2011-05-30 14:14:10

የር.ሊ.ጳ የጸሎተ ንግሥተ ሰማያት አስተምህሮ (29/05/2011)

ብሥራተ ወንጌል ሕይወት እንዲያብብ ያደርጋል፣ የቤተ ክርስትያን ጥሪ አስፍሆተ ወንጌል ነው


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ትላትና በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባብ ከተሰበሰበው ከኢጣሊያ እና ከውጭ አገር ከተወጣው በብዙ ሺሕ ከሚቆጠረው ምእመን ጋር በመሆን የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት መርተው ከማሳረጋቸው በፊት ባቀረቡት አስተምህሮ፣ በበረሃማው እና ደረቅ መሬት የሚዘንበው ዝናብ ያረንጓዴው ሃብት ዳግም ሕይወት እንዲዘራ እንደሚያድረግ ሁሉ RealAudioMP3 ወንጌል በሚሰበክበት ቦታ ሕይወት ዳግም እንዲያብብ ያደርጋል ካሉ በኋላ፣ ቅዱስ ካርሎ ቦሮመዮ፣ እናቴ ብፅዕት ተረዛ ዘ ካልኩታ እና አቢይ ልኡከ ወንጌል የሰየሙዋቸው ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እና ሌሎች ቅዱሳን እና ብፁዓን ብሩህ ምሥክርነት እና አገልግሎት የቤተ ክርስትያን ጥሪ አስፍሆተ ወንጌል መሆኑ የሚያረጋገጥ ነው ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በግብረ ሐዋርያት የሳምራዊው ዲያቆን ፊሊጶስ ተልእኮ ላይ በማተኮር፣ ፊሊጶስ እና ሌሎች ሐዋርያት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳደረገው ሁሉ በፍልስጥኤም መንደሮች መልካም ዜናን አበሥረዋል፣ ድንቅ ሥራዎችንም ፈጽመዋል፣ በእነርሱ አማካኝነት ይኸንን ሁሉ የፈጸመው ግን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

መልካም ዝናብ የደረቀውን መሬት እንደሚያረሰርስ እና ዳግም የአረንጓዴው ሃብት ዳግም ተጨባጭ እንደሚያደርግ ሁሉ ስብከተ ወንጌል ሕይወት ያስከትላል። ባለፉት ዘመናት እና አሁንም ቢሆን ወንጌል አቢይ የፈውስ ሃይል እንዳለው፣ ይኽ ደግሞ ልክ የአንድ የወንዝ መስኖ ለሕዝብ አቢይ ጠቀሜታ እንዳለው ወንጌልም ልክ እንደዚሁ ነው ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው በታሪክ ያለፉት አበይት ቅዱሳኖች በተለይ ደግሞ ቅዱስ ካሮሎ ቦሮመዮ በሚላኖ ዓቢይ የወረርሽኝ በሽታ በተከሰተበት ወቅት እናተ ብፁዕት ተረዛ በካልኩታ የክርስቶስን ወንጌል በማበሠር ጥልቅ ደስታ በሰዎች ሕይወት ዘንድ እንዲያብብ እንዳደረጉ ሁሉ ተስፋን እና ሰለምን አስተጋብተዋል።

በአሁኑ ወቅት አበይት ኃያላን እና ባለ ሥልጣናኖች ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጥቅማቸውን ሲያሳድዱ፣ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልኡካን ግን ክርስቶስን ማበሠር ተቀዳሚ ዓላማቸው መሆኑ በመረዳት፣ ክርስቶስ ብቸኛው እውነተኛው ነጻነት እና ዘለዓለማዊ ሕይወት (የሚሰጥ) መሆኑ ታምነው እርሱን ያበሥራሉ።

የቤተ ክርስትያን ተልእኮ ወይንም ጥሪ አስፍሆተ ወንጌል መሆኑም ሲያስረዱ በወንጌላዊው ሕያው የውኃ ምንጭ ገና ያልተነኩ ሁሉ አዲስ የእውነተኛው ሕይወት ምንጭ እንደሚያሻቸው እና ክርስትያናዊ ባህል መሠረት ያላቸው ዘመን ባለፈ ቁጥር በደከመባቸው ጥንታውያን የክርስትያን አገሮች በእምነት ዘንድ ያለው ውበት እና ደስታ ዳግም እንዲቀዳጁ የሚያደርግ የእስፍሆተ ወንጌል ተልእኮ መሆኑ ሲያስገነዝቡ፣ አቢይ ልኡከ ወንጌል በማለት ሰይመው ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊን ዘክረው፣ በቤተ ክርስትያን ይኸንን ጥሪ ዳግም ያነቃቁ እና ይኸንን የቤተ ክርስትያን ተልእኮ በማርያም አማላጅነት ሥር የሚረጋገጥ መሆኑ በቃል እና በሕይወት በማስተማር መሥክረዋል፣ የክርስቶስ እናት ቅድስት ድንግል ማርያም ዘወትር በየትም ሥፍራ ሰዎች የእግዚአብሔር ልጆች ከመሆናቸው ካለው የእምነት እርግጠኛነት የሚገኙት እና ዓለም ይኽ ደስታ የሚኖርበት መሆኑ ለሚያረጋገጠው የአስፍሆተ ወንጌል ተልእኮ ደጋፊ እና ብርታት ነች፣ ካሉ በኋላ ምእመናንን ሁሉ በተለያዩ ቋንቋዎች ሰላምታ ካቀረቡ በኋላ ጸሎተ መልአከ እግዚአብሔር አሣርገው ለሁሉም መልካም እሁድ ተመኝተው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው ሁሉም የአስፍሆተ ወንጌል ተልእኮ ተካፋይ እንዲሆን በማሳሰብ ወደ መጡበት አሰናብተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.