2011-01-22 14:43:12

ቻይና - የተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት፦ ኤኮኖሚ እና የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ


ከትላትና በስትያ የተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት ርእሰ ብሔር ባራክ ኦባማ የቻይናው አቻቸውን ሁ ጁንታኦ ተቀብለው ማነጋገራቸው ሲገለጥ፣ ግኑኝነት የሁለቱ አገሮች ስለ ኤኮኖሚ እና ቁጠባ ርእሰ ጉዳይ በመወያየት ስምምነትም መፈራረማቸው ሲገለጥ፣ እንዲሁም ስለ ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ በተመለከተ ርእሰ ብሔር ባራክ ኦባማ የአገራቸው አቋም እንደገለጡ ከዋሽንግተን RealAudioMP3 የተሰራጩ ዜናዎች ያረጋገጣሉ።

ርእሰ ብሔር ባራክ ኦባማ ለሚቀጥሉት ሰላሳ ዓመታት በቻይና እና በተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት መካከል የሚኖረው የጋራው ትብብር መሠረት ለመጣል የሚያስችል ክሌአዊ ግኑኝነት መሆኑ በመግለጥ፣ አክለውም የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ለአንድ ኅብረተሰብ መግባባት እና ኅብረአዊ መቀራረብ መሠረት የሆነው ለሁሉም እና በሁሉም ሥፍራ ዋስትና ሊሰጠው ይገባል ብለዋል። ልዩነት አለ መግባባት እና ቅድመ ፍርድ ለማስወገድ የቲበታውያን ሃይማኖታዊ መለያ ለማቀብ ቻይና ከዳላይ ላማ ጋር ውይይት ማድረግ ይኖርባታል፣ ይህ ጂ2 የሚል መጠሪያ የተሰጠው የስምነቱ በኢንዳስትሪ የበለጸጉት አገሮች ቡድን አባላት ውስጥ በኢዳስትሪ ከፍተኛ ብልጽግና አላቸው የሚባሉት የሁለቱ አበይት አገሮች ግኑኝነት በሁለቱ አገሮች የሚደረገው ግኑኝነት እና የጋራው ትብብር ለዓለም ሰላም እና ብልጽግና አጅግ አስፈላጊ መሆኑ ሁለቱ ርእሳነ ብሔር አስምረውበታል።

ርእሰ ብሔር ሁ ጂንታኦ በተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት እያካሄዱት ያለው ይፋዊ ጉብኝት የሁለቱ አገሮች ግኑኝነት በበለጠ በማሻሻል ለማጠናከር መሆኑ በማብራራት፣ መንግሥታቸው የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ኵላዊነት ገጽታውን እንደሚያምንበት ገልጠዋል። በሁለቱ አገሮች በ 45 ሚሊያርድ ዶላር የሚተመን የግብአተ ምርት አቅርቦት የስምምነተ ሰነድ መፈራረማቸው ተገልጠዋል።

በኢጣሊያ ላ ስታምፓ ለተሰኘው አለታዊ ጋዜጣ ጋዜጠኛ የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ፖለቲካ ሊቅ ፓውሎ ማስትሮሊሊ የቻይና እና የተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት የጋራው ግኑኝነት በተመለተ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ሲያብራሩ፣ የተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት በ 45 ሚሊያርድ ዶላር የሚተመን የምርት አቅርቦት እንድታከናውን እና ይህ ደግሞ በተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት 230 ሺሕ የሥራ እድል የሚፈጥር ስለዚህ በሌላው ረገድ በአገሪቱ ያለው የሥራ አጥነት ችግር በገሚሱ የሚፈታ ስምምነት ነው። ስለዚህ አሜሪካ ይኽ ስምምነት ችላ ልትለው አትችልም። የሁለቱ አገሮች ግኑኝነተ እና ስምምነት ብዙ የኤክኖሚ፣ የሥነ ኤክኖሚ ፖለቲካ ሊቃውንት እና መንግሥታትም የሁለት በኢንዳስትሪ የበለጸጉት አገሮች ቡድን እርሱም ጂ2 በሚል መጠሪያ በመሰየም በዓለም አቀፍ ደረጃ ሁለት አበይት እና ኃያላን አገሮች በማለት ገልጠዉታል። በኤኮኖሚው ረገድ መሠረታዊ ስምምነት ያደረጉ ቢሆንም ቅሉ በፖለቲካው መስክ በሁለቱ አገሮች ያለው ልዩነት አሁንም እንዳለ ነው ብለዋል።

ቻይና የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ኵላዊነት ገጽታው እንደምታምንበት በቃል በማሳወቅ በዚሁ ጉዳይ አቢይ እርምጃዎች እያረጋገጠች መሆኑዋ ርእሰ ብሔር ሁ ጁንታኦ በማብራራት፣ ሆኖም ግን ቻይና ሕዝባዊ ረፓብሊክ አገር በመሆንዋ እርሱም የአገር ልማት እና ብልጽግና ከሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ቅድሚያ የሚሰጠው ርእሰ ጉዳይ መሆኑ ያመለከቱ እንደሚመስል ጋዜጠኛ ማስትሮሊሊ በሰጡት ቃለ ምልልስ ገልጠው፣ የሰላም ኖቤል ተሸላሚው ቻይናዊ አሁንም በእስሥር እንዳሉ ነው። ሆኖም ርእሰ ብሔር ሁ ጂንታኦ የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ጉዳይ በተለከተል የሰጡት መግለጫ ተስፋ ያለው ነው ቢባልም ቅሉ፣ የተባበሩት የአሜርካ መንግሥታት በቻይና የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ እንዲረጋገጥ የምታካሂደው ግፊት ምን እንደሚመስል እና እንዴት እንደምታከናውነው እንቀጥሎ የሚታይ ጉዳይ ነው ብለዋል።

የተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት በባህላዊው በፖሊቲካው እና በኤክኖሚው ዘርፍ በኤውሮጳ ላይ አቢይ የፍላጎት ዝንባሌ አላት፣ ኤውሮጳ ለተባበሩት መንግሥታት በሁሉም መስክ የበለጠ ቅርብ ነች። የተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት ለሚከተለው የጸረ አሸባርያን ትግል የትብብር እና ትሥሥር ድጋፍ ታማኝ እና አስተማማኝ የሆነው ክፍለ ዓለም ኤውሮጳ ነው። ይህ ደግሞ የአፍጋኒስታን እና የኢራቅ ወቅታዊ ሁኔታ የሚያረጋግጠው እውነተ ነው። በመሬት ሥነ አቀማመጥ ፖለቲካ በሩቅ ምሥራቅ ክልል ቻይን አቢይ ተጽእኖ ያላት አገር በመሆኑ ሂደት እውቅና በማግኘቱ ጭምር እያደገች በመሆንዋ የተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት ከዚህች ኃያል እየሆነች ካለቸው አገር ጋር ያለው ግኑኝነት ማጠናከር ግድ ይሆንበታል በማለት የሰጡትን ቃል ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.