2011-01-10 15:20:44

በዓለ ጥምቀት ዘእግዚእነ


የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ትላንትና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማየ ዮርዳኖስ በእደ ቅዱስ ዮሓንስ የተጠመቀበት ዕለት አክብራ ውላለች። በዚህ ዓቢይ በዓል ሁሌ በየዓመቱ እንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ አማካኝነት ለሕፃናት እና የክርስትናን እምነት ለተቀበሉት ምሥጢረ ጥምቀት የምትሰጥበት ዕለትም ጭምር መሆኑ የሚታወቅ ነው። RealAudioMP3 ትላትና 14 ሕፃናቶ ወንዶች እና 7 ሕፃናት ሴቶች በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ መጠመቃቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. በ 2006 ዓ.ም. ለበዓለ ጥምቀት ያረገውን መሥዋዕተ ቅዳሴ መርተው ባሰሙት ስብከት፣ የምንኖርበት ዘመን የሞት ባህል ያንሰራፋበት ጸረ ባህል የሆነው ባህል እርሱም የታጠረ የተደበቀ የተደናገረ ሕይወት የሚኖርበት እና ከተለያዩ ችግሮች ለማምለጥ ሲባል ለተለያዩ አንደንዛዥ እጽዋት እጅ የሚሰጥበት፣ ከተጨባጩ ሕይወት ለማምለጥ አታላይ እና ጊዚያዊ ደስታ በሆነው ሕይወትን በሚያታለው የሓሰት መንገድ በኢፍትሃዊነት ተግባር ሌላውን ዋጋ ቢስ በማድረግ በማንቋሸሽ በጠቅላላ የሰው ልጅ ሰብአዊነት እየተዘነጋ እንደ ግኡዝ የሚታሰብበት መሆኑ በማብራራት፣ ወላጆች ይኽ ዓይነቱ ኢባህል በተዛመተበት ዓለም ቤተሰብ ይመሠርታሉ፣ ይኸንን ባህል በመጋፈጥም በእምነት ልጆቻቸውን ለማነጽ ይተጋሉ። ባላቸው እምነት ምክንያትም ልጆቻቸው የጥምቀት ምሥጢር ተካፋይ እንዲሆኑ ይፍቅዳሉ እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ሲያስታውስ።
እ.ኤ.አ. በ 2009 ዓ.ም. በበዓለ ጥምቀት ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት፣ ወላጆች ያላቸው እምነት በተመለከተ በሳል ግንዛቤ ካላቸው በርግጥ ልጆቻቸውን በእምነት ይመራሉ፣ ካልሆነ ግን እንደ ግእዙ እና እንደ ንብረት በማየት የገዛ ራሳቸውን ምኞች እና ፈቃድ መግለጫ እንዲሆኑ በማስገደድ ለተለያዩ ችግሮች እንዲጋለጡ ያደርጋሉ። የሚወለደው ሕፃን ምሉእ ነጻ ሰው መሆኑ በመገንዘብ ወላጆች ልጆቻቸው በእምነት ታንጸው የራሳቸው ጥሪ እንዲኖሩ አርአያ በመሆን በማነጽ ሰብአዊ እና መፍነሳዊ እድገት በማሟላታ ለማንከባከብ መጠራቸውን እንዲረዱ በማሳሰብ፣ የክርስትናው ባህል የተወለደውን ሕፃን ወደ እግዚአብሔር ብርሃን በመጥራት እውነተኛው ነጻነት ባለበት እርሱም የእግዚአብሔር ልጆች ከመሆን የሚገኘው ጸጋ እንዲቀበሉ ለሚያደርጋቸው የመለኮታዊ ሕይወት ጸጋዎችን እንዲታደሉ ብሎም እውነተኛው የነጻነት ትርጉም እየተረዱ የሚከተሉት የሕይወት ምርጫ ለመለየት የሚያግዛቸው የኃላፊነት ብቃት እንዲያጎለብቱ ያደርጋል እንዳሉ የሚዘከር ነው።
ወላጆች ልጆቻቸው ብርቱዎች እና ጤናማ አድርጎ ለማሳደግ በሚያደርጉት ጥረት ሕፃኑ የሚሻው ቁሳዊ እና እንክብካቤ ለማሟላት ዘለዓለማዊ ሕይወትን ለመታደል እግዚአብሔርን ማወቅ ማፍቀር እና በእማኔ ማገልገል ይኖርባቸዋል ሲሉ እ.ኤ.አ. በ 2008 ዓ.ም. በበዓለ ጥምቀት ባሰሙት ስክበት እንዳሰመሩበት የሚዘከር ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. በ 2007 ዓ.ም. ወላጆች በልጆቻቸው ሰብአዊ እና የመንፈሳዊነት ነጻነት ብስለት በመወሰኑ ረገደ የሚሰጡት አብነት እና ምስክርነት አቢይ ተጽእኖ እንዳለው ተገንዝበው፣ ምንም’ኳ በሥራው ዓለም እጅግ የተወጠሩ ቢሆንም በቤተሰብ ማዕድ እና ጥላ ሥር የክርስትናው እምነት ጽናት የሚያረጋግጠው የጸሎት መንፈስ እንዲኖር በማድረግ ኃላፊነት እንዳይጎድሉ አደራ እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ በማስታወስ ጠቅሶታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.