2011-04-26 12:23:05

ር.ሊ.ጳ ጸሎተ ንግሥተ ሰማያት ኣስተምህሮ (25.04.2011)


ጌታ በእውነት ተነሣ ሃሌሉያ የጌታ ትንሣኤ የእኛ ሁኔታ መታደሱን ያመለክታል። ክርስቶስ በኃጢኣታችን ምክንያት የተወሰብንን ሞት ኣሸነፈ፤ ዘለዓለማዊ ሕይወት ሰጠን፤ የቤተ ክርትያን ሕይወትና የክርስትያኖች ሕይወትም በጌታ ትንሣኤ ላይ ይመሠረታል፡ በዛሬው ንባብ ‘ስለ ክርስቶስ ትንሣኤ አስቀድሞ አይቶ፥ ነፍሱ በሲኦል እንዳልቀረች ሥጋውም መበስበስን እንዳላየ ተናገረ። ይህን ኢየሱስን እግዚአብሔር አስነሣው ለዚህም ነገር እኛ ሁላችን ምስክሮች ነን፤ ስለዚህ በእግዚአብሔር ቀኝ ከፍ ከፍ ብሎና የመንፈስ ቅዱስን የተስፋ ቃል ከአብ ተቀብሎ ይህን እናንተ አሁን የምታዩትንና የምትሰሙትን አፈሰሰው።’ የሚለውን ቅ.ጴጥሮስ ያኔ በተወለደችው ኣዲስትዋ ቤተ ክርስትያን ባደረገው ስብከተ ወንጌል በግብረ ሐዋርያት 2፡32/33 እናነባለን። የትንሣኤ ክርስቶስ ምልክቶች ኣንዱ ክርስትያን የሆነ ሁሉ በትንሣኤ ግዜ ሰላምታ ሲለዋወጥ የሚያደርገው ውይይት በጥንታዊ ሥር ዓተ ኣምልኮ እናገኘዋለን፤ ይህም ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ፤ እውነትም ተነሣ የሚለው ነው; ይህ ኣባባል የእምነ ምስክርነትና የሕይወት ግዴታ መሆኑን በወንጌለ ማቴዎስ 28.9/10 ‘እነሆም፥ ኢየሱስ አገኛቸውና። ደስ ይበላችሁ አላቸው። እነርሱም ቀርበው እግሩን ይዘው ሰገዱለት። በዚያን ጊዜ ኢየሱስ። አትፍሩ፤ ሄዳችሁ ወደ ገሊላ እንዲሄዱ ለወንድሞቼ ተናገሩ፥ በዚያም ያዩኛል አላቸው።’ በሚለው ጥቅስ ኢየሱስ ‘ሰላም ከእናንተ ጋር ይሁን’ ባላቸው ግዜ እነርሱም ቀርበው የተወጋውን እግሩን ኣይተው ክብር በሰጡበት ግዜ የተገለጠ ነው። የእግዚዐብሔር ኣገለጋይ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ኢቫንጀሊ ኑንስያንዲ በተሰኘው ብ1975 በጻፉት ሐዋርያዊ ምዕዳናቸው. ‘በዚሁ በጌታ ንግግር ቤተ ክርስትያን በኣጠቃላይ የስብከተ ወንጌል ተል እኮን ተቀበለች፤ በዚህም የእያንዳንዱ ክርስትያን ተግባር ለሁላችን እጅግ ኣስፈላጊ ሥራ ነው፤ ቤተ ክርስትያን ይህንን ተል እኮ ስትቀበል ምንም እንደማታሳይ መጋረጃና ሁሉም ኣጉልታ የምታሳይ መስትዋት በመሆን የኢየሱስ በመህከልዋ መኖርና ለሁሉም በእኩል የሚመለከትና ዘወትር መሀከላችን መኖሩን ያመለክታል፤ ቤተ ክርስትያን ይህንን እስከ መጨረሻ ታኖረዋለች አርሱ ዳግም እስኪመጣ ድረስም ትጠብቀዋለች; ያሉት ይንን ነው።

