2011-01-31 15:00:10

ጸረ ክርስትያን ዓመጽ የሰው ዘረ ማጥፋት ወንጀል ነው


በኢራቅ በውሁዳን ኃይማኖት እና ጎሳዎች ላይ እየተከሰተ ያለው ዓመጽ አሳሳቢ ከመሆኑም ባሻገር ለክልሉ ሰላም እና መረጋገት ጭምር እንቅፋት በመሆኑ ምክንያት የአገሪቱ መንግሥት ይኸንን ጉዳይ በቅርብ የሚከታተል እና መፍትሔ የሚያፈላልግ የሁዳን ሃይማኖት እና ጎሳ መብት እና ፈቃድ መከበር የሚያነቃቃ እ.ኤ.አ. ባለፈው ዓመት ጥቅምት 31 ቀን ባግዳድ በሚገኘው የድህነት RealAudioMP3 እናት ቅድስት እመቤት ቤተ ክርስትያን የአጥፍተህ ጥፋ ያሸባሪያን ጥቃት መከሰት ማግሥት በኢራቅ መንግሥት ውሳኔ የተቋቋመው ድርገት በኢራቅ የሚጣለው ጸረ ውሁዳን ሃይማኖት ጥቃት በሰው ዘር የማጥፋት ወንጀል የሚያስጠይቅ ጸረ ሰብአዊ ወንጀል ነው በማለት እንደገለጠው ሲር የዜና አገልግሎት አመለከተ።

የውሁዳን ሃይማኖት ምእመናን እና ጎሳ ጉዳይ የሚከታተለው ድርገት፣ የውሁዳን ሃይማኖት መእመናን እና ጎሳዎች ላይ የሚጣለው አመጽ ለመግታት፣ ይኸንን ጉዳይ በቅርብ የሚከታተል እና በዚህ ዓይነት ወንጀል የሚጠየቁትን በመለየት ለተገቢ ፍርድ የሚያቀርብ የውሁዳን ሃይማኖት ምእመናን መብት እና ፈቃድ የሚያነቃቃ ቀጥተኛ ለኢራቅ ሬፓብሊክ ርእሰ ብሔር እና ለአገሪቱ መራሔ መንግሥት የተጠሪነት ሥልጣን ያለው ልዩ ጽ/ቤት እንዲቋቋም መወሰኑ ሲሪ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከትላትና በስትያ በናይጀሪያ ጆስ ከተማ በሙስሊሞች እና ክርስትያኖች መካከል በተካሄደው ግጭት ሳቢያ ሁለት ሰዎች ለሞት መዳረጋቸው ሲገለጥ፣ ሌሎች ምንጭች ግን 15 ሰዎች የሞት አደጋ እንደደረሰባቸው ይናገራሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.