2011-01-28 15:29:07

የሶማሊያ ስደተኞች እና ተፈናቃዮች


በኢጣሊያ ርእሰ ከተማ ሮማ የቀድሞ የሶማሊያ መንግሥት ወኪል ሕንጻ ውስጥ የሚኖሩት 150 የሶማሊያ ተፈናቃይ እና ስደተኛ ዜጎች ሁኔታ እጅግ አሳዛኝ መሆኑ ሲገለጥ፣ እነዚህ ተፈናቃይ የሶማሊያ ዜጎች በኢጣሊያ ያቀረቡት የጥገኝነት ጥያቄ አወንታዊ ምላሽ የተሰጠበት ቢሆንም ቅሉ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ሆነው እያሉ፣ ነገር ግን መጠለያ የሌላቸው ሆነው ይኸው በቀድሞ የሶማሊያ ልኡከ መንግሥት RealAudioMP3 ሕንፃ ውስጥ ዘልቀው በመግባት ለመኖር ተገደው እያሳፉት ያለው ኑሮ እጅግ ለመገመቱ በሚያዳግት ችግር የተከናነበው የሕይወት ደረጃ መሆኑ ለማወቅ ሲቻል፣ የስደተኞች ጉዳይ የሚንከባከብ ሚግራረ፣ መሰደድ የተሰየመው ማኅበር አባል ሹክሪ ሳይድ የነዚህ የሶማሊያ ዜጎች ጉዳይ በማስመለከት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ እነዚህ 150 የሶማሊያ ስደተኞች የኑሮ ሁኔታ እጅግ የሚዘገንን ነው። በኢጣሊያ በታላቅዋ ሮማ እንዲህ ባለ የሰው ልክ በሌለው የሕይወት ደረጃ የሚኖር ሰው ማየቱ በጣም የሚያሳዝን ነው።

እነዚህ የሶማሊያ ዜጎች ወጣቶች ካንድ ፈላጭ ቆራጭ አምባ ገነናዊ መንግሥት ከሚያረማምደው የፖለቲካ የኤክኖሚ እና የማኅበራዊ ሥርዓት ያመለጡ ሳይሆን፣ ከአንዲት የእርስ በርስ ጦርነት ከተፋፋመባት ለጦርነት አውድማ ዕጣ እድል ከተተወች በሶማሊያ የአልቃይዳ የቀኝ እጅ ከሆነው ከአል ሻባብ ሃይል ከሚያረማምደው የምስልምና ሃይማኖት አክራሪነት ወጥመድ ያመለጡ ናቸው። ስለዚህ ከዚህ ዓይነት ችግር ቤት እና ንብረታቸውን ጥለው ለተሰደዱት ለሰው ልጅ ዕለታዊ ኑሮ የሚያስፈልግ በማቅረብ ዕለታዊ ኑሮአቸው የሰው ልክ ባለው የኑሮ ደረጃ እንዲኖሩ ማድረግ እንዴት ይሳነናል? በቅርቡ በኢጣሊያ ይፋዊ ጉብኝት ያካሄዱት የሶማሊያ ግዚያዊ የሽግግር መንግሥት መሪ እነዚህ 150 የሶማሊያ ስደተኞች ወደ ሚኖርበት ክልል በመሄድ የጎበኙዋቸውም ሲሆን፣ እነዚህ ዜጎች የሚገኙበት የሕይወት ደረጃ እጅግ እንዳሳዘናቸው እና ተገቢ እርዳታ እንዲያገኙ ለሚመለከተው አካል አቤት እንደሚሉ ማሳወቃቸው ሹክሪ ሳይድ በመግለጥ የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.