2011-02-25 14:24:30

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት መልእክት ለአርባ ጾም


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ለአርባ ጾም መልእክት አስተላልፈዋል። ቅድስነታቸው ጾመ አርባ መሠረት በማድረግ ባስተላለፉት መልእክታቸው ላይ ጥምቀት የእግዚአብሔር ስጦታ መሆኑ ማእከል ያደረገ መልእክት መሆኑ ታውቆዋል። የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የአርባ ጾም መልእክት በጥምቀት ከመድኅን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ተቀብራችሁዋል ከሱ ጋርም ተነስታችሁል ይላል ።

ጥምቀት ፡ የድሮ ባህል እንዳልሆነ ያመለከተ ይቅዱስ አባትችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ መልእክት ፡ ከከርስቶስ የሚደረገው ግንኙነት እና መለኮታዊ ሕይወት ሰጭ መሆኑ ያሰገነዝባል። በእርግጥ ጥምቀት የእግዚአብሔር ስጦታ ነው ያለው በነዲቶስ አስራ ስድስተኛ ለአርባ ጾም ያስተላለፉት መልእክት በገዛ ፍላጎቱ እና ኀይሉ ዘለዓለማዊ ሕይወት ለመቀዳጀት ተክህሎ እንደሌለው ያመለክታል። ጾም እና ጥምቀት የተሳሰሩ እና የሰው ልጅ ድህነት መሳርያ መሆናቸው መልእክቱ ይገልጻል።

የእግዚአብሔር ስጦታ የሆነ ጥምቀት ህያው እንዲሆን የክርስትያኖች ሀላፊነት መሆኑ የጠቀሰ መልእክቱ የጥንት ቤተ ክርስትያን ክርስትያን ጥምቀት የህልውናቸው ወሳኝ መሆኑ መገንዘባቸው እና የእግዚአብሔር ስጦታው በሚገባ ማቀባቸው የቅድስነታቸው የጾመ አርባ መልልእክት ዘግበዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ ለጾመ አርባ ያስተላለፉት መልእክት አያይዞ ለዓቢይ በዓለ ትንሳኤ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚያደርሰን ጾመ አርባ በሚገባ በመከታተል ሐቅ እና ሕይወት ወደ ሆነ በዓለ ትንሳኤ እንድረስ ያልል።

ምእመናን በጾመ አርባ ግዜ ጸም እና ጸሎት በማዝውተር ጾመ አርባ የሚጠይቅውን አግባብ በመከተል የመቀየር ሂደት በመከተል ለብርሃነ ትንሳኤው እንዲደርሱ ቅድስነታቸው ለጾመ አርባ ያስተላለፍት መልእክት አሳስበዋል።

መጦም ከምግብ መታቀብ ፡ ከራስ ወዳድነትን ተላቀን በፍቅር እና በደስታ ለመኖር ይረዳናል ይህ ሁሉ ለሌለው በመቻር የተሰኘ መሆን እንደሚገባም የቅድሰነታቸው መልእክት ይገልጣል። ጸሎት የዘለዓለመዊ ሕይወት መንገድ እና ከእግዚኣአብሔር ጋር የሚያገናኝ መስመር መሆኑ መልእክቱ ያስገነዝባል ።

በሌላ በኩል ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ለጾመ አርባ ያስተላለፍት መልእክት ይፋ በሆነበት የቫቲካን ማኅተም ክፍለ የተገኙ በቅድስት መንበር የኮር ኡኑም የተወሃሃደ ልብ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ብፁዕ ካርዲናል ሮበርት ሳራህ እንዳመለከቱት ፡

ቅድስነታቸው ለጾመ አርባ ያስተላለፉት መልእክት የቢተ ክህነት አባልትም ምእመናንም ሁላችን ክርስትያን ለድሃ ሕብረተ ሰቦች ፍቅር ርህራሔ እንዲኖረን ከራስ ወዳድነት እንድንላቀቅ እንድንለወጥ እምነታቻን በሚገባ ለመኖር እንድንጥር ያማለክታል ብለዋል።

መልእክቱ ይላሉ ብፁዕ ካርዲናል ሮበርት ሳራህ ጥምቀት ማከል ያደረገ ዳግመ ህንጸተ ልብ የሚጠይቅ ቅዱስ ወንጌል የሕወታችን መመርያ እንድናደርግ መንፈሳዊ ሕይወት እንድንኖር የሚጠይቅ እና የሚያሳስብ መሆኑ ገልጠዋል።

በቅድስት መንበር የኮር ኡኑም የተወሃሃደ ልብ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ብፁኦ ካርዲናል ሮበርት ሳራህ በሳቸው የሚመራ ይሄው ተቋም አስታውሰው ኮር ኡኑም ለተቸገረ እና የስቃይ ሰለባ ለሆነ ሁሉ በመርዳት የፍቅር የርህራሔ ስራ እየሰራ መሆኑ አስታውሰዋል። አያይዘው ከአንድ ዓመት በፊት በደሴት ሃዪቲ የተከሰተው አሰቃቂ በሆነ የመሬት መናወጥ ከሁለት መቶ ሺ በላይ ህዝብ ለሕለፈት መዳረጉ በብዙ ሚልዮን መጠለያ አልባ መቅረቱ በማስታወስ መቅሰፍቱ እጅግ አሳዛኝ መሆኑ አመልክተዋል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ፓጳሳት በነዲክቶስ አስቃቂ የመሬት መናወጥ እንድተከሰተ በኮር ኡኑም በተወሃሃደ ልብ በኩል ሁለት ሚዮን ዶላር ለሃዪቲ ህዝብ መቻራቸው አመልክተዋል።

ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርትያን ማተርያላዊ ርዳታ ብቻ ሳይሆን በመንፈሳዊ በኩልም ለችግር ለተጋለጠ ህዝብ እንደምትሰራ አስታውቀዋል።

በርካታ የቤተ ክርስትያን የርዳታ ተቋሞች በተለያዩ ክፍለ ዓለማት መንፈሳዊ ኣና ማተርያላዊ ሰብአዊ ራዳታ እየሰጡ መሆናቸው ያስታውሱት ብፁዕ ካርዲናል ሳራህ እስፓኛ ውስጥ የሚገኘው Manos Unidos የተባበሩ እጆች የተባለ በ60 የተለያዩ የዓለም ሀገራት የሚገኝ ሰብአዊ ተቋም ለተቸግሩ የሚሰጠው ሰብአዊ ርዳታ አድንቀው አሞግሰዋል።

ካሪታስ እንተርናጽዮናሊስ የተባለ ሀገራት አቀፍ ካቶሊካዊ የግብረ ሰናይ ድርጅት ሙያም በማስታወስ ድርጅቱ እየሰጠው ያለውን ሰብእዊ ርዳታ የታወቀ እንደሆነ በቅድስት መንበር የኮር ኡኑም የተወሃሃደ ልብ ጳጳሳዊ ምኽር ቤት ልቀመንበር ብፁኦ ካርዲናል ሮበርት ሳራህ አስገንዝበዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.