2011-01-12 13:59:08

ብፁዕ ካርዲናል ኮች፦ የቤተ ክርስትያን ተልእኮ


የቤተ ክርስትያን ተልእኮ እና ሚና ወደ ኅብረትሰብ የሚያቀናው በተለያዩ የመስህቦ ማስታወቂያ እና የፍጆት ገጽታ አማካኝነት፣ ወይንም በወረቀት ብቻ ሰፍረው በሚቀርቡ ሰነዶች ባዶ ቃላት በመሆን በመገናኛ ብዙሃን አማካኝነት የሚዘራ ወይንም RealAudioMP3 የሚቀርብ ሳይሆን በእኛ ዘንድ እርሱም በእያንዳንዱ ክርስትያን በግል እና በማኅበር በእግዚብሔር ማመን ያለው ውበተ እና ደስታ በመመስከር የሚገለጥ ሚና ነው። በጠቅላላ እምነታቸው በታመነ ተግባር በመኖር ምሥጢረ ጥምቀት በተቀበሉ ወንጌልን ሰብአዊ መልክ በሚሰጡ አማኞች አማካኝነት የሚገለጥ መሆኑ የክርስትያኖች አንድነት የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ኩርት ኮች ባለፈው እሁድ የ 2011 ዓ.ም. ዓለም አቀፍ የሰላም ቀን ምክንያት ሮማ በሚገኘው በቅድስት ካተሪና ዘ ሲየና በማኛናፖሊ ተገኝተው በሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው ባሰሙት ስብከት እንደገለጡ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ብፁዕ ካርዲናል ኮች ይላሉ እኛ ክርስትያኖች በዓለማችን በእያንዳንዳችን ልቦና ዘንድ ታትሞ ያለው የሃይማኖት ነጻነት ካለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ይረጋገጥ ዘንድ ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ ይጠበቅብናል በማለት፣ በአለማችን በብዛት ለስደት አደጋ እና መከራ የተጋለጠው ሃይምኖት የክርስትናው እምነት መሆኑ ገልጠው፣ በአለማችን 2.2 ሚሊያርድ ክርስትያን ምእመን እንዳለ ገልጠው በ 2008 ዓ.ም. 230 ሚሊዮክ ክርስትያን በክርስትና እምነቱ አማካኝነት የስደት ሰለባ መሆኑ እና ከጠቅላላው የክርስትያን ምእመን ብዛት አንጻር ሲታይ ደግሞ 80% የሚገመተው ክርስትያን በክርስትናው እምነቱ አማካኝነት ለስደት እና ምከራ መጋለጡ ነው የሚያብራራው። ይኽ ሁሉ ችግር የኵላዊት ቤተ ክርስትያን ተልእኮ የሚያሰናክል ቢመስልም ቅሉ ተልእኮው እንዳይከናወን ግን አያደርግም፣ ምክንያቱም በእምነት የሚከፈለው የደም ሰማዕትነት አማካኝነት እውነት እና ሕይወት የሚመሰክር ነውና እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.