2011-07-08 16:14:49

የደቡብ ሱዳን ሉአላዊነት፦ ተስፋ እና ኃላፊነት


እ.ኤ.አ. ሐምሌ 9 ቀን 2011 ዓ.ም. የደቡብ ሱዳን ሕዝብ ውሳኔ ያረጋገጠው የሉአላዊነት ፍላጎት በማክበር ደቡብ ሱዳን 54ኛውይቱ የአፍሪቃ አገር በመሆን ይፍዊ ሉአላዊነቷ ነገ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሓፊ ባን ኩ ሙን የተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት የኤውሮጳ ኅብረት የአፍሪቃ ኅብረት የአረብ ሊግ ተጠሪዎች በሚሳትፉበት በዓል በይፋ እንደሚታወጅ ሲገለጥ፣ በደቡብ ሱዳን የሩምበክ ሊቀ ጳጳስ በሱዳን ከሳላሳ ዓመት በላይ በተልእኮ ወንጌል ተሰማርተው በዚሃ ክልል ክርስትያናዊ ሰብአዊ ሕንጸት በማከናወን የሚገኙት ብፁዕ አቡነ ቸሳረ ማዞላሪ “ደቡብ ሱዳን አዲሲቱ ሉኣላዊት አገር ለመሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተገቢው መለያዋን ለመጨበጥ በመብቃትዋ ኩራት ይሰማታል።” በማለት የሰጡት መግለጫ ቸሳር የተስየመው መንግሥታዊ ያልሆነ የግብረ ሰናይ ማኅበር ከሰጠው መግለጫ ለመረዳት ተችለዋል።

የኮምቦኒ ልኡካን ማኅበር ጠቅላይ አለቃ አባ ኤንሪከ ሳንቸስ ጎንዛለስ እና የኮምቦናውያን ደናግል ማኅበር ጠቅላይ አለቃ እናቴ ሉዚያ ፕረሞሊ የደብብ ሱዳን መጪው ሕይወት ብሩህ እንዲሆን በመመኘት በአገሪቱ የሰላም እና የእርቅ ባህል እንዲሰርጽ የክልሉ የተፈጥሮ ሃብት ለዓመጽ ምክንያት ሳይሆን ለጋራ ጥቅም ታልሞ በፍትሃዊ መንገድ እንዲተዳደር ጥሪ ማቅረባቸው ሚስና የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ሱዳን በሰላም እና በጦርነት መካከል በሚል ርእስ ሥር ባለፈው ረቡዕ በሮማ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢጣሊያ በሱዳን የሰላም መረጋገጥ ዘመቻ ተሳታፊዎች የተለያዩ የሰላም አነቃቂ ማኅበራት እና የሰላም ጠረጴዛ የተሰየመው ማኅበር በጋራ ባዘጋጁት መድረክ ለተሳተፈው የኢጣሊያ የክርስትያን ሠራተኞች ማኅበር ምክትል ሊቀ መንበር ፓውላ ቫኪና ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የደቡብ ሱዳን ልኡላዊነት የሚታወጅበት ቀን የበዓል ቀን ነው፣ ቢሆንም ግን ደቡብ ሱዳን ሉአላዊነቷ ታውጀዋል ተብሎ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ለዚህ ክልል ያለው ትኩረት ማግለል አቢይ ስህተት ይሆናል ስለዚህ ከመቼውም በበለጠ ድጋፍ ትብብር ማቅረብ ይጠበቅበታል ብለዋል።

በይፋ ሉአላዊነትዋን የምታውጀው ደቡብ ሱዳን ቀርቦ አገራዊ መለያዋን ለማቆም በምታደርገው ጉዞ በፖለቲካ በኤኮኖሚ እና ማኅበራዊ ዘርፍ እንዲሁም በሰብአዊ ሕንጸት ጉዳይ ትደግፍ ዘንድ የታምቡራ ያምቢዮ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤድዋርድ ሂቦሮ ኩሳላ ጥሪ አቅርበው ከሰሜን ሱዳን ወደ የደቡብ ሱዳን የሚመለሰው የአገሪቱ ዜጋ ብዛት ለይቶ ለማወቅ በተካሄደው የሕዝብ ቆጥራ መሠረት በሳቸው ሐዋርያዊ ኃላፊነት ሥር ወደ ሚመራው ከተማ ብቻ 7 ሺህ እንዳሉ ገልጠው፣ በጠቅላላ ከጥቅምት ወር 2010 ዓ.ም. ወዲህ ብቻ ከሰሜን ሱዳን ወደ ደቡብ ሱዳን የተመለሰው ሕዝብ ብዛት 300 ሺ መሆኑም የተካሄደው የሕዝብ ቆጠራ የሰጠው ውጤት ማስታወሳቸውም ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ዜጎች እንደ የብቃታቸው እና ችሎታቸው ለአገር ግንባታ ማሰማራት ፍትህ እኩልነት በሌላው ረገድ መሠረታዊ የሆነው የጸጥታ እና የደህንነት ጉዳይ መቼም ቢሆን መዘጋት የለበትም፣ ጸጥታ እና ደህንነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ድጋፍ እና ትብብር የሚያሻው አዲስ አገር ነው ካሉ በኋላ አክለውም በላቀው ተስፋ አማካኝነትም ሁሉ የነገው ሕይወት አለ ምፍራት እየተጠባበቀ ነው በማለት የሰጡት መግለጫ እንዳጠቃለሉ ፊደስ የዜና አገልግሎት ካሰራጨው ዜና ለመረዳት ተችለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በዚህ የደቡብ ሱዳን የሉአላዊነት አዋጅ በዓል በምትካቸው ቅድስት መንበርን ወክለው እንዲሳተፉ በሱዳን የቅድስት መንበር ሓዋርያዊ ልኡክ ብፁዕ አቡነ ለዮ ቦካርዲን እና የናይሮቢ ሊቀ ጳጳስ የኬንያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጆን ንየ የተመራ ልኡካንን እንደሰየሙ የድስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል ተጠሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ አስታወቁ።







All the contents on this site are copyrighted ©.