2011-01-28 15:30:14

ኢራቅ፦ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል


በኢራቅ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል ብፁዕ አቡነ ጆርጆ ሊንጓ በኢራቅ ከኩርዲስታን ራስ ገዝ ክልል አስተዳዳሪ ማሱድ ባርዛኒ እና በክልሉ ከሚገኙት ከተለያዩ ሃይማኖት መሪዎች ጋር መገናኘታቸው ባግዳድ ሆፕ የተሰኘው ድረ ገጽ ካሰራጨው ዜና ለመረዳት ሲቻል፣ ባርዛኒ በኩርድስታን ራስ ገዝ ክልል የሚኖሩት የተለያዩ ሃይማኖቶች አለ ምንም ውጥረት በሰላም እና በመደጋገፍ በመግባባት RealAudioMP3 እንደሚኖሩ ጠቅሰው፣ በኢራቅ በተለያዩ ክልሎች እና በባግዳድ የሚፈጸመው ጸረ ክርስትያን አመጽ በማውገዝ የኢራቅ ማኅበረ ክርስያን አገሩን ጥሎ እንዲሰደድ ሆን ተብሎ በአክራሪያ ኃይሎች የሚፈጸም ጥቃት እና የሚተላለፈው የዛቻ መልእክት በመቃወም፣ ኩርድ የተለያዩ ሃይማኖት ምእመናን በጋራ የሚኖሩባት የኢራቅ ክፍለ አገር ነች ካሉ በኋላ፣ በሳቸው የሚመራው የክልሉ መስተዳድር በኩርድ ተሰደው የሚኖሩት ማኅበረ ክርስትያን ጉዳይ የሚንከባከብ ድርገት መመልመሉ እና ከክልሉ መስተዳድር አስፈላጊ ትብብር እያገኙ ናቸው እንዳሉ ባግዳድ ሆፕ ድረ ገጽ ያመለክታል።

ብፁዕ አቡነ ሊንጓ በመቀጠልም ከኩርድ ክልል መንግሥት መሪ ባርሃም አህማድ ሳሊህ ጋር መገናኘታቸው አስዋት አል ኢራቅ የተሰየመው የዜና አገልግሎት ሲያመለክት፣ ብፁዕ አቡነ ሊንጓ በኩርድ ክልል ተሰዶ መጠለያ አግኝቶ የሚኖረው የኢራቅ አገር ውስጥ ስደተኛ ማኅበረ ክርስትያን ተገቢ ትብብር አግኝቶ በአገሩ ውስጥ እንዲኖር የሚያስችለው እድል እየተረጋገጠለት መሆኑ በቅርብ ለመገንዘብ እንደቻሉ ማሳወቃቸው አስዋታ አል ኢራቅ የዜና አገልግሎት ካሰራጭው ዜና ለመረዳት ተችለዋል።

የኩርድ ክልል ነዋሪ ሕዝብ ያሳለፈው ችግር በኢራቅ ውስጥ በተመሳሳይ ችግር ለሚጠቃው ማኅበረሰብ ቅርብ እንዲሆን እንዳደረገው የኩርድ የሃይማኖት ጉዳይ ተጠሪ ካማል አል ሓጂ አሊ በማሳወቅ፣ በአሁኑ ወቅት ለተለያዩ ችግሮች ተጋልጦ ለሚገኘው የኢራቅ ማኅበረ ክርስትያን መብት እና ፈቃድ ድጋፍ እና ትብብር የጸጥታ እና ደህንነት ዋስትና መረጋገጥ የኩርድ ክልል መሥተዳድር ያላሰለሰ ጥረት እያደረገ ነው እንዳሉ አስዋት አል ኢራቅ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.