2011-03-04 16:00:12

ዓለም አቀፍ የምግብ እና የእርሻ ድርጅት


በዓለማችን የኑሮ ወደነት እጅግ ከፍ እያለ መምጣቱ ዓለም አቀፍ የምግብ እና የእርሻ ድርጅት ከሰጠው ጥናታዊ መግለጫ ለመረዳት ሲቻል፣ እ.ኤ.አ. የካቲት ወር 2011 ዓ.ም. የኑሮ ውድነት መናር በጥር ወር ከንበበረው 231 ነጥብ ጋር ሲነጻጸር RealAudioMP3 ወደ 236 ነጥብ ከፍ ብሎ መገኘቱ እና ይኽ ደግሞ የሩዝ፣ የሥጋ ምርት፣ ጥራ ጥሬ እና የስኳር አቅርቦት ላይ የተጨመረው የግዥ ዋጋ መሠረት በማድረግ የተሰጠ ጥናታዊ መግለጫ መሆኑ ለማወቅ ተችለዋል።

ዓለም አቀፍ የምግብ እና የእርሻ ድርጅት እ.ኤ.አ. ከ 1990 ዓ.ም. ካለ ማቋረጥ በየዓመቱ እያከናወነው ያለው የምግብ ምርት አቅርቦት ዋጋ ሚዛን ቁጥጥር በዓለማችን የነዳጅ ምርት ዋጋ መናር ለምግብ ምርት ዋጋ መናር መሠረታዊ ምክንያት መሆኑ በማብራራት፣ የኑሮ ውድነት በከፍተኛ ደረጃ የምርት አቅርቦት ጠያቂ አገሮች ላይ ብቻ ሳይሆን በምርት አቅራቢ አገሮች ጭምር በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚተዳዳረው የኅብረተሰብ ክፍል አቢይ ችግር መሆኑ የፋኦ መግለጫ በማረጋገጥ፣ በድኻው እና በሃብታሙ መካከል ያለው ድኽነት ለማጥበብ ብሎም ለመቅረፍ በሚደረገው ጥርት አይሎ ካልተገፋበት የኑሮው ውድነት ከፍ እያለ እንደሚሄድ እና ከዚህ አኳያም የምርት አቅርቦት ዋጋ ከቀን ወደ ቀን ከፍ እያለ እንደሚሄድ የፋኦ የጥናት መግለጫ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.