2011-06-29 15:11:28

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ፦ ለሚላኖ አዲስ ሊቀ ጳጳስ ሰየሙ


የሚላኖ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ዲዮኒጂ ተታማንዚ በእድሜ መግፋት ምክንያት ሐዋርያዊ ሓላፊነቱ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እጅ ለማስረከብ ያቀረቡት ትያቄ ቅዱስ አባታችን ብፁዕ አወንታዊ ምላሽ በመስጠት የቨነዚያ ፓትሪያርክ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ስኮላ የሚላኖ ሊቀ ጳጳስ እንዲሆኑ መሾማቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ሲያመለክት፣ የዚህ ተልእኮ መግለጫ የሆነው፣ RealAudioMP3 የቅዱስ ጴጥሮስ ቃለ ተአምኖ ምልክት አክሚም በቅዱሳን ጴጥሮስ ወጳውሎስ ዓመታዊ በዓል ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ እጅ ከተኖረላቸው ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ውስጥ አንዱ መሆናቸውም የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ብፁዕ ካርዲናል ስኮላ ከቅዱስ አባታችን የተረከቡት ሐዋርያዊ ኃላፊነት በተአዝዞ በመቀበል የፍቅር ምልክት አድርገው እንደተቀበሉት የተሰማቸውን ጥልቅ ስሜት በመግለጥ ምንም’ኳ የቅዱስ ማርቆስ መሬት የሆነቸውን ቨነዚያን ለቀው ወደ ሚላኖ በመዛወርም ከሕዝቡ እና ከሰበካው የሚለዩ ሆነው እንደ ማንኛውም ሰው ሲለይ ልቡ በኃዘን የሚነካ ቢሆንም ቅሉ፣ በቅዱስ አባታችን የተሰጣቸው አዲስ ኃላፊነት የፍቅር ምልክት መሆኑ ገልጠዋል።

ለሚላኖ ሰበካ ባስተላለፉት በመጀመሪያቱ መልእክታቸውም በትህትና እና በእምነት በዚህች የቅዱስ አምብሮዚዮ ከተማ ተዋህደው ለመኖር የሁሉም ምእመናን እና ውሉደ ክህነት ጸሎት እና ድጋፍ እንዳይላቸው አደራ ሲሉ በእድሜ መግፋት ምክንያት ከሚላኖ ሰበካ የሊቀ ጳጳስነት ሓዋርያዊ ኃላፊነት የሚሰናበቱት ብፁዕ ካርዲናል ተታማንዚ ለሚላኖ ምእመናን እና ውሉደ ክህነት ባስተላለፉት የምስጋና መልእክት፣ የሚላኖ ሰበካ የሓዋርያዊ እረኝነት ቃለ ተአምኖ ለብፅዕ ካርዲናል ስኮላ በማስተላለፋቸውም እጅግ ደስተኛ መሆናቸው እንዳመለከቱ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ብፁዕ ካርዲና አንጀሎ ስኮላ በኮሞ ክልል በምትገኘው በማልግራተ ከተማ የዛሬ 70 ዓመት በፊት እ.ኤ.አ. ህዳር 7 ቀን በሚላኖ ሰበካ ክልል መወለዳቸው እና ገና በወጣትነት ዕድሜአቸው በካቶሊክ ተግባር ማኅበር ሥር በመታቀፍ በመቀጠልም የመንበረ ጥብበ ተማሪ በነበሩበት ወቅትም በሚላኖ የመናብርተ ጥበብ ካቶሊክ ወጣት ተማሪዎች ማኅበር ሊቀ መንበር በመሆን እንዳገለገሉ ሲገለጥ፣ በሚላኖ ካቶሊክ መንበረ ጥበብ የፍልስፍና ሊቅነት ያስመሰከሩ፣ በ 29 ዓመት እድሜአቸው እ.ኤ.አ. በ 1970 ዓ.ም. በሚላኖ ሰበካ ማዕርገ ክህነት የተቀበሉ መሆናቸው ከታሪክ ማህድራቸው ለመረዳት ተችለዋል።

በጀርመን ፍሪቡርጎ ከተማ የቲዮሎጊያ ትምህርታቸውን አጠናቀው እዛው የቲዮሎጊያ ሊቅነት ያስመሰከሩ እና በኮሚኒዮኔ ኤ ሊበራዚዮነ - ኅብረት እና ነጻነት የካቶሊክ እንቅስቃሴ ንቁ አባል ኮሙኒዮ የተሰየመው በየወሩ የሚታተመው ዓለም አቀፍ የቲዮሎጊያ መጽሔት መሥራች አካላት አንዱ፣ ከአበይት የፍልስፍና እና የቲዮሎጊያ ሊቃውነት በዓለም አቀፍ ደረጃ የላቀ እወቅና ካላቸው እና ከነበራቸው በወቅቱ ብፁዕ ካርዲናል ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ጋር ከ ሄንሪ ደ ሉባክ ከሃንስ ኡርስ ቫን ብላታሳር ቅርብ ግኑኝነት ያደረጉ እ.ኤ.አ. በ 1982 ዓ.ም. በጳጳሳዊ ላተራነንሰ መንበረ ጥበብ በቅዱስ ዮሓንስ ዳግማዊ ተቋም የስነ ሰብእ-ቲዮሎጊያ መምህር በመሆን እንዳገለገሉም የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።

እ.ኤ.አ. በ 1991 ዓ.ም. በር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የግሮሴቶ ጳጳስ እንዲሆኑ ተሹመው፣ ሐዋርያዊው ተልእኮአቸውን ሁለተኛ ቆሮንጦስ ምዕራፍ 12 ቁጥር 9 “ጸጋዮ ይበቃሃል” በሚለው ቃል እንዲመራ በማድረግ ሲያገለግሉ እ.ኤ.አ. በ 1995 ዓ.ም. በር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ውሳኔ መሠረት የጳጳሳዊ ላተራነንሰ መንበረ ጥበብ ጠቅላይ አስተዳዳሪ ሆነው በማገልገል ላይ እያሉ፣ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 21 ቀን 2003 ዓ.ም. በር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ውሳኔ መሠረት የቨነዚያ ፓትሪያሪክ ሆነው ተሹመው በምስልምና እና በክርስትናው ሃይማኖት የግኑኝነት ድልድይ የሆነው ኦአሲስ በሚል መጠሪያ የባህል እና የምርምር ማእከል ያቋቋሙ የተለያዩ አቢይ እና ጥልቅ የቲዮሎጊያ የፍስፍና እና የስነ ሰብእ የምርምርና የጥናት መጻሕፍት የደረሱ እ.ኤ.አ. ጥቅምት ወር 2005 ዓ.ም. ቅዱስ ቁርባንን ማእከል ያደረገው የእንተ ላእለ ኵሉ ብፁዓን ጳጳሳት ዲኖዶስ ጠቅላይ መግለጫ አጠናቃሪ በመሆን እንዳገልገሉም የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.