2011-03-21 14:20:27

የቅድስት መንበር ርዕሰ ዓንቀጽ


ሁሌ በሳምንት ማገባደጃ የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ጉዳይ ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የሚቀርበው ርዕሰ ዓንቀጽ በመቀጠል፣ ትላትና ርእደ መሬት እና የኑክሊያር ኃይል ማመንጫ ማእከል በሚል ርእስ ሥር፣ በጃፓን የተከሰተው ርእደ መሬት እና ርእደ ምድረ ባህር በሰው እና በንብረት ላይ ያስከተለው ጉዳት እንዲሁም በኑክሊያር የኃይል ማመንጫ ማእከል RealAudioMP3 ላይ ያስከተለው አቢይ ጉዳት ለእያንዳንዳን የኅሊና ጥያቄ ነው በማለት፣ የዛሬ ስድስት ዓመት በፊት የሕንድ ውቅያኖስ ርእደ ምድር ያስከተለው ጉዳት በማስታወስ የዚህ አይነት በመደጋገም የሚታየው የተፈጥሮ አደጋ የሚያስከትለው ጉዳት በጣም የሚያስደነግጥ መሆኑ ገልጠው፣ በእውነት በአደጋው ሳቢያ ለተጎዱት ቅርብ በመሆን ተገቢ ድጋፍ እና ትብብር ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው።

የዕደ ጥበብ እድገት የሚደነቅ ቢሆንም ቅሉ ያለው ውስንነት ምንኛ ለአደጋ እንደሚያጋልጥ ለመረዳት መቻሉንም ገልጠው፣ ይኽ ደግሞ ጃፓን ካሉዋት 50 የኑክሊያር ሃይም ማመንጫ ማእክል ውስጥ በአንዱ ላይ ርእደ መሬት ያስከተለው አደጋ ምንኛ ለዓለማችን እንዳስደነገጠ ጠቅሰው፣ የኑክሊያር ኃይል ምንጭ ለሰው ልጅ አቢይ ጥቅም አለው፣ ሆኖም ግን በዚሁ የኃይል ምንጭ ጉዳት ሲደርስ የኃይሉ ምንጭ ተመልሶ የሞጎዳው የሰውን ልጅ ነው። ስለዚህ የዕደ ጥበብ እድገት ተጠቃሚነትን እና ጠቀሜታው ያለው ኃይል በተመለከተ በጥልቀት ማስተንተን ተገቢ መሆኑ ቅዱስ አባታችን የደረሰው ጉዳት በማስመለከት ባስተላለፉት መልእክት ያሰመሩበትን ነጥብ መሆኑም ጠቅሰው፣ በጃፓን ፉኩሺማ የኑክሊያር ኃይል ማመንጫ ማእከል ከደረሰበተ አደጋ ለማላቀቅ እና በሰው እና በተፈጥሮ ላይ ሊያስከትለው የሚችለውን ጉዳት ለማገድ ብዙ የሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋ መከላከያ ኃይል አባላት ልክ በኒው ዮርክ እ.ኤ.አ. መስከረም 11 ቀን 2001 ዓ.ም. አሸባሪያን የጣሉት ያጥፍተህ ጥፋ አደጋ ለመቆጣጠር ተሰማርተው የነበሩትን በማስታወስ ሌላውን ለማዳን ሕይወት እስከ መክፈል የሚሰጡት አገልግሎት የሚደነቅ ነው ካሉ በኋላ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጅ ለማዳን እራሱን አሳልፎ እስከ መስጠት የከፈለው መሥዋዕት አብነት ያደረገ የሚሠዋ ፍቅር ምስክርነት ነው በማለት ርዕሰ ዓንቀጹን ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.