2011-01-03 16:15:18

የኤውሮጳ ኅበረት፦ የጸረ ድኽነት ዓመት ግምገማ


እ.ኤ.አ. 2010 ዓ.ም. ኤውሮጳ የጸረ ድኽነት ዓመት በሚል ስያሜ በዚህ ክፍለ ዓለም የሚታየውን ድኽነት ለመቀረፍ የተለያዩ የጸረ ድኽነት እቅዶች እንዲከናወኑ በማቀድ የተካሄደው የልማት እቅድ ምን ያክል ድኽነት እንዲቀረፍ RealAudioMP3 ማገዙ እና በተለያየ ችግር ምክንያትም በተነጠለ ሕይወት ተገለው የሚኖሩት ዜጎች ካጋጠማቸው ሰብአዊ ችግር ለማላቀቅ የሕንጸት እና የልማት እቅድ የተነቃቃበት ዓመት እንዲሆን ተወስኖ፣ ይህ የልማት እቅድ ከኤውሮጳ ህዝብ ብዛት ውስጥ 75 ሚሊዮን የሚገመተውን የሚመለከት ሲሆን፣ ለእነዚህ በድኽነት እና በተነተጠለ ሕይወት የተጠቁት የተሰጠው እና የቀረበው የድጋፍ እቅድ በማስመልከት የኤውሮጳ የካሪታስ የ2010 የኤውሮጳ የጸረ ድኽነት ዓመት መርሃ ግብር ለኢጣሊያ የድጋፍ እቅድ ጉዳይ ተጠሪ ፓውሎ ፐዛና ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ በፖለቲካዊ እና በሕግ እና የፍትህ ጉዳይ መድረክ በኤውሮጳ ቀጣይነት ያለው የጸረ ድኽነተ እና በተለያዩ ችግር ተገለው የሚኖሩት የኅብረተሰብ ክፍል ከወደቁበት ሰብአዊ ማኅበራዊ ቁሳዊ ችግር የማላቀቅ ዓላማ እንዲረጋገጥ ማድረጉ ወሳኝ ነው። የጸረ ድኽነት እቅድ የዘወትር ጥረት መሆን አለበት። ስለዚህ በ 2010 ዓ.ም. የጸረ ድኽነት እና የልማት እቅዶች ጉዳይ የሚያነቃቁ መርሃ ግብሮች በባህላዊ በመገናኛ ብዙሃን ጉዳይ ሥር በመንግሥታዊ መዋቅሮች ጭምር መከናወኑ በመግለጥ፣ የሰውን ልጅ ከማኅበራዊ ኑሮ የሚያገለው በተነጠለ ሕይወት እንዲኖር የሚያስገድደው ችግር ለመቅረፍ የሚደረገው ትግል አጥጋቢ ውጤት እያስገኘ ቢሆንም ካለፈ ዓመት ጋር አብሮ የሚያልፍ እቅድ ሳይሆን የሚቀጥል መሆን አለበት ብለዋል።

የጸረ ድኽነት ዓላማ ለማነቃቃት የመገናኛ ብዙሃን የመደቡት የገንዘብ እና የጊዜ ሃብት እጅግ አነስተኛ ከመሆኑም አንጻር ስለ ጸረ ድኽነት ዓላማ ተጠናክሮ ብዙ አልተባለም፣ የጸረ ድኽነት ዓላማ ሁሉንም የሚመለከተ ነው። የኤውሮጳ ኅብረት የትብብር ኅብረት የመቀራረብ የመቀባበል የመደጋገፍ ኅብረት መሆን አለበት ብለዋል።

በመጨረሻም በዓለምችን የሚታየው ድኽነት እና ድኽነት ከፍ እያለ እንዲሄድ የሚያደርገው ምክንያት፣ የአጋጣሚ ሳይሆን የሰው ልጅ የሚከተለው የሕይወት አብነት ውጤት ነው። ስለዚህ የታረመ በግብረ ገብ እና ስነ ምግባር የተካነ የሕይወት አብነት መከተል በዓለማችን በክፍለ ዓለም አቀፍ እና በአገር አቀፍ ደረጃ የሚታዩት ችግሮች ለመቅረፍ የሚቻል ነው። ስለዚህ የኤኮኖሚው እና የማኅበራዊው አድማስ ማገናኘት ወሳኝ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.