2011-05-16 16:59:40

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ተጨማሪ የምትቀበላቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ለመተርጉምና ለማቅረብ እንቅስቃሴ ጀመረች፡፡


በይፋ በታወጀው በዚሁ እንቅስቃሴ ብፁዓን የኢትዮጵያ ካቶሊካውያን ጳጳሳት በአንድነት አባታዊ ቡራኬያቸውን የሰጡ ሲሆን ይፋ ሆኖ ሥራው እንደጀመረ ሚያዚያ 30 ቀን 2003 ዓ. ም. በልደታማርያም ካቴድራል ቤተክርስቲያን በበፁዕ አቡነ ብርሃነየሱስ ሊቀጳጳሳት ታውጇል፡፡

እነዚህ ተጨማሪ የኢትዮጵያን ካቶሊካዊ ቤተክርስቲያን የምትቀበላቸውን መጽሐፍ በተለያየ ጊዜያት የቤተክርስቲያን ሊቃውንት የተረጐሟቸው ቢሆንም የትርጉም ሥራ እጅግ ጥንቃቄ ሚያስፈልገው በመሆኑ በይፋ ሥራው እንዲጀምር ቤተክርስቲያን መፍቀድዋን በመግለጽ ለዚሁ ተግባር ከፍተኛ እገዛ የያደርገውን የኢትዮጰያ መጽሐፍ ቅዱስ ማህበርን አመስግነዋል፡፡

የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማህበር ሰብሰቢ የሆኑት አቶ ማርቆስ ገ/ማርያም በአደረጉት ንግግር ማህበሩ ሶስቱን ዓቢያት ክርስቲያን በማቀራረብ እያደረገ ያለውን ታላቅ አገልግሎት በመግለጽ ከሁሉ በላይ የሆነውን ይሀን ታላቅ ሀብታችን እናም ተገልግለንበት ሌሎችን እንዲጠቀሙ የክርስቲያናዊ የውዴታ ግዴታ እንዳለብን በመግለጽ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመንም እንደሌሎች እህት አብያተ ክርስቲያናት በሚችለው አቅም ለመጽሐሕፍ ቅዱስ መስፋፋት ለሁሉ ወገን እንዲርስ በሚችለው አቅም ሁሉ አስተባባሪውን የመጽሐፍ ቅዱስ ማህበር በሚችለው አቅም ሁሉ ድጋፉን እንዲያደርግ ተማጥነዋል፡፡

የማህበሩ ጸሐፊ አቶ ይልማ

ስለመጽሐፍ ቅዱስ ማህበር ዓላማና ተልዕኮ

በሀገራችን 81 ቋንቋ መነገሩን ከነዚህ ቋንቋዎች ሙሉ መጽሐፈ ቅዱስ በ5 ቋንቋ ብቻ መተርጐማቸው

የትርጉም ሥራ ቀላል እንደመሆኑና ስለሚወስደው ጊዜ

በሃገራችን መጽሐፍ ቅዱስን ለማሳተም የሕትመት መሣሪያ አለመኖር

መጽሐፍ ቅዱስን ለማሰራጨት ደግሞ ሌላው ከባድ ተግባር መሆኑን

በተመለከተ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጠዋል በመጨረሻም መጽሐፍ ቅዱስ ለሕይወታችን ታላቅ ትርጉም እንደሰጠን ሁሉ ሌሎችመ የዚሁ ዕድል ተጠቃሚ እንደሆኑ ባደረግን ቁጥር የተሰጠንን ስጦት ባግባቡ መጠቀማችን ገለጻ አድርገዋል፡፡

በመጨሻም ብፁዕ አቡነ ብርናነየሱስ ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካዊያን የመጸሐፍ ቅዱስ ማህበር እያከናወነ ያለውን አገልግሎት በማመስገን ለዚሁ ዓላማ በግንባር የቆሙትን ሁሉ በቤተክርስቲያኒቱ ስም አመስግነዋል፡፡

ከማንኛው መጽሐፍ በላይ ለተረሱትና ማንም ቦታ ለማይሰጣቸው ወገኖች የመጽሐፍ ቅዱስ ማህበር ቅድሚያ በመስጠት በቋንቋቸው በመተርጐም እያደረገ ያለውን አገልግሎት በገጠራማው የአገራችን ክፍል ለማየት መቻላቸውን ምስክርነት ሰጠዋል፡፡

በድጋሚም ለኢትዮጰያ ካቶሊከዊት ቤተክርስቲያን በመጽሐፍ ቅዱስ መስፋፋት ከማህበሩ ጋር በጋራ ለመሥራት ሁልጊዜ ዝግጁ መሆናዋን ገልጽዋል፡፡

የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ጽ/ቤት

ማህበራዊና ህዝብ ግንኙነት ማስተባበሪያ








All the contents on this site are copyrighted ©.