2011-02-28 17:20:51

የር.ሊ.ጳ የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ ኣስተምህሮ


ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ! የዛሬው ሥርዓተ ኣምልኮ በመጽሓፍ ቅዱስ ከሚገኙ ኃይለኛ ቃላት ኣንዱን ያስተጋባል። ይህንን ቃል መንፈስ ቅዱስ በኢሳይያስ ነቢይ ብርዕ በዳግማዊ ኢሳያስ በሚለው መጽሓፈ ትንቢት ሰጥቶናል፣ ቃሉም በተለያዩ ችግሮች ተከባ ለነበረች ኢየሩሳሌም ለመጽናናት የተሰጠ ነው፣ እንዲህም ይላል፣ ‘ልጅዋን ልትረሳ ትችላለችን? ለወለደችውስ ልጅ ኣትራራለትምን? ምናልባት እርስዋ ትረሳ ይሆና፣ እኔ ግን ኣልረሳሽም።’ (ትንቢተ ኢሳይያስ 49፣15) ይህ ጥቅስ በማይሸነፈው በእግዚአብሔር ፍቅር እንድንተማመን ጥሪ ያቀርባል፣ ቅዱስ ማቴዎስም ዛሬ በሚነበበው ወንጌል ኢየሱስ ለሐዋርያቱ ለሰማይ ወፎች ምግብ በሚሰጥና የበረሃ ኣትክልትን በኣበባ በሚሸልም እንዲሁም የእያንዳንዱን ፍላጎት በሚያውቅ በሰማያዊ ኣባት አሳቢነት እንዲተማመኑ ይማጠናል። ይህንን ሲገልጥ ጌታ ኢየሱስ በወንጌለ ማቴዎስ 6፣31-32 ‘እንግዲህ። ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና።’ በማለት ያብራረዋል።

በኣሰቃቂ ችግር የሚኖሩ በቅርብ በምንመለከታቸውና በሩቅ በምንከታተላቸው የብዙ ሰዎች ሁኔታ ስንመለከት ይህ የኢየሱስ ንግግር እምብዛም እውን ሆኖ ሊታየን ይችል ይሆናል። እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ጌታ ሊያስረዳን የፈለገው ለሁለት ጌቶች ማለትም ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መታዝዝ እንደማይቻል ነው። ልጆቹን በሙሉ ፍቅር በእግዚአብሔር የሚያምን የሚያስቀድመው የእግዚአብሔርን መንግሥትና ፍላጎት ወይም ፈቃድ መፈለግ ነው፣ ይህ ኣቋም በዕድል የማመንና የመወሰን ተቃራኒ ነው፣ በእግዚአብሔር ኣሳቢነት መተማመን የተገባ ሕይወት ለመኖር ከሚደረገው ትግል ነጻ ኣያደርግም፣ ሆኖም ግን ከማይሆን ጭፍን ኣስተያየትና ለነገ ካለን ጭንቀት ነጻ ያደርገናል። ይህ ሁላችንም በእኩል የሚመለከት የኢየሱስ ትምህርት በተለያዩ የሕይወት ጥሪዎች በተለያየ ኣኳሃን እተግባር ላይ እንደሚውል እውን ነው። ለምሳሌ ያህን ኣንድ የቅዱስ ፍራንቸስኮስ ማኅበር መነኮስ ትምህርቱን ቃል ለቃሉ በመከተል ከበድ ያለ የተጋድሎ ህይወት ሲኖር፣ ኣንድ የቤተ ሰብ ኣባት ግን ለባለቤቱና ለልጆቹ ሊያደርግላቸው የሚገባቸውን ነገሮች በማሰብ ግዴታዎቹን ሊወጣ ይታገላል። ያም ሆነ ይህ ክርስትያንን እንደ ኢየሱስ ከሌሎች የሚለየው በሰማያዊ ኣባቱ ኣሳቢነት ያለው ፍጹም መተማመን ነው፣ ለኢየሱስ ሕይወት እንዲሁም ለንግግሩና እስከ ሕማማት ሞትና ትንሳኤ ለፈጸማቸው ተግባሮቹ ትርጉምና ስሜት የሚሰጠው ከእግዚአብሔር ኣባቱ ጋር የነበረው ግኑኝነት ነው፣ በዚሁ ምድራዊ ሕይወታችን ልብን ወደ ሰማያዊ ነገሮች በማኖርና በእግዚኣብሔር ምሕረት ሙሉ በሙሉ በመጥለቅ ተጨባጭ የጓደኞች ሁኔታን ጠንቅቆ በመጠበቅ በምድር ላይ መኖር ምን ትርጉም እንዳለው በተግባር ኣሳይቶናል።

የተከበራችሁ ጓደኞቼ የዛሬው እሁድ ቃለ እግዚአብሔር በሚያብራራልን መንገድ እመቤታችን ድንግል ማርያምን የመልኮታዊ ኣሳቢነት እናት ብላችሁ እንድትማጠንዋት አደራ እላለሁ። ሕይወታችን የቤተ ክርስትያናችን ጉዞ እና የታሪክ ክንዋኔዎችን ለእርስዋ እናማጥነው። በተለይ ደግሞ እያንዳንዳችን በዕለታዊ ተግባራችንና እግዚአብሔር እንድንንከባከበው የሰጠንን ተፈጥሮን በመጠበቅ በገርነትና በመጠን ለመኖር እንድንማር ዘንድ በኣማላጅነትዋ እንማጠን።’








All the contents on this site are copyrighted ©.