2011-01-03 16:13:19

ለክብረ በዓል እመ አምላክ ዋዜማ


የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ኵላዊት ቤተ ክርስትያን አዲስ ዓመት ማለትም ጥር አንድ ቀን በዓል አመ አምላክ የምታከብርበት ዕለት ሲሆን፣ በበዓሉ ዋዜማ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እ.ኤ.አ. ታህሳስ 31 ቀን 2010 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ የመጀመሪያ ጸሎተ ሰርክ በመምራት ባሰሙት ስብከት፣ ዘለአለማዊ እግዚአብሔር በሰው ልጅ የጊዜ ሁኔታ ውስጥ በመግባት የዓለም አዳኝ በሆነው RealAudioMP3 በእየሱስ ክርስቶስ አካል በዓለም እና በሰው ልጅ ጊዜ ውስጥ በሙሉ ተሳታፊነት በመቅረት የሰውን ልጅ የእግዚአብሔር ዘለዓለማዊ ሕይወት ተሳታፊ እንዲሆን ገዛ እራሱንም በሰው ልጅ ጊዜ በሙላት ተሳታፊ አድርገዋል እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።

ኵላዊት ቤተ ክርስያን በዓመት መገባደጃ እርሱም ታህሳስ 31 ቀን ከምሽቱ አዲስን ዓመት በተስፋ ለመቀበል እና ባለፈው ዓመት እግዚአብሔር ላደረገልን ሁሉ ለማመስገን በላቲን ሥርዓት Te Deum Laudamus እግዚአብሔር እኛ እንወድስሃለን በሚል ስያሜ የሚታወቀው የምስጋና ጸሎት በመድገም ካቶሊክ ቤተ ክርስትይን ጥር አንድ ቀን የምታከብረው በዓለ እመ አምላክ በጥልቅ መንፈስ በማሰብ፣ ምንም’ኳ በዚህ በምንኖርበት ጊዜ ችግር መከራ ስቃይ የሚያጋጥመን ቢሆንም የሰው ልጅ በተለይ ደግሞ ባልተረጋገጠ ኑሮ በስፋት እየተጠቃ ያለው ቤተሰብ በማሰብ ሁሉም የሰው ልጅ መጪውን ሕይወት በተስፋ እንዲመለከት አደራ ብለዋል።

ዓመት ወራቶቹ ሳምንታት ቀናት በጠቅላላ የዕለታዊ ኑሮ ጊዜ የእግዚአብሔር ፍቅር ጸጋዎቹ ማደሪያው ያደረገ የመዳን ጊዜ ነው። እዎን ዘለዓለማዊው እግዚአብሔር በሚፈራረቀው ጊዜ ውስጥ እራሱን በማሳተፍ ዓለም በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አካል አማካኝነት አድነዋል።

የእኛ ግዜ ይላሉ ቅዱስ አባታችን፣ ክፋት ስቃይ በጠቅላላ የተለያዩ ችግሮች የሚፈራረቅበት ሰው ስራሽ እና የተፈጥሮ አደጋ አማካኝነት በሚደረሰው ስቃይ እጅግ ብንጎሳቆልም የደረሰ ችግር ቢደርስም የክርስቶስ አዳኝነት የሚሰጠው ደስታ እና ነጻነትን ግን ፈጽሞ አይሰርዘውም። በዚህ የአበይት በዓላት ወቅት ብዙዎች ገና በስቃይ እና በመከራ የሚኖሩትን በማሰብ ቅዱስነታቸው የሚሰቃየው ሁሉ በጸሎታቸው እንደሚያስቡዋቸው አረጋግጠዋል።

በመጨረሻም እዚህ ሮማ በሚገኘው የባቡር ጣቢያ የተርሚኒ ክልል ባለው ካሪታስ በሚል መጠሪይ በሚታወቀው የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን የተራድዖ ማኅብር የኢጣሊያ ቅርንጫፍ የሚያስተዳድረው በድኾች መርጃ ማእከል ያካሂዱት ሓዋርያዊ ጉብኝት ዘክረው፣ በሰብአዊ መንፈሳዊ ችግር በጠና የሚሰቃዩትን ቀርቦ በመደገፍ የእግዚአብሔር ፍቅር በዕለታዊ ኑሮአቸው የሚያጣጥሙ የሚኖሩ የተባረኩ ናቸው በማለት፣ በዚህ በምንኖርበት ዘመን ቤተሰብ ለስቃይ የሚዳርገውን ዘርፈ ብዙ ችግር በማስታወስም ቁምስናዎች በስቃይ ላይ ለሚገኙት ቤተሰብ ድጋፍ ይኖሁ ዘንድ አደራ ካሉ በኋላ፣ እግዚአብሔር የተወደደውን አንድ ልጁች ለእኛ እስከ መስጠት ያስገደደው ፍቅር የእያንዳንዳችን ልብ በማቃጠል የሚሰዋ ፍቅር አገልጋዮች ያደርገን ዘንድ መጸለያቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።








All the contents on this site are copyrighted ©.