2011-01-05 13:13:00

ግብጽ፦ ለግብጽ ኦርቶዶክስ ምእመናን ድጋፍ እና ትብብር


እ.ኤ.አ. በአዲስ ዓመት በእስክንድርያ የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ርክስትያን ምእመናን ላይ በደረሰው የሽበራ ጥቃት ሳቢያ 23 ለሞት አደጋ መጋለጣቸው እና ሌሎች ከባድ እና ቀላል የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸውም ሲነገር፣ ከባድ RealAudioMP3 የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ምክንያትም ከቀን ወደ ቀን የሟቾቹ ቍጥር ከፍ ሊል እንደሚችል ይነገራል።

በግብጽ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ምእመናን እና ካህናት ደናግል በተጣለው ጥቃት ሰለባ የሆኑትን ለተለያዩ ችግሮ ተጋልጠው ለሚገኙት ቅርበት እና ትብብር በማረጋገጥ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ሲቻል፣ በግብጽ የፍራንቸክሳውያን ወንድሞች ማኅበር አለቃ ወንድም ካማል ዊሊያም ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የግብጽ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ለግብጽ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን እና ምእመናን እንዲሁም በደረሰው ጥቃት ሳቢያ ለተጎዱት እና ሰለባ ለሆኑት ቅርብ በመሆን በመጸለይ ላይ መሆንዋ ገልጠው፣ ማኅበረ ክርስትያን ብቻ ሳይሆን ሙስሊሞች ጭምር የተሰማቸው ጥልቅ ሐዘን እያሰሙ ናቸው። በእውነቱ የተጣለው ጥቃት እጅግ የሚዘገንን ነው፣ ጥር 7 ቀን 2011 ዓ.ም. የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት ለማክበር በመዘጋጀት ላይ ስትሆን፣ የግብጽ ኦርቶዶስክ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ርእሰ ቅዱስ ሲኖዶስ ሼኑዳ ሶስተኛ የተጣለው የአሸባርያን ጥቃት በዓለ ልደት ከማክበር መንፍሳዊ ተግባር አያግደንም እንዳሉ ኣባ ካማል ዊሊያም አስታውሰው፣ የጥልቅ አስተንትኖ በዓል ይሆናል ብለዋል።

በግብጽ የተለያዩ የሊጡርጊያ ሥርዓት የሚከተሉት የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ምእመናን ብዛት 250 ሺሕ መሆኑ ገልጠው፣ ብዛቱ ጥቂት ቢሆንም ቅሉ በአገሪቱ በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል መቀራረብ መተዋወቅ እና በከባበር እንዲኖር አገናኝ ድልድይ በመሆን ለማህበራዊ እና ሃይማኖታዊ ሰላም አቢይ አስተዋጽኦ የሚሰጥ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.