2011-06-05 17:25:54

የቅዱስ አባትችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ ሐዋርያዊ ዑደት በክሮአጽያ


ቅዱስነታቸው በክሮአጽያ ላይ የሁለት ቀናት ሐዋርያዊ ዑደት ለማከናወን ከሐዋርያዊ መንበራቸው ትናንት ቅዳሜ በሮም ሰዓት አቆጣጠር ከቀትር በፊት 9፡30 ከሊዮናርዶ ዳ ቪንቺ ዓለም ዓቀፍ የአየር ማረፍያ ተነስተው ከአንድ ሰዓት ተኩል በረራ በዛጋብርያ ከተማ ፕለሶ ዓለም አቀፍ የአየር ማረፍያ ደርሰዋል።
ከሊዮናርዶ ዳ ቪንቺ ዓለም ዓቀፍ የአየር ማረፍያ ሲነሱ የቅድስት መንበር ብፁዓን ካርዲናላትና ጳጳሳት እንዲሁም በክሮአጽያ የቅድስት መንበር እንደራሴ ሸኝተዋቸዋል። ቅዱስነታቸው ከሮም ከተነሱ ለኢጣልያ ሪፓብሊክ ፕርሲዳንት ጆርጅዮ ናፖሊታኖ እና ለኢጣልያ ሕዝብ የመልካም ምኞት ተለግራም ከአይሮፕላኑ ኣስተላልፈዋል። የተለግራሙ ይዘት ቅዱስነታቸው በክሮአጽያ ተከብሮ ለሚለው ሃገራዊ የቤተሰብ ክብረበዓል እንዲሳተፉ በክሮአጽያ የሁለት ቀናት ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማድረግ በሚሄዱበት ግዜ ሰላምታቸውና ቡራኬአቸው ለመላክ መልካም ፍቃዳቸውን የሚገልጥ ነበር። ቅዱስነታቸው በአሊታልያ የበረራ ኩባንያ ካደረጉት የአንድ ሰዓት ተኩል ጉዞ ብኋላ በዛጋብርያ ከተማ ፕለሶ ዓለም አቀፍ የአየር ማረፍያ ደርሰዋል። በዓለም አቀፍ የአየር ማረፍያ በሚገኙ የከፍተኛ እንግሶች መቀበያ ክፍል በደረሱ ግዜም ከክሮአጽያ መንግሥት ሕዝብና ምእመናን ከፍተኛ አቀባበል ሲደረግላቸው፤ ቅድስነታቸው ለተደረገላቸው አቀባበል ልባዊ ምስጋና በማቅረብ ‘በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በክሮአጽያ አገራችሁ ንግደት ለመፈጸም መጥቼአለሁ፤ ለመላው የክሮአጽያ ሕዝብ ለክሮአጽያ ፕረሲደንትና ባለሥልጣናት፤ እንዲሁም ለክሮአጽያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ጳጳሳት ካህናት ደናግልና ምእመናን ሰላምታየን አቀርባለሁ።’ በማለት በተደረገላቸው አቀባበል የተሰማቸው ደስታና ሰላምታቸውን ገልጠዋል። ከእርሳቸው በፊት ነፍሰኄር ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ አገሪቱን ለሦስት ግዜ በመጎበኘታቸው በቅድስት መንበርና በክሮአጽያ ያለው ግኑኝነት የላቀ መሆኑንም አመልክተዋል። በታሪክ መለስ ብለን የተመለከትን እንደሆነ ደግሞ የክሮአጽያና የመንበረ ቅዱስ ጴጥሮስ መልካም ግኑኝነት በ13ኛው ክፍለ ዘመን የተጀመረ መሆኑንም ኣስታውሰዋል።
ቅዱስነታቸው ዛጋብርያ እንደገቡ በቀጥታ የክሮአጽያ መራሄ መንግስት ፕረሲዳንት ኢቮ ዮሲፖቪች ጽሕፈት ቤት ተጉዘው የክብር ጉብኝት ኣድርገዋል።
ከቀትር በኋላ ደግሞ በሀገሪቱ ብሔራዊ ትያትር ተጉዘው ከሀግሪቱ የሃይማኖት ሲቪል እና ባህል ማኅበረ ሰቦች ተወካዮች ጋር ተገናኝተው ቃለ ምዕዳን ሰጥተዋል፤ በማምሻውም በዛጋብርያ አደባባይ ከሀገሪቱ ወጣቶች ጋር በመገናኘት በጋራ ጸሎተ ሰርክ ኣሳርገዋል።
ዛሬ እሁድ ዕለት ሰነ አምስት ቀን ደግሞ በጥዋቱ ዛጋብርያ ከተማ ላይ በሚገኘው ትልቅ የፈረስ መጋለብያ ሥርዓተ ቅዳሴ ኣሳርገዋል። ዛሬ በክሮአጽያ የካቶሊካውያን ብሔራዊ የቤተ ሰብ ቀን ታስቦ እና ተከብሮ በመዋሉ ቅዱስነታቸው የብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ መል እክት በመጥቀስ ክርስትያናዊ ቤተ ሰብ በቤተ ክርስትያን የስብከተ ወንጌል ተል እኮ ሕያውና ኃላፊነታዊ ሚና መጫወት እንዳለባቸው በማመልከት ይህንን የሚጠየቁበት ምክንያት ደግሞ ክርስትያናዊ ቤተ ሰብ የሕይወትና የፍቅር ማኅበር እንዲሁም የእምነት ቀዳማዊ መስኖ በመሆን በማገልገሉ አሁንም ለአዲስ ስብከተ ወንጌል በተለያዩ መስኮች እንደሚያገለግል አመልክተዋል።
እኩለ ቀን ላይ የንግሥተ ሰማያት ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት በሰጡት ጉባኤ አስተምህሮ ቅዱስነታቸው ክሮአጽያ ላይ በሚያደጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ከአገሪቱ ቤተ ክርስትያን ጋር የእምነት ሥጦታ ልውውጥ ለማድረግ መሆኑን በመግለጥ ወንድሞቹን በእምነት ለማጽናት እንደመጡም ገልጠዋል፡ ይህ የቅዱስ ጴጥሮስ እምነትና ተመኩሮ በተለያዩ የሕይወት ገጠመኞች ማለትም ደስ በሚያሰኙና አሳዛኝ ገጠመኞች በልጽጋና አሸብርቃ እንደገና ለጴጥሮስ ተከታይ እንደምትመልስ በመግለጥ፤ ሁሉንም የክሮአጽያ ቤተሰቦች ለቅድስት ድንግል ማርያም አማጥነዋል።
ከቀትር በኋላ ቅድስነታቸው ዛጋብርያ ላይ የብፁዕ ስተፊናክ መቃብር ወደ ሚገኝበት
የክሮአጽያ ዜጋ የሆኑ ብፁዕ ስተፊናክ በዘመነ ዮሴፍ ቲቶ የኮሚኒዝም አምባገነናዊ አገዛዝ ሰፍኖ በነበረበት ግዜ ለሃይማኖት ነጻነት ሕይወታቸው አሳልፈው የሰጡ ሰማዕት መሆናቸው ይታወቃል።ከጸሎተ ሰርክ በኋላ የዛጋብርያ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ቦዛኒችን ጐብኝተዋል፤
አሁን ይህ ዜና በሚተላለፍበት ግዜ ወደ ሐዋርያዊ መንበራቸው ለመመለስ ዛጋብርያ ሀገራት አቀፍ አውሮፕላን ማረፍያ እየተግጓዙ ናቸው።








All the contents on this site are copyrighted ©.