2011-03-21 14:17:55

ቅዱስ አባታችን፦ የእግዚአብሔርን ማንነት አሳውቅ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ሮማ ካሳለ ፓሎኮ ሠፈር የሚገኘው አዲስ የቅዱስ ኮርቢኒያኖ ቁምስና ባርከው እንዳጠናቀቁ ለመላ የሰፈሩ እና የአዲስ ቅዱስ ኮርቢኒያኖ ቤተ ክርስትያን ቁምስና አባላት የእግዚአብሔር ፈቃድ ለመኖር የሚሻ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መከተል ቃሉን መልብ ማስተናገድ ማዳመጥ እና በጥልቅ ማጥናትን ይጠይቃል ካሉ በኋላ ስለዚህ ለሁሉም RealAudioMP3 የእግዚአብሔር ማንነት በማሳወቅ ፍቅሩን መመስከር እንደሚያስፈልግ እና ይኽ ደግሞ ክርስትያናዊ ጥሪያቸውን ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

የእግዚአብሔር ፍቃድ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሙላት ተገልጠዋል። ስለዚህ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ለመኖር የሚፈልግ በመንፈስ ቅዱስ ድጋፍ የእግዚአብሔር ምህረት ቅድስና እና ፍቃድ በሙላት የገለጠው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካለ ምንም ቅድመ ሁኔታ መከተል ይኖርበታል። ስለዚህ ሁሉም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እና ፍቅሩን በማወቁ ሂደተ እንዲያድግን አደራ ብለው፣ በቅዱስ ቁርባን እና በቃሉ በጸሎት እና በፍቅር ሥራ እንድንገናኘው ምዕዳን አቅርበዋል።

ቅዱሳን በቅዱስ ጴጥሮስ ላይ የተመሠረተቸው እና በዚሁ ዓለት ላይ ለተገነባችው ለቤተ ክርስትያን አንድነት እና ኵላዊነት የኖሩ የቤተ ክርስትያን ኵላዊነትን የመሰከሩ ናቸው ካሉ በኋላ የሁሉም ቁምስናዎች አባላት ጥሪ ለሁሉም የእግዚአብሔር የፍቅር መልእክት ማሳወቅ መሆኑ ገልጠው፣ በቁምስናው የሳቸው መገኘት ክርስትያን ምእመናን በዚህ ተልእኮ ጸንቶ ዘወትር በእያንዳንዱ ምእመን ኅያው የሆነቸው ቤተ ክርስትያን በሁሉም እንድትታወቅ በቃል እና በሕይወት ክርስቶስን እንዲመሰክሩ ለማበረታታት ነው በማለት ገልጠው፣ ስለዚህ አዲስቷ ቁምስና የእግዚአብሔር ቃል የሚኖርባት እና የምንማርባት ሁሉም በክርስትና ጥሪው እለት በእለት እንዲያድግ የምትደገፍ ነች ሁሉም የቅድስት ቤተ ሰብ አብነት በመከተል በምሥጢረ ተክሊል በአንድ ወንድ እና ሴት ከሚጸናው ውሁደት የሚመሠረተው ቤተ ሰብ የእግዚአብሔር ፈቃድ እንዲኖር የሚደገፈበት ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።








All the contents on this site are copyrighted ©.