2011-02-11 13:26:55

መናንያን እና የሐዋርያዊ ማኅበረሰብ አባላት ሕይወት ኅያው እና ፍሪያማነት


የመናንያን እና የሐዋርያዊ አገልግሎት ማኅበራት ሕይወት እና ጥሪ ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ኣቡነ ጆሰፍ ዊሊያም ቶቢን የላቲን ሥርዓት አምልኮ ግፃዌ የምትከተል ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን እ.ኤ.አ. የካቲት 2 ቀን 2011 ዓ.ም. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእየሩሳሌም ቤተ መቅደስ የቀረበበት በዓለ በአቱ ከሚከበርበት ዕለት ጋር በማያያዝ ሥነ ቲዮሎጊያዊ RealAudioMP3 እና መንፈሳዊ ትርጉም መሠረት በማድረግ ታስቦ የዋለው የመናንያን የገዳማውያን እና የሐዋርያዊ አገልግሎት ጥሪ ቀን ምክንያት፣ ቅዱስ አባታችን የመናንያን ማኅበር አባላት ካህናት እና ደናግል በኅብረተሰብ ዘንድ ቦግ ብሎ የሚታይ ቅንነተ እና እውነት ቃል እና ሕይወት ያጣመረ ምስክርነት በመስጠት የጥልቅ ውበት መስካሪያን ናቸው ያሉትን ሐሳብ በማስደገፍ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የመናንያን እና የሐዋርያዊ አገልግሎት ማኅበር አባላት ጥሪ የቤተ ክርስትያን እስትንፋስ እና የቤተ ክርስትያን ኅብረ ውበት ተጨባጭ መግለጫ መሆኑ አስረድተዋል።

በዓለም የእግዚአብሔር ብርሃን ቦግ ብሎ እንዲታይ በማድረግ ተልእኮ ለማገልገል ሕይወታቸውን ለእግዚአብሔር የሚሰዉ መናንያን ገዳማውያን ካህናት እና ደናግል ሕዝበ እግዚአብሔር ሊከተለው ለሚገባው ሕይወት አርአያ መሆናቸው ቅዱስ አባታችን የሰጡት ሥልጣናዊ ማብራሪያ መሠረት በማድረግ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ናዝሬት በሚገኘው ሙክራብ ተገኝቶ የነቢዩ ኢሳያስ መጽሐፍ ተሰጥቶት መጽሐፉን በመግለጥ “የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፣ መልካም ዜናን ለድኾች እንዳበሥር ሾሞኛል፣ ለታሠሩት መፈታትን ለታወሩት ማየትን እንዳውጅ፣ የተጨቈኑትን ነፃ እንዳወጣ ልኮኛል። እንዲሁም እግዚአብሔር ሕዝቡን የሚያድንበት የጸጋ ዓመት እንዳስታውስ ልኮኛል” ሲል ያነበበው መልእክት የሚኖርበት ነው። ስለዚህ የመናንያን እና የሐዋርያዊ ማኅበረሰብ አባላት ጥሪ ተቀዳሚ መሆናዊ ትርጉም እና ተልእኮው ይህ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተነበበው የገዛ እራሱ ተልእኮ የሆነው በቤተ ክርስትያን ሥር የሚኖርበት ሕይወት ነው ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት አቢይ ችግር የሆነው የጥሪ ማነስ ሳይሆን በለገዝጋዛ እና በወላዋይነት የሚኖር ጥሪ ነው። ስለዚህ ገዳማዊ፣ የሐዋርያዊ ማኅበርሰብ አባል መሆን የተመቻቸ ሕይወት መኖር ማለት ሳይሆን፣ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተልእኮ የተሰዋ ፍቅር በቤተ ክርስትያን መሪነት እና ማኅበራቱ በተቀበሉት የተልእኮ መንፈሳዊ ጸጋ መለያ አማካኝነት የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው ሲል፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያብራራው የተልእኮ መሠረታዊ ኃላፊነት በግል ደረጃ ሳይሆን የቤተ ክርስትያን አባል ከመሆን በሚመነጭ መንፈስ ተደግፎ የሚኖርበት ነው። በዚህ መንፈስ የሚመራ እና ይኸንን ሕይወት በቃል እና በሕይወት የሚኖር የመናንያን የገዳማውያን እና የሐዋርያዊ ማኅበርሰብ አባላት ሕይወት ወጣቱ ተውልድ ከእግዚአብሔር የሚቀርብለት ጥሪ ለማዳመጥ ደጋፊ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.