2011-06-06 14:36:07

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ እውነተኛ ደስታ የሚደረሰው/የሚጨበጠው በክርስቶስ ፍቅር ብቻ ነው


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በዚህ የሁለት ቀናት የክሮአዚያው ጉብኝታቸው ወቅት በታሪካዊው ጆሲፕ ዠላቺች አደባባይ ከ50 ሺህ በላይ ለሚገምተው ለአገሪቱ ወጣት የኅብረተሰብ ክፍል መሪ ቃል ሲሰጡ፣ ወጣቱ አታላይ እና በአቋራጭ በቀላል መንገድ ስኬታማ ለመሆን ትችላለህ በሚለው በእውነት ላይ ካልጸናው ባህል እራሱን እንዲጠብቅ እና ከዚህ አታላይ ባህል የላቀውን እውነት በእግዚአብሔር ፍቅር RealAudioMP3 ላይ ሳይጠራጠር እንዲሻ በማሳሰብ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእጁ ይዞ እንዲመራችሁ ፍቀዱለት በጉዞአችሁ እንደ ጓደኛ እና በጎዞአችሁ የሚሸኛችሁ ክርስቶስ ከእናንተ ጓር እንዲጓዝ ፍቀዱለት፣ አያሳፍራችሁም እታያታልላችሁም የእዚአብሔርን ፍቅር ቀርባችሁ እንድታውቁት ያደርጋችኋል፣ የሁሉም መልካም የሆነውን የሚሻ በፍቅሩ በፈጠረን እና ባዳነን እግዚአብሔር አርአያ እና አምሳያ የተፈጠርን ስለ ሆን እውነተኛው ደስታ ከእርሱ ጋር ከሚመሠረተው ጥብቅ ወዳጅነት ከእርሱ ጋር ከሚደረገው ጉዞ ብቻ ነው የሚረጋገጠው። ስለዚህ ዕለታዊው ኑሮ በሚጋርጥብን ችግር እና ድካም ሳንበገር እውነተኛው የሕይወት ትርጉም እለት በእለት የሃሰት ባህል በመቃወም ኑሩ መስክሩም እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን የሚያሳፍር የሚያታልል የሚያደናግር ሳይሆን ከእርሱ ጋር መጓዝ ጽናትን እና መሥዋዕት የሚጠይቅ መሆኑ ሳይደብቅ እና በግልጽ በማሳወቅ ባመለከተው መንገድ መጓዝ መኖር የደስታ ምክንያት ነው። ስለዚህ ችግር እና መከራም ቢፈራረቅብን ይኸንን እውነት መኖር ይበጃል። ስለዚህ መሠረተ ቢስ ከሆነው የማንነት መለያ የሆነው ጥልቅ እና ውስጣዊው መሆን ወደ ጎን በማድረግ ነጠፉን ብቻ ከሚያጎላው ባህል ተቆጠቡ፣ ይኸንን ባህል ተቃውሙት፣ ተስፋህን በሚበነው የዓለም ሃብት ላይ ገንባ ከሚለው የእውነት ምንጭ ውህ ከሆነው ክርስቶስ ወደ ሚመራን ከነገር ባሻገር ወደ ሆነው ክብር እንዳንጓዝ ከሚያሰናክለው ባህል ታቅባችሁ እና በመቃወም ወደ እግዚአብሔር ታላቅነት ትመሩ ዘንድ ፍቀዱ ካሉ በኋላ የሰው ልጅ ሕይወት ፍቅር ወደ ሆነው እግዚአብሔር የሚጓዝ ነው በማለት ሁሉንም ወጣት አንድ በአንድ በአባታዊ ፍቅራቸው በመመልከት ሐዋርያዊ ቡራኬ በመስጠት እንደሸኙዋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።







All the contents on this site are copyrighted ©.