2011-06-03 13:52:19

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ የሰው ልጅ ከክርስቶስ ጋር ለዘልዓለም ወደ እግዚአብሔር ቤት ገባ

በዓለ ዕርገት


የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ትላንትና በሃገረ ቫቲካን በዓለ ዕርገት ማክበርዋ ሲገለጥ፣ የሊጡርጊያው ባህረ ሐሳብ በዓሉ በማሸጋገር እ.ኤ.አ. ሰኔ 5 ቀን 2011 ዓ.ም. በተለያዩ አቢያተ ክርስትያን እንዲከበር የሚያዝ ሲሆን፣ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት የሰው ልጅ ወደ ሰማያዊ ቤት ተጓዥ መሆኑ ካለው ግንዛቤ ጋር የሚቀራረብ የክርስትና የእምነት ምሥጢር መሆኑ RealAudioMP3 ባለፉት ዓመታት በዓሉን ምክንያት በማድረግ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በሰጡት አስተምህሮ በተደጋጋሚ ያሰመሩበት ሥልጣናዊ ትምህርት መሆኑ የቅድስት መንበር መግለጫ በማስታወስ፣ እ.ኤ.አ. ግንቦት 24 ቀን 2009 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በካሲኖ መሥዋዕት ቅዳሴ አሳርገው ባሰሙት ስብከት፣ ወደ ሰማይ ባረገው ክርስቶስ አማካኝነት የሰው ልጅ ተሰምቶ እና ታይቶ በማይታወቀው አዲስ ሥልት አማካኝነት በእግዚአብሔር ውስጥ የገባበት እና ለእግዚአብሔር እጅግ ቅርብ በመሆን በእርሱ ውስጥ በማያዳግም ሁኔታ ዘለዓለማዊ ሥፍራውን እንዳገኘ የሚያረጋገጥ መሆኑ ገልጠው፣ ሰማያዊ ቤት ሲባል ከከዋክብት በላይ የሚገኝ ቦታ ማለት ሳይሆን፣ እግዚአብሔር እና ሰው ለዘለዓለም በማይነጣጠል ደረጃ አንድነት የተገለጸበት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊ ሰው እግዚአብሔር እና ሰው በሙላት እና ለዘለዓለም የሰውን ልጅ የተቀበለበት ማለት መሆኑ እራሱ ገልጦልናል ሲሉ ማስተማራቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ዓለም የመጣበት ምክንያት እንደ አንድ ፈላስፋ እና አንደ አንድ የጥበብ መምህር በሐሳብ ደረጃ ሳይሆን እውነተኛው እረኛ በጎቹን ወደ እውነተኛው ጒረኖ በትክክል ለመምራት በተጨባጭ የሰውን ልጅ ወደ እግዚአብሔር ዳግም ለመመለስ ወይንም ለማድረስ ነው። ይህ ወደ ሰማያዊ ቤት የሚደረገው ጉዞ ወይንም ጸአት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅድሚያ እና በገዛ እራሱ በመኖሩ ሙሉ በሙሉ ለእኛ ሲል የተጋፈጠው ሂደት ነው። ለእኛ ሲል ነው ከሰማየ ሰማያት የወረደው፣ ካለ ኃጢኣት በስተቀረ ሰብአዊነትን በሙላት በመኖር ጥቅጥቅ እና እልም ወደአለው ጨለማ በመዝለቅ ተዋርዶ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ በሰው ልጅ የተኖረው ከእግዝአብሔር ርቆ የመኖር ገጠመኝ ከኖረ በኋላ ከሙታን የተነሳው ለእኛ ሲል ነው ወደ ሰማየ ሰማያት ያረገው ለእኛ ሲል ነው በማለት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እ.ኤ.አ. ግንቦት 4 ቀን 2008 ዓ.ም. እኩለ ቀን ጸሎተ ንግሥተ ሰማያት መረተው ከመድገማቸው በፊት ባቀረቡት አስተምህሮ መግለጣቸው የቅድስት መንበር መግለጫ በማስታወስ ጠቅሶታል።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የደቀ መዛሙርቱ ዓይኖች ወደ ላይ እንዲያቀኑ እንዲያተኮሩ በመማረክ በምድራዊው የሕይወት ዘመን በመልካም መንገድ እንዴት መጓዝ እንዳለባቸው አስተምሮአቸዋል። እርሱ ወደ ሰማይ ቢወጣውም በሰው ልጅ ታሪክ ዘንድ ኅያው ሆኖ የሚኖር ለእያንዳንዳችን ቅርብ ሆኖ ክርስትያናዊ ጎዞአችንን የሚመራ፣ በእምነታቸው ለስደት እና ለመከራ ለሚዳረጉት ቅርብ ሆኖ አብሮአቸው በመጓዝ መጠለያ የሚሆን፣ በተለያየ ምክንያት ከህብረተሰብ ተገለው ለሚኖሩ ሰዎች ልብ ቅርብ በመሆን የሕይወት መብት ለሚነፈጋቸው ቅርብ ሆኖ የሚደግፍ ነው በማለት እ.ኤ.አ. ግንቦት 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ጸሎተ ንግሥተ ሰማይ ከማሳረጋቸው ቀደም በማድረግ ባቀረቡት አስተምህሮ እንደገለጡ የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።

ቤተ ክርስትያን የተወለደችው እና የምትኖረው የጠፋ ወይንም የተሰወረ ክርስቶስ ስላለ እርሱን በመተካት በእርሱ የተተወው ቦታ ለማሟላት ለመተካት አይደለም፣ እንዳውም የእርሷ ኅላዌ እና ተልእኮ መሠረት የማይደሳስ ባይሆንም በእርሱ ዘለዓለማዊ እና ቀጣይ የሆነው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ድንቅ ሥራውን የሚገለጥበት እና የሚሠራበት ኅላዌ ነው። በሌላው ረገድ ቤተ ክርስትያን የተሰወረው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲመለስ የሚያዘጋጅ ሙያ የሚፈጸምባት ሳይሆን፣ የምትኖረው እና የምታገለግለው ክብር እና ሞጎስ የተሞላው ኅላዌው በመካከላችን እንደሚገኝ በታሪካዊ ሂደት እና በተጨባጭ ኅላዌነት እንደምታውጅ እ.ኤ.አ. ግንቦት 24 ቀን 2009 ዓ.ም. በካሲኖ መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው ባሰሙት ስብከት ማብራራታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ያስታውሳል።







All the contents on this site are copyrighted ©.