2011-07-05 13:52:58

ብፁዕ ካርዲናል ፒያቸንሳ፦ ለንስሃ አባቶች እና መንፈሳዊ መሪዎች ሕንጸት


የካህናት ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ማውሮ ፒያቸንዛ ይህ በሳቸው የሚመራው ቅዱስ ማኅበር የንስሃ እና የእርቅ እንዲሁም መንፈሳዊ አባቶች (ካህናት) ክርስትያናዊ ቅድስና ላይ ያተኮረ እና ይኸንን ኩላዊው ክርስትያናዊ ጥሪ መርህ በማድረግ የሚደገፉበት አዲስ የተሟላ መመሪያ የሚያገኙበት የዛሬ አራት ወር በፊት በማሳተም ለመላ ዓለም ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት RealAudioMP3 ያሰራጨው ተጨማሪ የድጋፍ ሰነድ በማስመልከት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ እ.ኤ.አ. መጋቢት ወር 2011 ዓ.ም. ዓመት ሐዋርያዊ ቤተ ኑዛዜ አዘጋጅቶት ለነበረው 21ኛው የሐዋርያዊ ቤተ ኑዛዜ የአባላት ውስጣዊ ጉባኤ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ተገኝተው በሰጡት መሪ ቃል፣ ካህናት ምሥጢረ ኑዛዜ የመሥራቱ ቅዱስ አገልግሎት ላይ እንዲያተኩሩ እና እንዲተጉ፣ ይህ በቅዱስ ቁርባን በሙላት የሚገለጠው የእግዚአብሔር መለኮታዊ ምኅረት ማረጋገጫ የሆነው እና ምኅረቱ የሚገኝበት ምሥጢር ምእመናን እንዲያፈቅሩት እና እንዲሆሩት በዚሁ ምሥጢር እንዲሳተፉ ማድረግ የወቅቱ ተቀዳሚ ሓዋርያዊ አገልግሎት መርሃ ግብር መሆን አለበት ያሉትን ቃል ጠቅሰው፣ ይህ የካህናት ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ያንን ቅዱስ አባታችን ቃል መሠረት በማድረግ የእግዚአብሔር መለኮታዊ ምኅረት ኅላዌ ለምእመናን ለማረጋገጥ የንስሃ አባቶች እና አበ ነፍሳት ይኽ የእግዚአብሔር መለኮታዊ ምኅረት ለመመስከር መእመናን ወደ ቅዱስ ቁርባን ለመምራት ያቀደመ መሆኑ በመገንዘብ ካለው ጥልቅ መንፈሳዊ እና ሰብአዊ ትርጉም በመነሳት እንዲሁም ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ በማኅበረ ክርስትያን እና በኅብረተሰብ የሚያስከትለው የመግባባት እና የመረጋጋት መንፈስ ግምት በመስጠት የተዘጋጀ ደጋፊ ሰነድ ነው ብለዋል።

ምእመናን በቅዱስ ቁርባን ማዕድ ሲሳተፍ ማየቱ እጅግ ደስ ያሰኛል፣ በዚህ ማእድ መሳተፍ በምሥጢረ ንስሃ ያለው ተሳታፊት የሚያረጋገጥ መሆን አለበት፣ ሆኖም ግን የቅዱስ ቁርባን ማእድ የተሳታፊው ብዛት ለቤተ ክርስትያን ለሰበካዎች አቢይ ጥያቄ መሆን አለበት፣ ምክንያቱም ቅዱስ ቁርባን የሚካፈለው ምእመን በቀጣይነት እና ሥርዓት የተከተለ የምሥጢረ ንስሃ ተሳታፊ መሆን ይገባዋል። ስለዚህ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ፣ ሁሉም ለቅድስና መጠራቱ እና ኩላዊነት ቅድስና በማለት የሰጠው መመሪያ መሠረት በምሥጢረ ንስሃ እና በነፍስ አባትነት አግልግሎት የሚሰጡ ካህናት የሚመሩበት የድጋፍ ሰነድ ነው።

አዲስ ወይንም ዳግመ አስፍሆተ ወንጌል በነዚህ ሁለት ሥምጢራት የሚጀመር ሐዋርያዊ ተግባር ነው። የአስፍሆተ ወንጌል ተጨባጭ ውጤት በቅዱሳት ምጢራት ተመርቶ የሚኖር የቅዱሳዊ ምሥጢረ ሕይወት ማረጋገጫ ነው፣ ካሉ በኋላ ሰነዱ የንስሃ ምሥጢር ክርስትያናዊ ቅድስና በማስቀደም አክሎም፣ የቅዱስ ኩራቶ ዳርስ የአበ ነፍስ ምስክረንት በማስደገፍ የአበ ነፍስ አገልግሎት ያለው አቢይ እና ጥልቅ ቲዮሎጊያዊ ቤተ ክስትያናዊ ትርጉሙ በማብራራት በነዚህ ምሥጢር የተካኑ ካህናት የነዚህ ቅዱሳት ምሥጢራት ሠሪዎች ብቻ ሳይሆን የሚኖሩት በመሆን አብነት ሆነው በመገኘት እና ምእመናን በቅዱሳት ምሥጢራት የተካነ ክርስትያናዊ ሕይወት እንዲያጎለብቱ ወደ እነዚህ ቅዱሳት ምሥጢራት ለመሳብ የፍቅር ሐዋርያዊ አገልግሎት መሆኑ የሚገልጥ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.