2011-06-08 15:50:25

ዓለም አቀፍ የውህደት አቢያተ ክርስትያን ምክር ቤት መልእክት


እ.ኤ.አ. ሰኔ 12 ቀን 2011 ዓ.ም. ለሚከበረው በዓለ ጰራቅሊጦስ ምክንያት ዓለም አቀፍ የውህደት አቢያተ ክርስትያን ምክር ቤት በዓለ ጰራቅሊጥዕስ ለእያንዳንዱ አቢያተ ክርስትያን ማኅበረሰብ ለእያንዳዱ አማኝ ክርስትናው በቅዱስ ቁርባናዊ RealAudioMP3 መንፈስ እና በቃለ ውዳሴ እርሱም እግዚአብሔርን በሚያወድስ መንፈስ እንዲኖረው የሚያበቃው ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ይስጠን በሚል ጥልቅ ጸሎት የተመራ መልእክት ማስተላለፉ ሲገለጥ፣ ይህ በዚህ ዓለም አቀፍ የውህደት አቢያተ ክርስትያን ምክር ቤት ድረ ገጽ አማካኝነት የተሰራጨው መልእክት የተለያዩ አቢያተ ክርስትያን የበላይ መንፈሳውያን መሪዎች ፊርማ የሠፈረበት መሆኑም ከድረ ገጹ ለማረጋገጥ ተችለዋል።

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስትያንን እንዲያድስ እና ክርስትያን እና አቢያተ ክርስትያን በምንኖርበት የተለያየ ችግር እና ስቃይ እየተፈራረቀበት ባለው ዓለም እውነተኛ የቃል እና የሕይወት መስካሪያን እንዲሆኑ ብርታት እና ጽናት የሚሰጣቸው መንፍስህ ላክ፣ በክርስቶስ በሙላት የተፈጸመው የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ ብዙውን ጊዜ የሰውል ልጅ ጠንቅቆ ለመረዳት የሚያዳግተው ቢሆንም ቅሉ በሁሉም ሥፍራ እና ጊዜ ለዓለም ሕዝብ እንዲሰበክ እና ለሁሉም ይገለጥም ዘንድ የመንፈስ መለኮታዊ ኃይል በልኡካነ ወንጌል በምእመና ዘንድ ላክ የሚል ጥልቅ የልመና ጸሎት የሰፈረበት ሲሆን በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተኖረ በደቀ መዛሙርት የቀጠለው ዓለም እና የሰውን ልጅ የሚለውጠው ወንጌል በሁሉም ሥፍራ እና ጊዜ እንዲሰበክ ብርታት ሁነን የሚል ጸሎት ጭምር የሰፈረበት መሆኑ ከድረ ገጹ ለመረዳት ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.