2011-03-09 16:02:51

ወደ እብራውያን የተጻፈው መልእክት የሚተነትን የጥናት መጽሓፍ


የጳጳሳዊ የቅዱስ መጽሓፍ ድርገት ልሒቅ ዋና ጸሓፊ በዘመናችን አሉ ከሚባሉ የሥነ ቅዱስ መጽሓፍ ሊቅ ብፁዕ ካርዲናል አልበርት ቫንሆየ የደረሱት ወደ እብራውያን የተጻፈው መልእክት የሚተነትን ጥልቅ የጥናት መጽሓፍ በአራት ቋንቋዎች ታትሞ ከትላትና በስትያ ሮማ በሚገኘው በግረጎሪያና ጳጳሳዊ መንበረ ጥበብ የጉባኤ አዳራሽ በተካሄደው ዓወደ ጥናት በይፋ ለንባብ መቅረቡ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

መጽሓፉ ለንባብ ለማቅረብ በተካሄደው ዓውደ ጥናት በመሳተፍ ንግግር RealAudioMP3 ያሰሙት በሚላኖ የቲዮሎጊያ መንበር ጥበብ መምህር የቅዱስ መጽሓፍ ሊቅ አባ ፍራንኮ ማንዚ፣ ወደ እብራውያን የተጻፈው መልእክት ነሮነ ሮማ ይገዛበት በነበረበት በ 67 – 68 ዓ.ም. የተጻፈ መልእክት መሆኑ የተረጋገጠ ቢሆን ነገር ግን ደራሲው ወይንም የመልእክቱ ጸሐፊ ማንነት ለመለየት በጣም አስቸጋሪ ቢሆንም ቅዱስ ጳውሎስ እንዳልሆነ ብቻ በትክክል ለመግለጥ የሚቻል መሆኑ በማብራራት፣ ሆኖም ግን ከጳውሎስ ጋር በመሆን በአስፍሆተ ወንጌል አገልግሎት ከተሰማሩት ልኡካን ውስጥ አንዱ መሆን አለበት። ምክንያቱም የቅዱስ ቍርባን ጉባኤ፣ የሊቃነ ካህናት የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ በእኛ እና በእግዚአብሔር መካከል የአዲስ ኪዳን አማካኝ የአይህድ እምነት ተከታዮች እና ከአረመኔነት አመለካከት የመጡ ክርስቶስን የተቀበሉ ማኅበረ ክርስትያን ሕይውት የሚገልጥ የአዲስ ኪዳን ክፍል ነው።

ብሉይ ኪዳንን በሥነ ኢየሱሳዊ ግልጸት መሠረት የሚመለከት በቅዱስ ቁርባን አማካኝነት ቀድሞ በነቢያት አፍ የተነገረው አዲስ ኪዳንን የሚተነትን መልእክት ነው። በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሥዋዕት አማካኝነት በብሉይ ኪዳን የነበረው የክህነት ምሥጢር ፍጻሜ የአዲስ ካህን አቋም የሚገልጥ ነው።

የመጽሐፉ ደራሲ ብፁዕ ካርዲናል አልበርት ቫንሆየ ወደ እብራውያን የተጻፈው መልእክት ኢየሱስ ክርስቶስ ካህን ማእከል ያደረገ፣ እርሱም ከብሉይ ክህነት የተለየ ብቻ ሳይሆን ያንን ክህነት በምልአት የገለጠ እና እፍጻሜ ያደረሰ የክርስቶስ አዲስ ካህን እርሱም የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ እፍጻሜ ያደረሰ ነው። የሰውን ልጅ ሰብአዊነት ባህርይ የለወጠ እርሱም የክርስቶስ ባህርይ በሁሉም አቅጣጫ ፍጽሙነቱ የሚያርረጋግጥ እና ይኽ ደግሞ ከገዛ እራስ ውጭ የሆነ መሥዋዕት ማቅረብ ሳይሆን ገዛ እራሱን ለእግዚአብሔር የተገባ ፍጹም መሥዋዕት በማቅረብ በቅዱስ ቍርባን አማካኝነት ሰብአዊ ባህርይን የለወጠ ያደሰ ነው። ክርስቶስ ፍጹም መሥዋዕቱም ፍጹም መሆኑ የሚገልጥ መጽሐፍ ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.