፈኖች እና ባህላዊ ውዝዋዜዎች የተሸኘ፣ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሓፊ ባን ኪ ሙን፣ የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የኤውሮጳ ህብረት የአፍሪካ ኅብረት ልኡክን እንዲሁም የሰሜን ሱዳን ርእሰ ብሔር ኦማር አል ባሺር በክብር እንግድነት የተገኙበት እንደነበርም የዜናው አገልግሎት አስታወቀ።

የአዲሲቷ 54ኛይቱ የአፍሪቃ አገር ርእሰ ብሔር ሳልቫ ኪር ቀኑን ምክንያት በማድረግ ባሰሙት ንግግር፣ የደቡብ ሱዳን ነጻ አውጭ ግንባር መሪ የነበሩት እ.ኤ.አ. በ 2005 ዓ.ም. በሁለቱም ሱዳን ወደዚህ የነጻነት ቀን የሸኘው የደቡብ ሱዳን የመጪው እድል በሕዝብ ውሳኔ የሚለው ሐሳብ የተኖረበት የሰላም ስምምነት መፈራረም በኋላ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ጆን ጋራንግን በማሰብ ለነጻነት ቀን የተበቃበት፣ ለዚህ አቢይ ቀን የተደረገው የድል ጉዞ መደረጋገጥ የአንተ አቢይ ጥረት እና የአስተዋጽኦ ወጤት ነው በማለት በምስጋና ቃል እንደዘከሩዋቸው ሚስና የዜና አገልግሎት አመለከተ።

በደቡብ ሱዳን የኮምቦናውያን ማኅበር አለቃ አባ ዳኒኤለ ሞስከቲ ቀኑን ምክንያት በማድረግ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ደቡብ ሱዳን የታገረጠበት ችግር የተለያየ ዘርፍ ያለው መሆኑ ዘክረው፣ ይህ በዓለም 193ኛው አገር እጅግ በድኽነት የተጠቃ፣ የትምህርት የሕክምና አገልግሎት መስጫ መጓደል በስፋት የሚታይበት፣ ማኅበራዊ ገጽታው ገና መደገፍ ያለበት፣ በተለያዩ ጎሳዎች የቆመ ሀገር መሆኑም ገልጠው፣ ስለዚህ ነጻነት ብቻ ሳይሆን ውህደት ጭምር የሚያሻው አዲስ አገር ነው ብለዋል። ስለዚህ በዚች አዲስቷ አገር የተለያዩ የማኅበራዊ ተጨባጭ ጉዳዮች የሚሳተፉበት ማኅበራዊ ሂደት ወሳኝ መሆኑ አብራርተው፣ በዚሁ ዘርፍ የቤተ ክርስትያን አስተዋጽኦ በርግጥ አቢይ ነው። ስለዚህ የተለያዩትን የአገሪቱ ጎሳዎች የምታገናኝ የሁሉም ቤት ነች፣ አንድነቱን የሚያረጋግጠው እሰይታ ላይ እርሱም የክልሉ ሕዝብ ክርስትያናዊ ግንዛቤው ላይ ማትኮር ይኖርበታል ብለዋል።

ገና መፍትሄ የሚያሻው አወዛጋቢ የሚባሉት ጥያቄውች እንዳሉም በመጥቀስ በዚሁ ዘርፍ የአለም ዓቀፍ ማኅበረሰብ ተሳታፊነት ብሎም ሰሜን ሱዳን የነዳጅ የውሃ ሃብት እና የሌሎች የተፈጥሮ የማዕድን ሃብት ተካፋይ ማድረግ አጅግ አስፈላጊ ነው። ሁለቱ አገሮች ተደጋግፈው መሄድ ለክልሉ ሰላም ዋስትና ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.