2011-03-07 16:00:30

ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሐንስ ጳውሎድ ዳግማዊ


በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ና ውሳኔ መሠረት እ.ኤ.አ. ግንቦት 1 ቀን 2011 ዓ.ም. በእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን በይፋ ቅድስትና ስለ ሚታወጅላቸው ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በማስመልከት ጆአኪን ናቫሮ ቫልስ የቫቲካን የዜና ኅትመት ክፍል ተጠሪ በመሆን ለ 20 ዓመት ያገለገሉት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ RealAudioMP3 ለመላ የሰው ልጅ ስለ እግዚአብሔር በቃል እና በሕይወት የተናገሩ ናቸው በማለት፣ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩባት እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 2 ቀን 2005 ዓ.ም. የዓለም ሕዝብ የገለጠው የሐዘን ስሜት፣ ሐዘን ሳይሆን ምንኛ አቢይ የእግዚአብሔር ሰው መሆናቸው እና ስለ እግዚአብሔር ለሰጡት ምስክርነት እውቅና የሰጠ ስሜት መሆኑ በማብራራት። በዚያኑ ወቅት የታየው ሕዝባዊ ስሜት ከዚህ ዓለም በሞት መለያታቸው ምክንያት ቢሆንም ቅሉ ግንቦት አንድ ቀን 2011 ዓ.ም. ቅድስት ቤተ ርክስትያን በይፋ ብፁዕ በምትልበት ቀን ደስታ ሆኖ በመላ ዓለም በከፍተኛ ደረጃ ደምቆ እንደሚስተጋባ ቀድሞ ያረጋገጠ ስሜት ነው ብለዋል።

ጃአኮን ናቫሮ ቫልስ ለ 20 ዓመት ከር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ጎን በመሆን የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል ተጠሪ ሆነው ያገለገሉ መሆናቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ከዚህ ዓለም በሞት እስከ ተለዩበት ሚያዝያ 2 ቀን 2005 ዓ.ም. በነበራቸው ኃላፊነት ሁሌ በቀን ሁለት ሶስት ሰዓት ከሳቸው ጋር ማለትም ከዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ጋር ያሳልፉ የነበረው ግኑኝነት ዘክረው፣ አሁን ግን በመንፈስ ካለ ምንም የሰዓት ገደብ ለእኔ ቅርብ ሆነዋል በዕለታዊ ሕይወቴ ይሸኙኝ ዘንድ በሳቸው አማካኝነት እግዚአብሔር እጸልያለሁ፣ ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማሚ ወንጌል የኖረ ሕይወት ያጎሉ፣ ወንጌልን በቃል እና በሕይወት የመሰከሩ ናቸው፣ ታላቅ የሚያሰኛቸው የኖሩት ወንጌላዊ ሕይወት ነው። ብዙ ታላቅ የሚሰኛቸው ጉዳይም አለ ሆኖም በቃለ መጠይቅ መልክ አጠር አድርጎ ለማዘርዘር ጊዜውም አይበቃል ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.