2011-05-13 14:44:03

የቁስጥንጥንያ የውህደት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስያን ፓትርያርክ መልእክት


ዓለም አቀፍ የአቢያተ ክርስትያን ጠቅላይ ምክር ቤት እ.ኤ.አ. ከግንቦት 17 ቀን እስከ ግንቦት 22 ቀን 2011 ዓ.ም. በጃማይካ ለሚያካሂደው ዓለም አቀፍ ዓመታዊ ጠቅላይ ጉባኤ ከወዲሁ በማስመልከት፣ የቁስጥንጥንያ የውህደት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ በርጠለሚዮስ አንደኛ ባስተላለፉት አዋዲ መልእክት ሰላም RealAudioMP3 ለመሻት የሚደረገው ጥረጥ ግቡን እንዲመታ ሁሉም ሰላም ለመሻት የሚከተለው መንገድ ዳግም በማጤን ሥር ነቀላዊ ኅዳሴ ይሰጥበት ዘንድ ማሳሰባቸው ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

የቁስጥንጥንያ የውህደት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ በርጠለሚዮስ አንደኛ በዚህ ባስተላለፉት ዓዋዲ መልእክት ሁሉም ካለ ምንም ቅድመ ሁኔታ አመጽ እና ጦርነት በመቃወም ለማስወገድ እንዲተጋ በማሳሰብ፣ ውጥረት በሰዎች እና በአገሮች መካከል ሊኖር የሚችል እና አይቀሬ ቢሆንም፣ ለጦርነት መንስኤ ግን ሊሆን አይችልም። ጦርነት ወይም አመጽ አይቅሬ የሚባል ጉዳይ ወይንም ምርጫ አይደለም። ስለዚህ ሰላም ለመሻት የሚደረገው ጥረት አቢይ ተጋርጦ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት የሰላም ጥያቄ ከመቼም በበለጠ አንገብጋቢ ጥያቄ መሆኑ ብፁዕ ወቅዱስ በርጠለሚዮስ አንደኛ ባስተላለፉት አዋዲ መልእክት በመጥቀስ፣ ስለዚህ ሰላም ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት የሚከተለ ምርጫ እና መንገድ ዳግም ተከልሶ መለወጥ እና መታደስ አለበት። ሰላም መለወጥን ትጋት እንዲሁም ጽናት እና ብርታት የሚጠይቅ ዓላማ ነው እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

አቢያተ ክርስትያን ሰላም ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት አቢይ ኃላፊነት እንዳለባቸውም ብፁዕ ወቅዱስ በርጠለሚዮስ አንደኛ በማስታወስ፣ ይህ እጅግ የተወሳሰበው እና በሰላም እጦት ለሚሰቃየው አመጽ በተከናነበው ዓለም፣ አቢያተ ክርስትያን ሰላም ለማረጋገጥ እና የሰላም መሣሪያ ሆነው መገኘት እንዳለባቸው እና ይኽ ደግሞ የአቢያተ ክርስትያን ባህርይ ነው ካሉ በኋላ በእግዚአብሔር አርአያ እና አምሳያ የተፈጠረው የሰው ልጅ ሰላም ለማረጋገጥ የሚከተለው መንግድ ይኸንን መሆናዊ አርአያነት እና አምሳያነት ኃላፊነት ላይ የጸና መሆኑ በማስገንዘብ፣ ስለዚህ ሰላም መሻት እና መገንባት የአቢያተ ክርስትያን ተቀዳሚ አላማዎች ውስጥ አንዱ እና ተልእኮዋም ጭምር ነው። እስካሁን ድረስ ሰላም ለማረጋገጥ የምንከተለው መንገድ አጥጋቢ ምላሽ ያላሰጠ ሆኖ በመገኘቱ ምክንያት፣ ክርስትያን ሁሉ መለስ ብሎ የኅሊና ምርመራ ብሔርተኝነት ወገናዊነት የመሳሰሉት ባጠቃላይ በሰው ዘር መካከል ልዩነት የሚያስከትሉ የአጋጣሚ ክፍለ መሆናዊ ሰላም ለመሻት ለምንከተለው መንገድ መሠረት ከማድረጉ ምርጫ መቆጠብ አለብን በማለት ሰላም አለ ፍትሕ ፈጽሞ አይረጋገጥም አለ ፍትሕ ሰላም አይኖርም በማለት ያስተላለፉት አዋዲ መልእክት እንዳጠናቀቁ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.