2011-06-15 15:36:59

ዓለም አቀፍ የአቢያተ ክርስትያን ጉባኤ


በደቡባዊ ሱዳን ክልል በሱዳን መንግሥት ወታደሮች እና በቀድሞ የሱዳን የነጻነት ግንባር አባላት በካከል የተጀመረው ግጭት ከሶስት መቶ ሺሕ በላይ የሚገመተው የክልሉ ነዋሪ ሕዝብ ለከፍ አደጋ እያጋለጠ መሆኑ ሲገለጥ RealAudioMP3 ፣ ዓለም አቀፍ የአቢያተ ክርስትያን ምክር ቤት ጠቅላይ ዋና ጸሐፊ መጋቤ ኦላቭ ፍይክሰ ትቫይት የተቀጣጠለው ግጭት ተወግዶ በክልሉ ሰላም እንዲረጋገጥ ጥሪ በማቅረብ፣ የዚህ ዓይነቱ ውጥረት በክልሉ በሰላማዊ መንገድ የተረጋገጠው እ.ኤ.አ. ሓምሌ 9 ቀን 2011 ዓ.ም. 54ኛው የአፍሪቃ አገር በመሆን ይፋዊ እውቅና የሚያገኘው የደቡብ ሱዳን ነጻነት ለአደጋ ሊያጋልጥ የሚችል እምቅ ኃይል ያለው እንደሚመስል በማብራራት፣ በክልሉ ሰላም እንዲረጋገጥ የክልሉ ሕዝብ እና አቢያተ ክርስትያን በመተባበር ያላሰለሰ ጥረት ማድረጋቸውንም መጋቤ ትቫይት እንደገለጡ ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ የተሰየመው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ በትላትናው ኅትመቱ በማብራራት፣ በሱዳን በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል የሚካሄደው የጋራው ውይይት የሚከታተለው ጉባኤ በዓለም አቀፍ የአቢያተ ክርስትያን ምክር ቤት ተደግፎ በሱዳን ያለው ሁኔታ በተለያዩ የዓለም አቀፍ መድረኮች እንዲታወቅ ከማድረግ አልፎ ሰላም እንዲረጋገጥ አቢይ አስተዋጽኦ እንዳበረከተም ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ በማስታወስ፣ የዚህ ጉባኤ ተባባሪ ሊቀ መንበር መጋቤ ኤበርሃርድ ሂትዝለር የደቡብ ሱዳን ሰላማዊ ሕዝብ ሕይወት እና ደህንነት ዋስትና እንዲያገኝ ለመላ ዓለም መሪዎች ጥሪ በማቅረብ የሚታየው ውጥረት የሰሜን ሱዳን መረጋገት እና የደቡብ ሱዳን መጪው ሉአላዊነት ለአደጋ የሚያጋልጥ ሊሆን እንደሚችል በማሳሰብ በክልሉ ሰላም እንዲረጋገጥ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ከመቼውም በመለጠ አበክሮ እንዲንቀሳቀስ ጥሪ እንዳቀረቡ ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ አክሎ አስገንዝበዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.