2011-01-28 15:27:41

የናዚው ሥርዓት በአይሁዳውያን ላይ የፈጸመው ጅምላዊ እልቂት


በናዚው የአገዛዝ ሥርዓት ለሞት የተዳረጉት አይሁዳውያን የሚዘከሩበት ዓለም አቀፍ ቀን ትላንትና ታስቦ መዋሉ ሲገለጥ፣ የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ ባን ኪ ሙን ዕለቱን ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት መልእክት፣ በአረመኔው የናዚው ሥርዓት ውሳኔ ለጅምላዊ እልቂት ተላልፈው የተሰጡትን በማሰብ፣ በተለይ ደግሞ ከዚህ አሰቃቂው ጅምልዊ ግድያ የተረፉት አይሁዳውያን መቼም ቢሆን በህይውታቸው የማይረሳ ዘግናኝ ጠባሳ ጥሎ ማለፉን አብራርተው፣ ይህ የተፈጸመው ዘር የማጥፋት ተግባር እና ያስከተለው ማኅበራዊ RealAudioMP3 ሰብአዊ ፖለቲካዊ እና ኃይማኖታዊ ቀውስ በታሪክ እና በሰው ልጅ ኅሊና የማይረሳ ነው ብለዋል።

በአይሁድ ላይ የተፈጸመው ጅምላዊ እልቂት በዓለም አቀፍ ደረጃ ሲዘከር በዓለማችን ተመሳሳይ አሰቃቂ የቅትለት እና የአመጽ ተግበር ዳግም እንዳይከሰት ለሚለው ውሳኔ እና ቁርጥ ፈቃድ ኃይል መሆኑ ሲገለጥ፣ ይኽ በአይሁድ ላይ የተፈጸመው ጅምላዊ እልቂት የዛሬ 66 ዓመት በፊት በአይሽዊዝ ለተመሳሳይ እልቂት ተራቸውን በሚያሰቅቅ ሁኔታ ይጠባበቁ የነበሩት ነጻ የወጡበት ዕለት ጭምር መሆኑ ለማወቅ ሲቻል፣ እ.ኤ.አ. ጥር 27 ቀን 1945 ዓ.ም. የቀድሞ ሶቪየት ህብረት ጦር ኃይል በናዚው ፈላጭ ቆራጭ መከላከያ ኃይል ላይ ድል በመንሣት የተለያዩ ለጅምላዊ እልቂት ማጎሪያ ሰፈር በሮች በመክፈት የቀሩትን ነጻ ያወጡበት ዕለት ሲሆን፣ ይህ ታሪክ የቅርብ ታሪክ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ ከዚህ የሞት እልቂት ፍርድ የተረፉት የሚያወሱት የሚያስታውሱት እና የሚመሰክሩት ታሪክ ነው።

ከዚህ ጅምላዊ እልቂት ከተረፉት ውስጥ ሚያዝያ 11 ቀን 1987 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ኢጣሊያዊ ደራሲ ፕሪሞ ለቪ፣ የሰው ልጅ የዚህ ዓይነት አሰቃቂ ተግበር እንዴት በሌላው አምሳያው ላይ ይፈጽማል የሚል ጥያቄ በማቅረብ ይላሉ በአይሁድ ላይ የተፈጸመው ጅምላዊ ቅትለት ለመገመቱ እና ለመረዳቱ የሚያዳግት ቢሆንም፣ የዚህ ታሪክ የቅርብ ምስክር በመሆኑ ቀጥተኛ ገጠኝ ሊኖር ግድ ነው በማለት ሆኖም የተፈጸመ እልቂት በታሪክ የተፈጸመ ከሰብአዊ የታሪክ ኅሊና የማይፋቅ ሁኔታ ነው እንዳሉ ይዘከራል።

አይሁድውያን ለሞት ይዳረጉበት የነበረው በአውሽዊዝ የሚጠራው ጅምላዊ ቅትለት ይፈጸምበት የነበረው የማጎሪያ ሠፈር የዚህ ያለፈው ታሪክ ኅያው ቤተ መዘክር ሆኖ የሰውን ልጅ ሰብአዊ ክብር ለመሰርዝ ሆን ተብሎ ታልሞ እና ታቅዶ የተገነባው ማጎሪያ ሠፈር የሚመሰክረውና የሚያወሳው ጅምላዊ ቅትለት የተፈጸመበት ታሪክ ያለፈ ቢመስልም፣ ከሞት እልቂት በተረፉት አይሁዳውያን ኅሊና በማኅበራዊ ኅሊና ዘንድ ታትሞ የቀረው እውነታኛ ታሪክ ነው። የጅምላው እልቂት ታሪክ መዘከር ተመሳሳይ አሰቃቂ ድርጊት ላለ መፈጸም ኃይል ነው በማለት ዝክረ ዕለቱን ምክንያት በማድረግ የኢጣሊያ ሬፓብሊክ ርእሰ ብሔር ጆርጆ ናፖሊታኖ ባስተላለፉት መልእክት አስምረውበታል።

ይኸ በሰው ልጅ ላይ የተፈጸመው የጅምላ ግድያ ከሰው ልጅ ኅሊና ለመደለዝ አንዳንድ የታሪክ ሊቃውንት ነን ባዮች የሚፈጽሙት የታሪክ ክለሳ፣ መሠረት የሌለው ብቻ ሳይሆን ያ ታሪክ ለመሰረዝ ጥረት ማድረጉ ጅምላ ግድያ ከፈጸመው የናዚው አገዛዝ ሥርዓት ጋር በሚስተካክል ወንጀል የሚያስጠይቅ ነው።

ዝክረ ዕለቱን ምክንያት በማድረግ በተለያዩ የዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ያንን ታሪክ የሚያወሱ የተለያዩ የትረካ ፊልም የሥርጭት መርሃ ግብሮች መቅረባቸው ሲገለጥ፣ ይህ በእንዲህ እንዳለ የፊልም ደራሲ እና ቀራጭ ሮሰ ቦሽ እ.ኤ.አ. በ 1942 ዓ.ም. የናዚው ፈላጭ ቆራጭ መንግሥት በፈረንሳይ 13 ሺሕ ሕጻናት አዛውንት እናቶች እና ወጣቶች የሚገኙባቸው በወቅት በፈረንሳይ በነበሩት ተባባሪዎቹ አማካኝነት ለሞት የተዳረጉት የአይሁድ ሕጻናት ታሪክ የሚያወሳ የፊልም ትርኢት ትላትና በኢጣልያ በተለያዩ የሲኔማ አዳራሽ ለትርኢት መቅረቡ ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.