2011-01-10 15:22:00

ኵላዊት ቤተ ክርስትያን፦ ድጋፍ እና ትብብር ለሃይቲ ሕዝብ ለማረጋገጥ


እ.ኤ.አ. ጥር 12 ቀን 2011 ዓ.ም. የዛሬ አንድ ዓመት በፊት በሃይቲ ተከስቶ በነበረው ርእደ መሬት ሰለባ የሆኑትን ለመዘከር ሮማ በሚገኘው ር.ሊ.ጳጳሳዊ ባሲሊካ ሳንታ ማሪያ ማጆረ የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ RealAudioMP3 መሥዋዕተ ቅዳሴ እንደሚያቀርቡ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።

በርእደ መሬት ለሞት አደጋ የተጋለጡት የሃይቲ ዜጎች ለማሰብ በቅድስት መንበር የሃይቲ ልኡከ መንግሥት መሥዋዕተ ቅዳሴ እንዲቀርብ በማሰብ ሙታንን ለመዘከር በሚያርገው መሥዋዕተ ቅዳሴ በቅድስት መንበር እና በኢጣሊያ የተለያዩ አገሮች ልኡካነ መንግሥታት ይሳተፉ ዘንድ ጥሪ ማስተላለፉም የቅድስት መንበር የዜና እና የኅትመት ክፍልል ካሰራጨው ዜና ለመረዳት ተችለዋል።

እንደሚዘከረውም በሃይቲ የዛሬ አንድ ዓመት በፊት ተከስቶ በነበረው ርእደ መሬት ሳቢያ 220 ሺሕ ሰዎች የሞት አደጋ እንዳጋጠማቸው እና በደረሰው አሰቃቂው ሰብአዊ እና ቁሳዊ ጉዳት ሳቢያም 500 ሺሕ ሕጻናት የሚገኙባቸው በጠቅላላ አንድ ሚሊዮን የሚገመተው የአገሪቱ ዜጋ በከፋ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ እና ባለፉት ወራት በተከሰተው የወረርሽኝ በሽታ ሳቢያ በሺዎች የሚገመቱት ጭምር ለሞት አደጋ መጋለጣቸው የሚታወስ ነው።

የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ለሃይቲ ሕዝብ ድጋፍ እና ለአገሪቱ ዳግመ ግንባት የሚቀርበው ድጋፍ እና ትብብር እርዳታ የሚያቀነባበረው ጳጳሳዊ የውሁደ ልብ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ሮበርት ሳራሕ ዛሬ ወደ ሃይቲ መነሳታቸው የቅድስት መንበር የዜና እና ኅትመት ክፍል ያሰራጨው መግለጫ ሲያስታውቅ፣ ብፁዕነታቸው ወደ ሃይቲ ከመነሳታቸው ቀደም በማድረግ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ለሃይቲ ሕዝብ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ድጋፍ ትብብር እና ቅርበት ለማቅረብ እና በቅዱስነታቸው ጸሎት ዘወትር የሚዘከሩ መሆንቸውንም ለማረጋገጥ ከዚህ አልፎም፣ ከአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ጋር ስለ አገሪቱ ሁኔታ በመነጋገር የሃይቲ ሕዝብ ለማዳመጥ እና አብሮ መሥዋዕተ ቅዳሴ ለማቅረብ የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን ቅርበት በማረጋገጥ እየቀረበ ያለው ድጋፍ እና ትብብር ሂደት እንደሚገመግሙ አስታውቀዋል።

ቅዱስ አባታችን በተደጋጋሚ የሃይቲ ሕዝብ እንዳይረሳ ያቀረቡት እና እያቀረቡት ያለውን ጥሪ በማስተጋባት የአገሪቱ ሕዝብ ዕለታዊ ሕይወቱን እና አገሩንም ጭምር ዳግም እንዲገነባ የሁሉም ድጋፍ እንዳይለው ጥሪ እንደሚያቀርቡ በመግለጥ ዳግመ ግንባታው ከሰብአዊ ዳግመ ግንባታ የሚነቃቃ የሕዝባዊ አገልግሎት መስጫ መዋቅሮች እና የግብርናው ኤኮኖሚ ዳግመ ግንባታ ማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑ ይኸንን ሐሳብ ለማካፈል የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት መሆኑ ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.