2011-03-21 14:22:09

ጃፓን፣ የአቶም ጨረር መጠን መጨመር ያሳደረው ሥጋት


በሰሜናዊ ምሥራቅ የጃፓን ክልል በተከሰተው ርእደ መሬት እና ድህረ ርእደ መሬት በሚታየው የመሬት መናጋት አደጋ፣ አሁንም እየቀጠለ ሲሆን፣ በተከስተው ርእደ መሬት ወደ 20 ሺሕ የሚጠጋው የአገሪቱ ሕዝብ RealAudioMP3 ሰለባ መሆኑ ይነገራል።

በተከሰተው ርእደ መሬት ሳቢያ በፉኩሺማ የሚገኘው የአቶሚክ ኃይል ማመንጫ ማእከል ላይ የደረሰው የፍንዳታ አደጋ ሳቢያ በክልሉ የተረጨው የአቶም ጨረር መጠን እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ እና የቶኪዮ ቀጥሎም የጉንማ የመጠጥ ውኃ በዚሁ በአቶም ጨረር መበከሉ ሲገለጥ መንግሥት የብከላው መጠን በጣም ዝቅተኛ እና ለሕይወት አደገኛ እንዳልሆነ ይናገራል። በርእደ መሬት ሳቢያ የተጠቁት የአቶሚክ ኃይል ምንጭ ማእከል የሚያስከትለው አደጋ ለመግታት በተለይ ደግሞ የፉኩሽማ የአቶም ኃይል ማመንጫ ለማቀዝቀዝ የሚደረገው ጥረት እየቀጠለ ነው። በክልሉ ያለው የአቶሚክ ጨረር መጠን እጅግ ከፍ ያለ በመሆኑ የአቶሚክ ኃይል ማመንጫ ማእከል ለማቀዝቀዝ የሚደረገው ጥረት አንዳንድ መሰናክ ቢያጋጥመው ውጤተ እያስገኘ መሆኑ ይንገራል። በፉኩሺማ የኑክሊያር ኃይል ማመንጫ ማእከል የጥገናውን ተልእኮ እያከናወኑ ያሉት 50 ባለ ሙያዎች ከነዚህም ውስጥ ስድስቱ ለአቶም ጨረር በክፈተኛ ደረጃ የተጋለጡ ቢሆንም ቅሉ የኑክሊያር ኃይል ምንጭ የሚያገለግሉ አበይት ጋኖችን የሚረጩት የአቶም ጨረር ለማክሸፍ የሚያደርጉት ጥረት ውጤት እያስገኘ መሆኑ ይነገራል።








All the contents on this site are copyrighted ©.