2011-01-22 14:41:54

ቅድስት መንበር በተለያዩ ሃይማኖቶች ስለ ሚከናወነው የጋራ ውይይት


በተለያዩ ሃይማኖትች መካከል የሚደረገው የጋራው ውይይት በተመለከተ በግብጽ ርእሰ ከተማ ካይሮ ከሚገኘው የአል አዝሃር መንበረ ጥበብ ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ አሊ አብደል ዳየም፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በክርስትያኖች ምእመናን ላይ የሚወርደው በደል የሞት አደጋ እና የሃይማኖት እና የአምልኮ ነጻነት ረገጣ እንዲወገድ አደራ በማለት በተለያዩ ሃይማኖት መካከል በሚደረገው RealAudioMP3 የጋራው ውይይት አማካኝነት ጸረ ክርስትያን አመጽ ጨርሶ እንዲወገድ ያቀረቡት ጥሪ የምስልምና ሃይማኖት የሚተች እና ሙስሊሞች በመካከለኛ ምሥራቅ የሌሎች ሃይማኖት ምእመናን ያንገላታሉ ይጨቁናሉ የሚል አሰተያየት የሚያሰማ ነው በማለት የዚህ የምስልምና ሃይማኖት የቲዮሎጊያ ማእከል ከቫቲካን ጋር የሚደረገው ውይይት የሚከታተለው ኮሚቴ ላልተወሰነ የጊዜ ገደብ ከቫቲካን ጋር የሚያካሄደው ግኑኝነት እና የጋራው ውይይት እንዳቋረጠ የሰጠው መግለጫ መሠረት በማድረግ፣ የቅድስት መንበር የዜና እና የህትመት ጉዳይ ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ከተለያዩ ሌሎች ሃይማኖቶች ጋር የሚደረገው ውይይት የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ተከስቶ ያለው አለ መግባባት ተወግዶ የጋራው መረዳዳት እዲረጋገጥ አስፈላጊ መረጃዎችን እያሰባሰበ መሆኑ ትላትና ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ በማሳወቅ፣ የተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል የጋው ውይይት የሚያነቃቃው ጳጳሳዊው ምክር ቤት ከሌሎች ሃይማኖቶች ጋር የሚደረገው የጋራው ውይይት አስፈላጊነቱ እና ከሌላው ጋር ለመወያየት እራስን ክፍት ማድረግ የሚለው ሥልት አሁንም የሚከትለው መንገድ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.