2011-07-01 14:29:36

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ሊቃነ ጳጳሳት ከክርስቶስ በፊት ምንም ነገር አለ ማስቀደም ከቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ጋር ልዩ ትሥሥር እና ኅብረት ማሳየል


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ከትላትና በስትያ በላቲን ሥርዓት በተከበረው ዓመታዊ በዓለ ቅዱሳን ጴጥሮስ ወጳውሎስ ምክንያት ለተለያዩ ከተሞች ሊቃነ ጳጳሳት እንዲሆኑ ለሾምዋቸው 41 ብፁዓን ጳጳሳት የቅዱስ ጴጥሮስ የቃለ ተአምኖ ምልክት አክሚም እርሱም ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ለሚጸናው ምልክት ማቴ. 11,29-30 “ቀንበሬን በጫንቃችሁ ተሸከሙ RealAudioMP3 ከእኔም ተማሩ እኔ የዋህና ትሁት ነኝ፣ ለነፍሳችሁ ዕረፍት ታገኛላችሁ…ቀንበሬ ልዝብ ነው ሸክሜም ቀላል ነው” የሚለውን ቃለ ወንጌል የሚገልጥ የፈቃዱ እና የፍላጎቱ እርሱም የእውነት እና የፍቅር ፈቃድና ፍላጎት የሆነው የክርስቶስ ቀንበር የጓደኝነት ምልክት የማኖር ቅዱስ ሥነ ሥርዓት የፈጸሙላቸውን ብፁዓን ሊቃነ ጳጳስት ትላትና ቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ ተቀብለው የጋራ እምነት መግለጫ የሆነው የቤተ ክርስያን ውኅደት እና አንድነት ማረጋገጫ ማእከል ያደረገ መሪ ቃል መለገሰቻው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ቅዱስ አባታችን ከመረጠን ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፊት ሊቃነ ጳጳሳቱ ምንም ነገር እንዳያስቀድሙ የቅዱስ ሲፕሪአኑስ ቃል ጠቅሰው፣ የሐዋርያዊ ተልእኮአቸው መሪ ኮከብ ማንነት ማእከል ያደርጉ ዘንድ በማሳሰብ የተፈጸመው ግኑኝነት የቤተ ክርስትያን ውህደት እና አንድነት እና ቤተሰብአዊ መግለጫ መሆኑ አብራርተዋል።

አዲሶቹን ሊቃነ ጳጳሳት በተልእኳቸው እግዚአብሔር እንዲባርካቸው እና በዚህ የተቀበሉት የእረኝነት ሐዋርያዊ ኃላፊነት እና እግዚአብሔር አምኖ ላስረከባቸው ማኅበረ ክርስትያንን ለመምራት በሚሰጡት አገልግሎት በፍቅር በተስፋ በጸና ሕይወት እንዲመሩ ሃብታም በሆነው እምነት ይተጉ ዘንድ እግዚአብሔር እንዲደግፋቸው ጸልየው። እናንተ ከቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ጋር ለሚኖራቸው ህብረት ምልክት የሆነው የቅዱስ ጴጥሮስ ቃለ ተአምኖ አክሚም የተቀበላቸውሁ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ደስተኞች የእምነት መስካርያን እና የቤተ ክርስትያን ልጆች እንደ ቤተ ሰብ በአንድ ጥላ ሥር ለማሰባሰብ ለሚሻው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ታማኞች እንዲሆኑ የተቀበሉት የቅዱስ ጲጥሮስ ቃለ ተአምኖ አክሚም ጥልቅ ትርጉምን ገልጠው አክለውም የእግዚአብሔር ሕዝብ ከሚመራው ከቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ጋር በእምነት እና በፍቅር የተመራ ውህደት እንዳላችሁ የሚገልጥ እንደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልበ ፈቃድ እረኞች እንዲሆኑ ከሐዋርያዊ መንበር ትሥሥር ያላችሁ መሆናቸው የሚገልጥ ነው ብለዋል።

በመጨረሻም ለብፁዓን ሊቀነ ጳጳሳት በመንፈሳዊ ቅርበት በመሆን በሐዋርያዊ ተልእኮአቸው ለመደገፍ ዕለት በዕለት በጸሎት እንደሚያስቧቸው በማረጋገጥ ለክርስቶስ ያላቸውሁ ፍቅር በመኖር ከርእሱ በፊት ማንም ሳታስቀድሙ ሐዋርያዊ አገልግሎታቸውን እንዲፈጽሙ በማሳሰብ የሰጡት መሪ ቃል እንዳጠቃለሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.