2011-01-17 14:13:17

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ለውህደት የሚደረገው ጉዞ የእግዚአብሔር ተግባር ውጤት ነው


የአገረ ፊንላንድ ጠባቂ ቅዱስ ኤንሪኮ በዓል ምክንያት ሁሌ በየዓመቱ የፊንላድ ሉተራን አቢያተ ክርስትያን መንፈሳዊ መሪዎች በጋራ በሮማ ከተማ እና በቫቲካን መንፈሳዊ ንግደት የማካሄድ ባህል መሠረት በሮማ መንፈሳዊ ንግደት በማክሄድ ላይ የሚገኙት የፊላንድ ሉተራን ቤተ ክርስትያን ልኡካን ከትላንትና በስትያ በቅድስት መንበር ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ጋር መገናኘታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።

በየዓመቱ ስለ ክርስትያኖች አንድነት የሚከናወነው የጸሎት ሳምንት መርሃ ግብር ከአንድ RealAudioMP3 ሳምንት በኋላ እንደሚጀመር የሚታወቅ ሲሆን፣ ቅዱስ አባታችን እነዚህን ከፊንላንድ የመጡት የተለያዩ የሉተራን አቢያተ ክርስትያን መንፈሳውያን መሪዎችን በመቀበል የተለያዩ አቢያተ ክርስትያን ለአንድነት እና ለውህደት የሚያደርጉት መንፈሳዊ እና ባህላዊ ጥረት እና ጉዞ አስፈላጊነቱን በማስመር፣ በካቶሊክ እና በሉተራን ቤተ ክርስትያን መካከል ለውህደት ታልሞ የሚደረገው ጥረት ስለ ቤተ ክርስትያን አንድ ዓይነት የጋራ እይታ እንዲኖር በሚያግዝ የጋራ ትብብር ያጎለብቱ ዘንድ በማሳሰብ፣ ለአንድነት እና ለውህደት የሚደረገው ጥረት ተጨባጭ የተስፋ ምልክት እና የጋራ ውይይት በሚዳሰስ ተጨባጭ ክንዋኔ ተሸኝቶ የጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ፈቃድ ለማረጋገጥ እና በእርሱ ሁሉም አንድ እንዲሆኑ የሚለው የጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ጸሎት የሚያጎላ እና ይኸንን ለማረጋገጥ ታልሞ የሚፈጸም ግኑኝነት እና ውይይት መሆኑ ቅዱስ አባታችን ልኡካኑን ተቀብለው ባሰሙት ንግግር በማብራራት፣ እነዚህ የፊላንድ ሉተራን አቢያተ ክርስትያን ልኡካን በሮማ እና በቫቲካን የሚያካሂዱት መንፈሳዊ ንግደት በኵላዊት ቤተ ርክስትያን እና በሉተራን አቢያተ ክርስትያን እና በሁለቱ አቢያተ ክርስትያን ምእመናን መካከል ያለው አመርቂ ግኑኝነት የሚመሰክር፣ ቅርርብ ግልጽነት ወዳጅነት የትብብር መንፈስ የተካነ መሆኑ የሚያርጋገጥ ነው። ሆኖም ግን ሙሉ የእምነት ውህደት እንዲጨበጥ የሁሉም ጥረት ወሳኝ ነው፣ ለዚህ ዓላማ መረጋገጥ ሁሉም ካለ መታከት አቢይ ሚና እንዲጫወት አሳስበዋል።

ለአንድነት እና ለውህደት የሚደረገው ጥረት ግብ የእምነት አንድነት መረጋገጥ ማለት ሲሆን፣ ሆኖም ይህ ግብ ገና ያልተረጋገጠ መሆኑ አስታውሰው፣ ገና ብዙ ጥረት ይጠበቅብናል ካሉ በኋላ፣ ለውህደት እየተደረገ ያለው የጋራው ውይይት እና ግኑኝነት በሳል እየሆነ መሄዱ እና አወንታዊ ውጤቶችም እያስገኘ መሆኑ የማይዘነጋ ነው። የውህደቱ ግብ የጌታችን እየሱስ ክርስቶስ እርሱም ሁሉም አንድ እንዲሆኑ የሚለው ፈቃድ እና ጸሎት ነው ብለዋል።

በካቶሊክ እና በሉተራን አቢያተ ክርስትያን መካከል የሥነ ጽንድቅ ነገረ መሎኮት ርእሰ ጉዳይ በተመለከተ የሁለቱ አቢያተ ክርስትያን በአንቀጸ ሃይማኖት ሥር የተደረሰው የስምምነት ውሳኔ የሁለቱ አቢያተ ክርስትያን ለውህደት የሚደረጉት ጥረት አወንታዊ ውጤተ እያስገኘ መሆኑ ያረጋግጥልንናል ብለዋል። ይህ የስምምነት ውሳኔ ስለ ቤተ ክርስትያን እና ሐዋርያዊ ኃላፊነት በተመለከተ የጋራ ራእይ እንዲኖረ የሚያግዝ መሆኑና በሁለቱ አቢያተ ክርስትያን ያለው ተስፋ ውህደቱ እንዲረጋገጥ የሚደግፍ የቅዱስ መንፈስ ሥራ ነው። ውህደቱ ይረጋገጥ ዘንድ ዘወትር ደጋፊያችን እርሱ ነው ብለዋል።

ለውህደት የሚደረገው ጥረት፣ አድካሚ እና መሥዋዕት የሚጠይቅ መሆኑ በማንም የተዘንጋ እንዳልሆነ ቅዱስነታቸው በማስታወስ፣ ስለዚህ ዘወትር በጸሎት የተደገፈ መሆን አለበት። ውህደት የእግዚአብሔር ተግባር ውጤት ነው። ግብረ ሐዋርያት ምዕራፍ 2 ቁጥር 42 “እነርሱም የሐዋርያት ትምህርት በመስማት በወንድምማችነት አብሮ በመኖር እንጀራ በመቍረስና በጸሎት ይተጉ ነበር” የሚለው የአዲስ ኪዳን ቃል በመጥቀስ፣ ይህ የሐዋርያት ትምህርት ላይ የተመሠረተው ውህደት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፈቃድ የእኛ ጸሎት መሆኑ ገልጠው ይኽ ይረጋገጥ ዘንድ የመንፈስ ቅዱስ ድጋፍ እና ኃይል በመጸለይ ያሰሙት ንግግር እንዳጠቃለሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።








All the contents on this site are copyrighted ©.