2011-02-10 09:46:34

ህንድ፣ በካርናታካ ግዛት የተፈጸመው ጸረ ክርስትያን አመጽ


በህንድ የሶማሸካራ ግዛት በምትገኘው የካርናታካ ከተማ በሚኖሩት ማኅበረ ክርስትያን የአገሪቱ ዜጎች ላይ እ.ኤ.አ. በ 2008 ዓ.ም. ቀጥሎም በ 2009 ዓ.ም. የተጣለው አመጽ በመከታተል እንዲያጣራ እና ስለ ጉዳይ ዘገባ እንዲያቀርብ የሶማሸካራ ግዛት መንግሥት ያቋቋመው የፍትህ ድርገት ባካሄደው ምርመራ መሠረት ያቀረበው ሰነድ፣ የካርናታካ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር የባንጋሎረ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቤርናርድ ሞራስ የህንድ ዜጋ የሆኑት ማኅበረ ክርስትያን በተለይ ደግሞ በካርናታካ ክልል የሚኖረው እና የአመጽ ሰለባ የሆነው በደል እና ግፍ የደረሰበት ማኅበረ ክርስትያንን ሌሎች በሚል አጠራት ማለትም የኅብረተሰብ አካል እና ክፍለ ኅብረተሰብ እንዳልሆነ መጤ አድርጎ ሲያቀርባቸው እና ሲገልጣቸው የሚያሳዝን ነው። የአመጹ ሰለባ የሆኑት ማኅበረ ክርስትያን ሆነው እያሉ ሆኖም ይኸንን መለያቸውን በመሸፈን ጠቅለል ባለ አነጋገር ሌሎች ብሎ በመሰየም በቅድሚያ የአመጹ ተጠያቂ ግለ ሰቦችም ይሁን ድርጅቶች ለመለየት ከአዲሁ እንቅፋት ከመሆኑም በላይ ተጠያቂዎች ለፍርድ ለማቅረብ የሚለው ፍላጎት የሚያከሽፍ እና ጸረ ክርስትያን አመጽ የማያስጠይቅ ወንጀል ያስመስለዋል ብለዋል።

በሌላው ረገድ ማኅበረ ክርስትያን የሌሎች የኑሮ ድኽነት ተገን በማድረግ በገንዘብ ኃይል የሌሎች ሃይማኖት ተከታዮች ክርስትያን እንዲሆኑ እያደረጉ ናቸው የሚል ሀሳብ የሰፈረበት እና ማኅበረ ክስትያን ጸረ ማኅበራዊነት እንደሆኑ በውስጥ ታዋቂነት ይገልጣቸዋል። ስለዚህ ሰነዱ የክልሉ ማኅብረሰብ የሚከፋፍል ከመሆኑም ባሻገር፣ ማኅበረ ክርስትያን ለአደጋ የሚያጋልጥ ሃይማኖታዊ ወጥረት የሚጋብዝ ነው። በተለይ ደግሞ የክርስትያን የአምልኮ ሥፍራዎች ቁጥጥር እና ክትትል ማድረግ አስፈላጊ ነው የሚል የሠፈረው ሐሳብ፣ ማኅበረ ክርስያን ለአመጽ ለአድልዎ እና ለስደት አደጋ የሚያጋልጥ ነው ብለዋል።

ብፁዕ አቡነ ሞራስ ባስተላለፉት መልእክት አክለው፣ የክልሉ መንግሥት በማኅበረ ክርስትያን ላይ የተፈጸመው አመጽ ተጣርቶ የድርጊቱ ተጠያቂዎች ተለይተው ለሕግ እንዲቀርቡ ያደርግ ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.