2011-02-07 13:05:48

የኢጣሊያ ቅዱስ ጠባቂ ቅዱስ ፍራንቸስኮስ ዘአሲዚ


ቅዱስ ፍራንቸስኮስ የኢጣሊያ ቅዱስ ጠባቂ በሚል ርእስ ሥር በየወሩ የሚታተመው መጽሔት እ.ኢ.አ. ከዚህ ከተገባው ወር ጀምሮ በሁሉም የጋዜጣ እና የመጽሔት መሸጫ ጣቢያዎች አማካኝነት ለአንባብያን እንደሚቀርብ የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት አስታወቀ።

ይህ መንፍሳዊ እና ባህላዊ መጽሔት የዛሬ 71 ዓመት RealAudioMP3 በፊት ጀምሮ በየወሩ ለኅትመት የበቃ መሆኑ ለማወቅ ሲቻል፣ በዚህ እ.ኤ.አ. በየካቲት ወር የቀርበው ኅትመቱ አምካኝነት የ71 ዓመት ታሪክ ይካተተ፣ የአሲዚ መንፈሳዊነት፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በአሲዚ የሃይማኖት ነጻነት እና ሰላም ርእሰ ጉዳይ ያደረገ የሁሉም ሃይማኖት መሪዎች እ.ኤ.አ ጥቅምት ወር ለጋራ ጉባኤ እና ጸሎት ያቀረቡት ጥሪ በጥልቀት የሚያብራራ፣ አበይት ምሁራን እና ሊቃውንት ከእነርሱም ውስጥ የባህል ጉዳይ የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጃንፍራንኮ ራቫዚ፣ በኢጣሊያ የሶለ 24 ኦረ ዕለታዊ ጋዜጣ አስተዳዳሪ እና ዋና አዘጋጅ ፈሩቾ ደ በርቶሊ፣ ጆቫኒ ማሪያ ቪያን፣ አልዶ ማሪያ ቫሊ፣ አንድረያ ሪካርዲ፣ የኢጣሊያ የውስጥ ጉዳይ ሚኒ. ሮበርቶ ማሮኒ እና ሌሎች ያሳተፈ ኅትመት መሆኑ ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.