ጌታን በምን ልናገኘው እንችላለን እንዴትስ የእርሱ እውነተና ምሥክሮች ለመሆን ብቃት እናገኛለን፧ ለዚህ መልስ የሚሆን የቶሪኖ ቅዱስ ማሲሞ ይሰጠናል፤ ‘መድኃኔ ዓለም ጌታ ኢየሱስን ለማግኘት የሚሻ ሁሉ መጀመርያ በእምነት በእግዚኣብሔር ኣብ ቀኝ ሊያኖረው ያስፈልጋል ከዛ በኋላ ልቡን በሰማይ በማኖር ሊከተለው ይገባል’ ይለናል። በሌላ ኣነጋገር ማንኛውም ምእመን ልቡና ኅሊናውን ዘወትር ከሙታን ተለይቶ የተነሣ ክርስቶስ ባለበት ቦታ ማኖር ኣለበት። በሥርዓተ ኣምልኮኣችን ዲያቆን ‘በሰማይ የሀሉ ልበክሙ፤ ልባችሁ በሰማይ ይኑር ካለ ብኋላ ‘ብነ ኅበ እግዚኣብሔር ኣምላክነ ኣቡነ ዘበሰማያት ኣዎ ልባችን በሰማይ ካለው እግዚኣብሔር ኣባታችን ጋር ነው’ እንደ ማለት ነው። ይህም ማለት ቅዱስነታቸው እንዳሉት ከሙታን ተለይቶ የተነሣ ክርስቶስ ያለበት ማለት ነው። ለምስጋናና ለኣምልኮ በምናቀርበው ጸሎት እግዚዐብሔር የሰው ልጅን ያገኛል ማለት ነው፤ ሮማዊው ትምህርተ ንባበ መለኮታዊ ሊቅ ሮማኖ ጓርዲኒ እንደሚለው ‘ለእግዚኣብሔር የምናቀርበው ስግደትና ኣምልኮ ማንኛ ተግባር ሳይሆን የሰው ልጅ የመጨርሻ ፍላጎት የማንነቱ ትርጉምና ህልውና የሚመለከት ነው፤ የሰው ልጅ በስግደትና በኣምልኮ በእግዚኣብሔር ፊት ንጹሕ ያልተደባለወና ቅዱስ የሆነውን ነገር ለይቶ ያውቃል;’ ይለናል። በዚህም ማንነታችንና የሕይወት ትርጉምን ለማወቀ የምንችለው በጸሎት ወደ እግዚኣብሔር ለመቅረብ ስንችል ብቻ ነው፤ በዚህም ዕለታዊ የሕይወት ጉዞኣችን ከሙታን ተለይቶ በተነሣው ክርስቶስ ብርሃን ሊበራ ይችላል።

ውድ ጓደኞቼ ዛሬ በምሥራቅና በም ዕራብ የምትገኝ ቤተ ክርስትያን ወንጌላዊው ማርቆስን ታከብራለች፤ ወንጌላዊው ማርቆስ የዘለዓለማዊው ቃል ኣብሳሪና የክርስቶስ ትምህርት ጸሓሪ ነው፤ ቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ በቅርቡ ጉብኝት ለማድረግ የማቅደው የቨነስያ ጠባቂ ቅዱስም ነው፤ ካሉ በኋላ ኣሁን በታማኝነትና በደስታ ከሙታን ተለይቶ የተነሣው ክርስቶስ ለእያንዳንዳችን የሰጠውን ተል እኮ በብቃት ለመፈጸም እንድንችል ትረዳን ዘንድ እመቤታችን ድንግል ማርያምን እንማጠን በማለት የንግሥተ ሰማያት ጸሎት ኣሳርገዋል።

ከንግሥተ ሰማያት ጸሎት ብኋላ ለሁላቸውም መልካም ትንሣኤ ተምኝተው በተለያዩ ቋንቋዎች ኣመስግነው ሐዋርያዊ ቡራኬ ችረዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.