2011-02-02 15:27:04

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፣ ያልተወሳሰበ ምሥጢር እና አቢይ በዓል


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ገና በተወለደበት በአርባኛው ቀን በኢየሩሳሌም ወደ ሚገኘው ቤተ መቀደስ የቀረበበት እለት የሚዘከርበት አቢይ በዓል እና ከዚህ ዓቢይ ጋር በተያያዘ ሥነ ቲዮሎጊያዊ እና መንፈሳዊ ትርጉም መሠረት በማድረግ ታስቦ የሚውለው 15ኛ የመናንያን የገዳማውያን እና የሐዋርያዊ አገልግሎት ጥሪ ቀን የመናንያን ማኅበር አባላት ካህናት እና ደናግል አባላት የተሳተፉበት በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ትላንታን የበዓሉ ዋዜማ የመጀመሪያው ጸሎተ ሠርክ RealAudioMP3 መምራታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ይህ የላቲን ሥርዓት አምልኮ ግፃዌ የምትከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ዛሬ ያከበረቸው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤተ መቀደስ የቀረበበት ዓቢይ በዓል በሌላ መልኩ በዓሉ የመናንያን እና የገዳማውያን እንዲሁም የሐዋርያዊ አገልግሎት መናንያም ማኅበር አባላት በዓል መሆኑ ሲገለጥ፣ ይኸንን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የአርባ ቀን ሕፃን እያለ ወደ ቤተ መቀደስ የቀረበበት ዕለት የሚዘከርበት በዓል ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ያልተወሳሰብ ጥልቅ ምሥጢር እና አቢይ በዓል በሌላ መልኩ የቅድስት ቤተ ሰብ በዓል የመላ ሰው ዘር የሚመለከት እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መከፋፈልን መራራቅን የልዩነት አጥር በማግለል በእግዚአብሄር እና በሰው ልጅ መካከል ፍጹም ገላጋይ በመሆን ገና በሕጻንነቱ እና እስከ ፍጻሜም በመታዘዝ ከማርያም ፍጹም ተአዝዞ ጋር የማዳን ተልእኮ እንደ ጀመረ ቅዱስ አባታችን እ.ኤ.አ. የካቲት 2 ቀን 2006 ዓ.ም. ዓለም አቀፍ የመናንያን ቀን ምክንያት በማድረግ ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት እንዳመለከቱ የሚዘከር ሲሆን፣ ቅድስት ድንግል ማርያም ሕፃን ኢየሱስን እየሩሳሌም ወደ ሚግኘው ቤተ መቀደስ ለእግዚአብሔር በማቅረብ የዓለም ሓጢኣት የሚያነጻ የእግዚአብሔር በግ በስምዖንና በሓና ፊት ካቀረበችው በኋላም የተስፋ ቃል መፈጸሙ ተገለጠ፣ ዕለቱ የእስራኤል የመዳን ተስፋ ይጠበቁ ለነበሩት ሁሉ መሲህ የተገለጠበት የሚያረጋግጥ አቢይ በዓል መሆኑ ቅዱስ አባታችን በማብራራት፣ በእውነት እና በፍቅር ጎዳና በሚደረገው ጉዞ ለእግር ብርሃን ሆኖ የሚመራ እውነት እና ፍቅር የተገለጠበት ቀን ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ በማስታወስ ጠቅሶታል።

እ.ኤ.አ. የካቲት 2 ቀን 2006 ዓ.ም. ባሰሙት ስብከት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እና የማርያም ተአዝዞ እግዝአብሔርን ለማገልገል እና በቤተ ክርስትያን እና በዓለም የእግዚአብሕIአር ብርሃን ቦግ ብሎ እንዲታይ በማድረግ ተልእኮ ለማገልገል ሕይወታቸውን ለእግዚአብሔር የሚሰው መናንያን ገዳማውያን ካህናት እና ደናግል ሊከተሉት የሚገባ አርአያ ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፍጹም ተአዝዞ እና መሥዋዕት ኅያው እግዚአብሔር ከኛ ጋር መሆኑ ያረጋገጠበ ዕለት ሲታሰብ፣ መናንያን በጠቅላላ በመካከላችን ለእግዚአብሔር መንግሥት ኅላዌ የርቱዕ አንደበት ትእምርት ናቸው። ስለዚህ ካህናት ደናግል በጠቅላላ መናንያን ሕይወታቸው ለክርስቶስ እና ለቤተ ክርስትያን እጅ ሲያስረክቡ የሰውል ልጅ ሊረዳው በሚችለው ኅያው አንደበት በመካከላቸው የእግዚአብሔር ከኛ ጋር መሆኑ መስካሪያን ናቸው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ያስታውሳል።

መናንያን፣ ካህናት ደናግል ብዙውን ጊዜ በተደናገረው ጎዳና ለሚመላለሰው የሕይወት ትርጉም የሆነው የሕይወት እና የኅልውና እውነተኛ ጌታ የሆነው እግዚአብሔርን የሚሻው የሰው ልጅ በቃል እና በሕይወት አብነት በመሆን እውነተኛው የሕይወት ትርጉም የት እንዳለ እና ማን መሆኑ የሚያበሥሩ ናቸው። በሕይወት ታሪክ የአዲስ ሕይወት መሥካሪያን ናቸው። ምድራዊ ሕይወታቸው ከእግዚአብሔር ጋር ፊት ለፊት ለምንገናኝው ሕይወት ሸኝ ነው። ስለዚህ ምድራዊው ሕይወታቸው የተለያየ ችግር የሚፈራረቅበት ቢሆንም ቅሉ፣ ከሁሉም በላይ እግዚአብሔርን በማስቀደም የሚኖረው የተአዝዞ የድኽነት እና የድንግልና ሕይወት በመመስከር ሁሉ ወደ እግዚአብሔር እንዲጓዝ ያ ሆነን ለምኖረው አዲስ ሕይወት ከወዲሁ መስካሪያን ናቸው በማለት እ.ኤ.አ. የካቲት 2 ቀን 2007 ጸሎተ ሠርክ መርተው ባሰሙት ስብከት እንደገለጡ የቅድስት መንበር መግለጫ ያስታውሳል።

የመናንያን እና የገዳማውያን ሕይወት ባይኖር ዓለማችን ምንኛ ድኻ በሆነ ነበር። የመናንያን ሕይወት ተልእኮ ካለው የአገልግሎት የኃላፊነት ገጽታ ባሻገር የሚሰዋው ፍቅር አብነት እና ምስክር ነው። በዚህ በፋይዳዊነት ላይ ብቻ በመታጠር በሚብለጨለጨው ቦግ ብሎ እልም በሚለው አታላይ ዓለም የሚሰዋ በነጻ የሚሰጠው ፍቅር ምስክር እና እኛን ለማዳን ሲል ሕይወቱን ለሰዋው የእግዚአብሔር ፍጹም ፍቅር የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እኔ ብሎ ሕይወቱን የሚሰዋ ሕይወቱን ያድናል ባለው ቃል ላይ የታመነ ሕይወት የሚኖርበት የሚሰዋው ፍቅር ሱታፌ መሆኑ እ.ኤ.አ. የካቲት 2 ቀን 2010 ዓ.ም. በዓሉን ምክንያት በማድረግ ጸሎተ ሠርክ በመምራት ባሰሙት ስብከት ማብራራታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ በማስታወስ ገልጦታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.