2011-06-08 15:47:36

በተባበሩት መንግሥታት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ያነቃቃው ስብሰባ


እ.ኤ.አ. ከነሐሴ 16 እስከ ነሐሴ 21 ቀን 2011 ዓ.ም. በማድሪድ ከተማ የሚካሄደው 26 ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ምክንያት በማድረግ በተባበሩት መንግሥታት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ቢሮ ስለ ወጣት ጉዳይ እና በየዓመቱ RealAudioMP3 በእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን አዘጋጅነት የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ዋና ዓላማ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚሰጠው አስተዋጽእ ለማሳወቅ ያቀደ ዓውደ ጥናት እ.ኤ.አ. ባለፈው ሰኔ 3 ቀን 2011 ዓ.ም. 500 ወጣቶች በማሳተፈ መካሄዱ ፊደስ የዜና አገልግሎት በማሳወቅ፣ እነዚህ ወጣቶች በተካሄደው ዓወደ ጥናት በዓለም አቀፍ ደረጃ እጅግ አንገብጋቢ የሆኑት በተለይ ደግሞ የሕይወት ባህል ለማስፋፋት እና ለማነቃቃት እርሱም ሕይወት ከመጸነስ እስከ ባህርያዊ ሞት መከበር በተሰኘ እሰይታ ላይ ያተኮረ የላቀው በማንም ሊጣስ የማይገባው የሕይወት ክብሩ በምንኖርበት ዓለም ዋስትና እንዲያገኝ በሚል ጥሪ ላይ በማተኮር ጥያቄዎች በማቅረብ ውይይት ማካሄዳቸው ያመለከተው የዜናው አገልግሎት አክሎ የተካሄደው ዓውደ ጥናት ከተለያዩ አገሮች የተወጣጡ የባህል የሥነ ጥበብ አካላት ማሳተፉንም አስታውቀዋል።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ብፁዕ አቡነ ፍራንሲስ አሲዚ ቹሊካት በተካሄደው ዓወደ ጥናት ባሰሙት ንግግር የሕይወት ባህል የሚያነቃቃ፣ ሕይወት በሁሉም ደረጃ ከመጸነስ እስከ ባህርያዊ ሞት እንዲከበር የሚለው የላቀው እሰይታ ማእከል ያደረገ ይኸንን እሰይታ የሚያነቃቃ እና መሠረታዊ አመክንዮው የሚያስተጋባ የጥናት ጽሑፍ፣ መዝሙር ቅብ እና ንድፍ አማካኝነት ከ 16 እስከ 30 ዓመት ዕድሜ ያላቸው የሚያሳትፍ የባህል ውድድር እንደሚካሄድ ፊደስ የዜና አገልግሎት ያሰራጨው የዜና ምንጭ ይጠቁማል።







All the contents on this site are copyrighted ©.