2011-01-12 14:00:04

የኮንጎ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት


በኮንጎ የሕዝባዊ ምርጫ ሂደት ማስፈጸሚያ የሚፈሰው 700 ሚሊዮን ዶላር ወደ 350 ሚሊዮን ዶላር ለማጉደል ያግዛል በማለት እና በጠቅላላ ለብሔራዊ ሕዝባዊ ምርጫ የሚፈሰው የገንዘብ ሃብት ለመቀነስ፣ በአገሪቱ በመምራት ላይ ያለው መንግሥት RealAudioMP3 የምርጫ ጉዳይ የሚመለከተው ሕግ በሁለት ተራ እና በአንድ የቆጠራ ሥልት የሚለውን በአንዳዊ ተራ በሚል ሥልት እንዲተካ ለማድረግ እንደሚሻ የላምበርት መንደ መንግሥት በቃለ አቀባዩ አማካኝነት የተገለጠው የአገሪቱ መንግሥት ፖለቲካዊ ፍላጎት የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በኪንሻሳ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ላውረንት ሞስነግዎ ፓስንያ አማካኝነት ተቃውሞውን እያሰማ መሆኑ ተገልጠዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ሞንሰንግዎ ከለ ፖተንቲየል ከተሰኘው ዕለታዊ ጋዜጣ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ በመጀመሪያ ምርጫ ተገቢ የብዙሃን ድምጽ እርሱም 50 በአንድ የድምጽ ጭማሬ የብዙሃን ድምጽ ካልተገኘ ምርጫው ዳግም እንዲካሄድ የሚለውን በመተው፣ በአንድ ተራ እርሱም የብዙሃን ድምጽ መለያ የሆነው የብዛት መግለጫ በታች ድምጽ ያገኘ ለምሳሌ 20% ያገኘም ሊያሸንፍ የሚያደርግ አስቸጋሪ እና የብዙሃን መግለጫ ያልሆነው መንግሥት ለማቆም የሚያበቃው የምርጫ ሥልት ለማጽደቅ እየተገለጠ ያለው ፍላጎት ተቀባይነት የሌለው ነው እንዳሉ ጋዜጣውን የጠቀሰ አፒክ የዜና አግልግሎት አስታወቀ።

የአገሪቱ ተቃዋሚው የፖሊቲካው ሰልፍ ጭምር መንግሥት ያቀረበ ሀሳብ እንደማይደገፈው ያሳወቀ ሲሆን። ብፁዕ ካርዲናል ሞንሰንጉዎ የአገሪቱ መንግሥት የሕዝብ ፍላጎት መግለጫ የሆነው የምርጫ ሥልት ለማደስ የሚለው ፍላጎት በኤኮኖሚው ጉዳይ ላይ ተንተርሶ የሚወሰን ሳይሆን፣ በአገሪቱ የብዙሃንድ እና የውሁዳን ድምጽ ዋስትና የሚሰጥ የምርጫ ሥልት ሊከበር እና ገቢራዊ ማደረግ በሚለው መሠረታዊ አመክንዮ ላይ የጸና መሆን አለበት እንዳሉ ኤፒክ የዜና አገልግሎት ለ ፕተንቲየል የተሰየመው ዕለታዊ ጋዜጣ በመጥቀስ ያመለክታል።







All the contents on this site are copyrighted ©.