2011-05-30 14:15:38

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ


በሳምንት ማገባደጃ የቅድስት መንበር የዜና ኅትመት ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የሚያቀርቡት ርእሰ ዓንቀጽ በመቀጠትል፣ ትላትና ካንድ ሳምነት በኋላ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በክሮአዚያ የሚፈጽሙት ሐዋርያዊ ጉብኝት ርእስ ሥር ቅዱስነታቸው እ.ኤ.አ. ከሰነ 4 እና ሰኔ 5 ቀን 2011 ዓ.ም. በዚያች ብፁዕ ካርዲናል እያሉ በተለያየ ወቅት RealAudioMP3 የጎበኝዋት አገር ይላሉ አባ ሎምባርዲ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ከተሾሙ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ የሚፈጽሙት ሐዋርያዊ ጉብኝት መሆኑ አስምረውበታል።

ይህ ሐዋርያዊ ጉብኝት በቅድስት መንበር እና በክሮአዚያ መካከል ያለው ጽኑ ግኑኝነት እና የጠበቀው ወዳጅነት የሚመሰክር ሲሆን፣ ክሮአዚያ በቀውጢው የፈላጭ ቆራዥ ሥርዓት ወቅት ክርስትያናዊ እምነቷን አቅባ በስቃይ እና በመከራ ተፈትና የመሰከረውችው ክርስትያናዊ እምነቷ በአሁኑ ወቅት በዓለማችን እየተስፋፋ ባለው በተዛማጅ ባህል የተጠቃ እንደሚመስል እና በተለይ ደግሞ ይህ ማመን እና አለ ማመን ሁሉም ያው ነው፣ እሴቶች ብሎ ነገር የለም የሚለው አደገኛው ባህል ቤተሰብ ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል ላይ አቢይ ችግር እያስከተለ መሆኑ አባ ሎምባርዲ በመጥቀስ፣ ስለዚህ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በክሮአዚያው ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው ከካቶሊክ ቤተሰብ ጋር እንዲሁም ከወጣት የኅብረተሰብ ክፍል ጋር በመገናኘት ይኽ ከክርስቶስ ጋር በሚል መሪ ቃል የሚሸኝ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸ ክርስቶሳዊው ሕይወት ማእከል ያደረገ አስተምህሮ እንደሚያቅረቡ በርእሰ አንቀጽ ማብራሪያ ተሰጥቶበታል።

በክርስቶስ የተመሠረተቸው ቤተ ክርስትያን የቤተሰብ አንድነት እና ተልእኮ በመደገፍ በወጣት የኅብረትሰብ ክፍል ተስፋ እንደምታነቃቃ አባ ሎምባርዲ በርእሰ ዓንቀጹ ገልጠው፣ ክሮአዚያ ጥልቅ እና መሠረት ያለው ክርስትያናዊ ባህልዋ የሥነ ምርምር ሊቅ ነፍሰ ኄር እየሱሳዊ ካህን ሩገሮ ቦሾቪች፣ ብፁዕ ኢቫን ማርዝ፣ እረኛ እና ሰማዕት ካርዲናል ብፁዕ ስተፊናክ እና ሌሎች ቅዱሳን ልጆችዋ አማካኝነት የተሰጠው ምስክርነት በመከተል ከክርስቶስ ጋር እና ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በመሆን መጪው የአገሪቱ ሕይወት በእምነት በመመልከት እንድትራመድ የሚያነቃቃት ሐዋርያዊ ጉብኝት ነው በማለት ርእሰ አንቀጹን ደምድመዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.