2011-03-04 15:52:58

ብፁዕ ኣቡነ ቶማሲ፦ የማኅበረ ክርስትያን ሁኔታ በዓለም


በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ብፁዕ አቡነ ሲልቫኖ ማሪያ ቶማሲ ከትላትና በስቲያ ዋና ጽሕፈት ቤት ጀነቭ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ አስከባሪ ድርጅት የሰብአዊ መብት አስከባሪ ምክር ቤት ባካሄደው 16ኛው ክፍለ ጉባኤ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር፣ የሃይማኖት ነጻነት ጉዳይ በዓለም ያለው ተጨባጭ ሁኔታ RealAudioMP3 በመዳሰስ በዚያኑ ዕለት በፓኪስታን የተገደሉት በአገሪቱ የመንግሥት ሥልጣን በኃላፊነት የተቀመጡት ብቸኛ የመጀመሪያ ካቶሊክ ምእመን የአገሪቱ የውሁዳን የኅብረተሰብ ጉዳይ ሚኒ. ሻባዝ ብሃቲ ጉዳይ በማንሳት በሚኒስትሩ ላይ የተፈጸመው የቅትለት አደጋ በዓለማችን የክርስትያኖች ሕይወት ምንኛ አደጋ መጋለጡ እና ጸረ ክርስትያን ዓመጽ እየተስፋፋ መሆኑ የሚያረጋገጥ ሁኔታ ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ። ብፁዕነታቸው በማያያዝ በእስያ እና በአፍሪካ እየተዛመተ መሆኑ ገልጠው፣ የክርስትያኖች መብት እና ፈቃድ በመጣስ ብቻ የሚታጠር አመጽ ሳይሆን፣ የግድያ ተግባር ጭምር የሚከተለው አመጽ ነው። ይህ የክርስትያኖች ሁኔታ ለዓለም ማኅበርሰብ የኅሊና ጥያቄ መሆን ይገባዋል። ማኅበረ ክርስትያን የዓመጽ ሰለባ እንዲሆኑ የሚዳርገው ምክንያት ለይቶ ለመግለጥ አስቸጋሪ ባይሆንም ቅሉ በመንግሥት ደረጃም የሚወሰዱት ውሳኔዎች አንዳንድ የሃይማኖት ቡድኖች በዓለማችን እያስፋፉት ላለው የፀንፈኛነት ርእዮት የሚቀሰቅስ ሆኖ እንደሚገኝ ነው። አነዚህ ፅንፈኞች መለያቸው የሚያረጋገጡት ከእነርሱ በሃይማኖት የተለየውን ማጥፋት እንደ መሠረት በማድረግ የሚፈጽሙት ጸረ ክርስትያን ያነጣጠረ ተግባር ነው። የመለያ ኅልውና የሌላው መለያ ኅልውና መሰረዝ በሚለው ጭፍን ጽንሰ ሃሳብ የተመራ ጸረ ሰብአዊ ተግብር ነው ብለዋል።

ክርስትያኖች ለሚፈጸምባቸው አመጽ የተስተካከለ ግብረ ምለስ የማይሰጡ በምኅረት የሚያምኑ በመሆናቸው የብቀላ ጥማት የለባቸውም፣ ስለዚህ ይህ ጥልቅ የእምነት ተግባር በቀላሉ የአመጽ ኢላማ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፣ ሆኖም ግን መንግሥታት እና የዓለም ማኅበርሰብ በማኅበረ ክርስትያን ላይ የሚሰነዘረው እና እየተስፋፋ ያለው አመጽ ለመግታት እምብዛም ጥረት የሚያደርጉ አይመስልም፣ ስለዚህ ይህ ለገዛ እራሱ ለጸረ ክርስትያን አመጽ መስፋፋት ምክንያት ሊሆን ይችላል ካሉ በኋላ፣ ይህ ጸረ ክርስትያን ዓመጽ፣ ጸረ ውሁዳን የማኅበረሰብ ክፍል የመሳሰሉት ጸረ ሰብአዊ ድርጊቶች መፍትሔ እንዲያገኝ በአንዳንድ አገሮች በተለይ ደግሞ በኤውሮጳ አንዳንድ የፖለቲካ አካላት ዋና ርእስ በማድረግ በዓለም አቀፍ መድረኮች ሲንቀሳቀሱ ይታያል። የሃይማኖት የአምልኮ እምነትን የመግለጥ ነጻነት የማንኛው የሰው ልጅ ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ነው። ምክንያቱን የሰው ልጅ ወደ ላይ የሚያቀናው የመለኮት ጥማት እና የመሻት ባህርዪ መሠረት ያለው ነው፣ ስለዚህ ይኸንን ጥልቅ የሰው ልጅ መሆናዊ ባህርይ ማክበር እና መጠበቅ ሌላው ለማክበር እና ለሰላማዊ ማኅበራዊ ኑሮ ለሚደረገው ጥረት መሠረት ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.