2011-02-04 15:41:46

ስፐይን፣ ለዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን


ሁሌ በየዓመት ከሁሉም አገሮች የተወጣጡ ወጣቶችን በማሰባሰብ ከቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ አስተምህሮ ምክር፣ የሚለገስበት የተለያዩ መንፈሳዊ እና ባህላዊ መርሃ ግብር የሚረጋገጥበት በጠቅላላ እምነት የሚመሰከርበት ኵላዊነት ቤተ ክርስትያን የምታዘጋጀው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን እቅድ መሠረት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የዘንድሮው 26ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን RealAudioMP3 በስፐይን ርእሰ ከተማ ማድሪድ እ.ኤ.አ. ከነሓሴ 16 ቀን እስከ ነሓሴ 21 ቀን 2011 ዓ.ም. እንዲካሄድ መወሰናቸው የሚዘከር ሲሆን፣ ይህ የሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ ወድ ቆላሲያስ ሰዎች የጻፈው መልእክት ምዕራፍ ሁለት ቅጥር 7 “በእርሱ ተመሥርታቸሁና ታንጻፍሁ በተማራችሁት መሠረት በእምነታችሁ ጸንታችሁ ኑሩ…” የሚለውን ቃል መርህ በማድረግ በማድሪድ የሚካሄው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን እምነት የሚገነባበት፣ እምነት የሚመሰክርበት እና በማኅበራዊ ሕይወት እምነትን በቃል እና በሕይወት ለመመስከር የእምነት ሥልጠና የሚረጋገጥበት መድረክ መሆኑ፣ የሮማ ሰበካ የወጣቶች ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ድርገት ተጠሪ አባ ማውሪዚዮ ሚሪሊ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ በማብራራት፣ እያንዳንዱ ወጣት እግዚአብሔር ማን ነው የሚለው ጥያቄ በቅርብ በማጤን በቃል እና በሕይወት ከሚቀርበው ምስክርነት መልስ የሚያገኝበት እምነት በተግባር ለመኖር የሚያግዝ ወጣቱ እምነቱን እንዲመሰክር የሚያነቃቃ መድረክ መሆኑ ገልጠዋል።

በተባለ እና ከሚነገረው ታሪክ ክርስቶስ መቀበል ሳይሆን ከተባለው እና ከተነገረው ባሻገር እያንዳንዱ ከክርስቶስ ጋር ግኑኝነት እንዲኖረው የሚያግዝ የሚያነቃቃ ቀን ነው ካሉ በኋላ ሰላም ፍቅር መከባበር መደጋገፍ የሚከተል ወጣቶች የእምነት አብዮተኞች እንዲሆኑ የሚያነቃቃ መርሃ ግብር መሆኑ በማብራራት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.