2011-06-03 13:53:52

ብፁዕ አቡነ ቨሊዮ፦ ኤውሮጳ እና ስደተኞች


ስደተኛው ከተስተናገደበት አገር እና ባህል ጋር ተዋውቆ እና ተግባብቶ በኅብረት ለመኖር እንዲችል የእርስ በእርስ ውይይት እና ሕንጸት ማነቃቃት ወሳኝ መሆኑ በቡዳፐስት የኤውሮጳ ኅብረት ተረኛ ሊቀ መንበር የሃንጋሪ መንግሥት የተለያዩ ሃይማኖቶች የእርስ በእርስ ውይይት በሚል ርእሰ ጉዳይ ባነቃቃው ጉባኤ በመሳተፍ ንግግር ያሰሙት የስደተኞች እና የተጓዦች ሐዋርያዊ RealAudioMP3 ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አንቶኒዮ ማሪያ ቨሊዮ በማብራራ፣ ስደተኛው በተስተናገደበት አገር በሰላም ተዋህዶ ለመኖር እንዲችል በሚደረገው ጥረት የሁሉም ሃይማኖቶች ሚና ማእከል ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ሲጠቁም፣ በዚህ ዛሬ በተጠናቀቀው ጉባኤ የኤውሮጳ አገሮች የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ፐተር ኤርዶ በመሳተፍ ንግግር ማሰማታቸውም ከቅድስት መንበር የተላለፈ መግለጫ ያስታውቃል።

የባህል ልዩነት እና ኅብረ-ባህል በቅድሚያ ሃብት መሆኑ ብፁዕ አቡነ ቨሊዮ በመግለጥ፣ ስደተኛው ከተስተናገደበት አገር እና ኅብረተሰብ ጋር አንድነት ፈጥሮ እንዲኖር እራሱን እንዲያሳውቅ እድል ማግኘት እንዳለበት እና አስተናጋጁ አገር እና ሕዝብ ገዛ እራሱ ማስተዋወቅ አለበት፣ ስለዚህ ይህ እቅድ እግብ ለማድረስ የተለያዩ ሁሉም ሃይማኖቶች አቢይ ኃላፊነት እንዳለባቸው ውይይት እና ሕንጸት በተሰኙት ሁለት መንገዶች አማካኝነት እግብር ላይ መዋል አለበት እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።

ሰላም የተካነው ተጨባጭ ማኅበራዊ ኑሮ ለማረጋገጥ ውይይት እና ሕንጸት ተቀዳሚ መሣሪያዎች ናቸው። መስተንግዶ፣ ትብብር፣ መከባበር ፍርሃት እና ግደ የለሽነትን በመቃወም ስደተኛው ገዛ እራሱን ባዶ አድርጎ ያስተናገደው አገር ባህል እንዲቀበል እና በዚህ ባህል እንዲዋጥ የሚያስገድድ የስደተኛው ባህል እና ታሪክ የሚደልዝ የስደተኛው የማስተናገጃ መርሃ ግብር ጨርሶ መወገድ አለበት። የሚበጀው እና ማህበራዊ ሰላም ለማረጋገጥ እና እውነተኛው ውህደት እንዲኖር የሚያግዘው አለ ምንም ቅድመ ፍርድ መተዋወቅ፣ መቀራረብ እራስን ገልጦ ሌላውን አውቆ በመተዋወቅ ለመኖር የሚያግዝ ባህል ነው ካሉ በኋላ፣ ስደተኛው ለአንድ አገር እና ሕዝብ ባህል እና ሃይማኖት ብሎም ፖለቲካ እና ኤኮኖሚ ባጠቃላይ ለማንነት መለያ ዛቻ አይደለም፣ ስለዚህ ይህ እውነት በአስተናጋጅ አገር እንዲሰርጽ ሆሉም ሃይማኖቶች አቢይ ሚና መጫወት ይኖርባቸዋል። ኤውሮጳ ክርስትያናዊ የባህል መሠረትዋ በማግለል ተመሳስሎ ለመኖር በሚለው አመለካከት ተመርታ ስደተኛው ለማስተናገድ የምታደርገው ጥረት ጎጂ ነው። ስለዚህ እውነተኛው መለያህን በማሳወቅ እራስህን በትክክል ማስተዋወቅ ይኽ ደግሞ ተስተናጋጁ እራሱን በትክክል ለማስተዋወቅ ያነቃቃዋል፣ በማለት ሁሉም የኤውሮጳ መንግሥታት ይኸንን መንገድ የተከተለ ስደተኛው የማስተናገድ መርሃ ግብር ይወጥኑ ዘንድ ቤተ ክርስትያን አደራ እንደምትል ገልጠው ያሰሙት ንግግር እንዳጠቃለሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።








All the contents on this site are copyrighted ©.