2011-06-27 15:28:02

የር.ሊ.ጳ ጸሎተ መልአከ እግዚአብሔር አስተምህሮ (26/06/2011)

ቅዱስ ቍርባን የቤተ ክርስትያን ማእከል የወቅቱ ግለኝነት ለሚያረማምደው ባህል ማርከሻ ነው


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ትላትና እሁድ ሰኔ 26 ቀን 2011 ዓ.ም. እኩለ ቀን በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከውጭ እና ከአገር ውስጥ ከተሰበሰበው በብዙ ሺህ የሚገመቱት ምእመናን በተገኙበት ጸሎተ መልአከ እግዚአብሔር ከማሳረጋቸው ቀደም በማድረግ እንደተለመደው ባቀረቡት አስተምህሮ፣ እ.ኤ.አ ባለፈው ሓሙስ ሰኔ 23 ቀን 2011 ዓ.ም. በመላ RealAudioMP3 ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የተከበረው የቤተ ክርስትያን ማእከል የሆነው በዓለ ቅዱስ ቍርባን ዘክረው፣ በብዙ አገሮች በዓሉ እሁድ ሰኔ 26 ቀን 2011 ዓ.ም. መከበሩንም ዘክረው፣ አለ ቅዱስ ቍርባን ቤተ ክርስትያን ባልኖረች ነበር ካሉ በኋላ፣ ይህ የጌታችን ቅዱስ ሥጋ እና ደም በዘመናችን እየተዛመተ ላለው ግለኝነትን የሚያከር ሥነ ሐሳብ ማርከሻ መሆኑ ገልጠው፣ በዚህ አጋጣሚም በዕለቱ እንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን በሃምበርግ ሦስት የእምነት ሰማዕታት እና በሚላኖ ከተማ ብፅዕና የታወጀላቸው ሦስት የቤተ ክርስትያን ልጆች በማስታወስ እግዚአብሔር እነዚህ አዲስ ብፁዓን ስለ ሰጠን ልናመሰግነው ይገባል እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።

ቅዱስ ቍርባን የቤተ ክስትያን ማእከል የልብ ንዝረት መሆኑ አስረድተው፣ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ እና ደም ማለትም፦ ምሥጢረ ቅዱስ ቍርባን የላቀው እና እጅግ ውድ የሆነው ሃብት ነው። ቅዱስ ቍርባን የሰብአዊው ማኅበረ-ሰብ የውኅደት ምሥጢር መሆኑ ገልጠው እግዚአብሔር ወደ ዓለም፣ ዓለም ወደ እግዚአብሔር የሚያደርስ ነው ብለዋል።

በዚህ የምእራቡ ኅብረተሰብ የተነከረበት እና ወደ ሌላው የዓለማችን ክፍል በመዛመት ላይ ያላው የግለኝነት ባህል እየተስፋፋ ባለበት ዘመን፣ ቅዱስ ቍርባን በአማኝ አዕምሮ፣ ቀልብ እና ልብ ውስጥ የሚሠራ የኅብረት እና የውህደት የአገልግሎት የመተሳሰብ እና ተካፍሎ የመኖር ሥነ አመክንዮ በጠቅላላ ወንጌላዊ ሥነ አምክንዮ የሚያስፋፋ የዚህ ግለኝነት ለሚለው ባህል ማርከሻ ነው።

ቀደምት ክርስትያኖች በእየሩሳሌም በዚህ ወንጌላዊ ሥነ አመክንዮ ለሚመራው የእኗኗር ሥልት አብነት እርሱም አንድ ልብ እና አንድ አሳብ የእኔ የማይባልበት ሁሉ ነገር የጋራ ለእያንዳንዱ እነደ አስፈላጊነት የሚታደልበት በወንድማማችነት መንፈስ የተካነ ሕይወት አብነት መሆናቸው ዘክረው፣ የዚህ የአኗኗር ሥልት ምንጭ ቅዱስ ቁርባን መሆኑም ገልጠው፣ ቤተ ክርስትያን ባለፉት ዘመናት እና በአሁኑ ወቅት ምንም’ኳ የሰው ልጅ ኢፍጹምነት እና ስህተቶች የሚታይበት ቢሆንም ቅሉ፣ ቅዱስ ቍርባን አሁንም የውህደት የአንድነት ኃይል ነው። በፈላጭ ቆራጭ፣ አምባገነን ሥርዓተ መንግሥት ሠፍኖባቸው በነበሩት አገሮች ሕዝበ እግዚአብሔር አንድነቱን እና ውኅደቱን በሰንበት የሥርዓተ ቅዳሴ ማዕድ ዙሪያ ያረጋገጥ እንደነበር በማስታወስ፣ በአሁኑ ወቅት የግለኝነት ባህል የሚወልደው የሐሰት ነጻነት ሥነ ሐሳብ፣ እጅግ አደገኛ ነው። ስለዚህ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋ እና ደም ጋር የሚጸናው ውህደት ለቀልብ ለፈቃድ ከሚገኘው ፈውስ እውነትን እና የጋራ ጥቅም የማፍቀር ፍላጎት ያጎናጽፍፈናል ብለዋል።

በመጨረሻም ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ “ቅድስት ድንግል ማርያም የቅዱስ ቍርባን ሴት በማለት” ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናት የሰጡት ጥልቅ ሥያሜ አስታውሰው፣ ሕይወታችን የዚህች ቅድስት እናት አብነት በመከተል ቅዱስ ቍርባናዊ ሕይወት እናድርገው ለእዚአብሔር እና ለሌሎች ክፍት፣ ክፍትን በፍቅር ኃይል አማካኝነት ወደ መልካምነት የሚለውጥ፣ አንድነት ውህደት እና ወንድማማችነት የሚያነቃቃ ይሆን ዘንድ ጸልየው፣ ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር ደግመው እንዳበቁ፣ በዕለቱ እንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን ብፅዕና ያወጀችላቸው የቤተ ክርስትያን ልጆች አስታውሰው፣ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ለሚፈጸመው ሐዋርያዊ አገልግሎት እና ግብረ ሠናይ አመርቂ እንዲሆን በጸሎት እና በምጽዋት ደገፋቸውን ለሚያቀርቡት ሁሉ በማመስገን፣ ቀጥለውም በፓላንድ የቭሎችሎወክ ሰበካ የተመሠረተበት 600 ኛው ዓመት ክብረ በዓል ዘክረው፣ የቅዱሳን አበው እምነት ተቀብሎ እና በመኖር በመመሥከር ዕለት በዕለት ክርስቶስ የሚኖር ሕይወት በማበረታታት ሓዋርያዊ ቡራኬ በመስጠት መልካም እሁድ ተመኝተው ሁሉንም ወደ መጡበት ሸኝተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.