2011-06-01 14:14:47

መንፈሳዊ/የተቀደሰ መዝሙር እድገት


ጳጳሳዊ የተቀደሰ ሙዚቃ ተቋም የተመሠረተበት 100ኛውን ዓመት ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የካቶሊክ ትምህርት ጉዳይ ለሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ዘኖን ግሮቾለውስኪ ባስተላለፉት መልእክት፣ ቤተ ክርስትያን እውነተኛ የሊጡርጊያ ባለቤት በመሆንዋ ምክንያት የተቀደሱ መዝሙሮች ወይንም ማሕሌት ምእመን ወይንም በቅዳሴ ሥርዓት RealAudioMP3 የሚሳተፍ ጉባኤ ለማነቃቃት እና በሊጡርጊያ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን የሚያነቃቃ የመዝሙር ጸሎት የተሰኘው ጥልቅ ትርጉሙን ክብሩን እና ውበቱን የሚያጎናጽፍ መሆን አለበት እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

በአሁኑ ወቅት ፖፕ የተሰኘው የሙዚቃ ሥልት የሊጡርጊያ ሥርዓት እየበከለ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ የተለያዩ ከሙዚቃ ጋር የተወሃሃደ የትያትር ድርሰት እና ር.ሊ.ጳ. ፒዮስ አሥረኛ አንድ መንፈሳዊ መዝሙር ወይንም የተቀደሰው ሙዚቃ በተመለከተ የሚቀርበው የሙዚቃ የጽሑፍ ምልክት ጭምር ከሊጡርጊያ መለኮታዊው ትርጉም ጋር የሚዛመድ መሆን እንዳለበት ማሳሰባቸው ቅዱስ አባታችን ባስተላለፉት መልእክት በማስታወስ፣ ር.ሊ.ጳ. ፒዮስ አሥረኛ እ.ኤ.አ. በ 1911 ዓ.ም. ከፍተኛ የመንፈሳዊ ሙዚቃ ትምህርት ቤት በማቋቋም እና ይኽ የሙዚቃው ትምህርት ቤት በር.ሊ.ጳ. ፒዮስ አሥራ አንደኛ ከ20 ዓመት በኋላ ጳጳሳዊ የመንፈሳዊ ሙዚቃ ተቋም ተብሎ እንደተሰየመም ዘክረው፣ ስለዚህ በቤተ ክርስትያን የሊጡርጊያ አገልግሎት ለቤተ ክርስትያን ሥልጣናዊ ትምህርት እና ትውፊት ታማኝ የሆነ ቅዱስ መዝሙር ለማቅረብ እንዲቻል፣ የዚህ ሙዚቃ ደራሲያን ዘማርያም እና መሪዎች በከፍተኛ ደረጃ የሚያዘጋጁበት ጳጳሳዊ የሙዚቅ ተቋም መሆኑ ገልጠዋል።

ቅዱስ አባታችን ከቤተ ክርስትያን የሊጡርጊያ አገልግሎት ጋር ተያይዘው የሚቀርቡት መንፍሳውያን መዝሙሮች የቤተ ክርስትያን ሥልጣናዊ ትምህርት ቀጣይነቱ የሚረጋገጥበት መሆኑ በማረጋገጥ ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ እንዲሁም ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ መንፈሳዊ መዝሙር መሠረታዊው የቤተ ክርስትያን ባህላዊው መመዘኛ በመከተል መዝሙር ጸሎት ክብር እና ውበት የተሰኘውን ጥልቅ ትርጉሙ በማጎናጸፍ ከሊጡርጊያ “ሥርዓት እና ምልክቶች” ጋር የሚጣጣም መሆን እንዳለበት ካሳሰቡ በኋላ፣ የሊጡጊያ ባለ ቤት ቤተ ክርስትያን ነች ስለዚህ በቅዳሴ ሥርዓት ግለ ሰብ ወይን አንድ ጉብኤ የሚያቀርበው ማለት ሳይሆን በቤተ ክርስትያን ዘንድ የእግዚአብሔር ተግባር መግለጫ ነው። ስለዚህ የተቀደሰ ታሪክ ያለው ለኅዳሴ ያቀና ባጠቃላይ እውነተኛው የቤተ ክርስትያን ባህል እና ተገቢ እና ትክክለኛውን ኅዳሴ በማጣመር የሚጓዝ የተቀደሰ መዝሙር ነው። ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ አበው የቤተ ክርስትያን ባህል ተጨባጭ እና ኅያው ሆኖ በውስጡ መሠረታዊ መመሪያዎችን በመከተል ለእድገት እና ለኅዳሴ ያቀና መሆኑ የሰጡት ማብራሪያ በመጥቀስ ያስተላለፉት መልእክት እንዳጠቃለሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.